Netsanet: März 2015

Dienstag, 31. März 2015

በየመን ኢትዮጵያውያኖች በጭንቅ ላይ ናቸው

ግሩም ተ/ሀይማኖት (ከየመን)
 
ረቡዕ ሌሊት 8፡30 ላይ የተጀመረው የአየር ድብደባ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ የመን ነዋሪ የሆነ ሁሉ በፍርሃት ርዷል፡፡ በተለይ በትላንትናው ሌሊት የነበረው የአየር ድብደባ ከፍተኛ ስለሆነ ህዝቡ ላይ የጣለው ፍርሃት ከወትሮው የተለየ ነው፡፡ “በሁቲይን አማጽያን ሚሊሻ ላይ የተጀመረው የአየርጥቃት አሁንም በድርድሩ ካልተስማሙ ወይ ሰነዓ ከተማን ለቀው እስካወጡ አያቆምም!” ሲሉ የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ ገልጸዋል፡፡ ይህን አባባላቸውን ተከትሎ እግረኛ ሰራዊትም ሊንቀሳቀስ መሆኑ እየተገለጸ ነው፡፡ 20.000 እግረኛ ወታደር ተዘጋጅቶ ድንበር ላይ መሆኑን የየመን መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ተጀምሮ የነበረውን ድርድር እንዲቀበሉ ለሁቲይን አማጺዎች ከትላንት ወዲያ የ3 ቀን እድሜ ቢሰጣቸውም አልተቀበሉትም፡፡

 
በሳዑዲ ሰብሳቢነት የአረብ ሊግ ሀገራት መንግስታት በየመን ጉዳይ ለመመከር ግብጽ ሻርማ ሸኸ ተሰብስበው ነው ያሉት። በዚህ ስብሰባ ላይ የአየር ጥቃቱ የዘመቻ መሪ ሀገር የሳዑዲ አረቢ ንጉስ ሰልማን ሀቲይን የተባሉት አማጽያን ለቀው እስኪወጡና የመን እስክትረጋጋ ድረስ የተጀመረው ጥቃት ቀጣይ እንደሆነ ገልጸዋል በማለት የየመኑ ቶውራ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ የየመኑ መሪ አብድረቡ መንሱር ሀዴ ተገኝተዋል፡፡ ህዝቡ ግን ሀገራችንን እያስደበደበ ያለው ፕሬዘዳንታችን ነው በማለት ጥስ እየነከሰባቸው ነው፡፡ የቀድሞው ፕሬዘዳንት አሊ አብደላ ሳላ ድርድሩን እንደሚቀበሉ ቢገልጹም ተቀባይነት ያገኙ አይመስልም፡፡

 
ዛሬ ሌሊት በሳውዲ የተመራው የአስሩ ሀገራት ህብረት ጦር በሰንዓ ፈጂ አጣን የተባለው ቦታ ጋራ ላይ የሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ያለ የብላስቲክ ሚሳየል ክምችት ማውደሙ ታውቋል፡፡ ይህ የመሳሪያ ክምችት በተመታበት ወቅት መላ ከተማው የተርገደገደበት የመሬት መንቀጥቀጥ አይነት ሁኔታ ነበር፡፡ አንዳንድ ህንጻዎች መስታዎታቸው ሁሉ ርግፏል፡፡ ነዋሪው ሲነጋ እንቅልፍ አጥቶ መደሩ ዋነኛው ርዕስ ነበር፡፡ በተለይ ስደተኛ ኢትዮጵያዊን ከፍተኛ ፍርሃት ተውጠን እንዳለን በርካታ ያናገርኳቸው ወገኖቼ ገልጸውልኛል፡፡ በእርግጥ ሌላውስ ወገን የመን ያሉ ኢትዮጵያዊያንን እንዴት እያሰባቸው ይሆን?
 
የተመታው ካምፕ ላይ የሚቃጠለው መሳሪያ ፍንዳታም ከፍተኛ ነበር፡፡ ከሌሊቱ 8፡20 ጀምሮ ጠዋት ድረስ እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ ነበር፡፡ የሁቲይን አማጺያን ድብደባውን በዝምታ እያዩት አይደለም፡፡ ከየአቅጣጫው በአየር መቃወሚያ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ 
እንደ አባባላቸው ከሆነ የአየር ጥቃቱን ከሚያደርሱት ጀቶች እስካሁን ሁለት መምታታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዛሬው ሌሊት ሰነዓ ላይ ድብደባው ቀነስ ቢልም ሁዴዳና ሌሎች ደቡባዊ የመን ላይ ጠንከር ያለ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ሁቲይኖቹም ከየአቅጣጫው የሚደረገውን ጥቃት ለመከላከል ሙከራቸው በዛሬው ሌሊት ቀንሶ ታይቷል፡፡ ሰነዓ ያለ ኢትዮጵያዊ በጭንቅ ውስጥ ሲሆን አደን የተባለው ሁለተኛ ከተማ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊን በከፍተኛ ሁኔታ እያነቡ ነው፡፡

Montag, 30. März 2015

የይቅርታ ደብዳቤ ለጃዋር መሐመድ (ሄኖክ የሺጥላ)

ውድ ጃዋር ፣ ሳልውቅ ፣ ጠነኝነቴ አሳስቶኝ ፣ አንተም ምንም የመረረ እና የተንዛዛ ዘረኛ ብትሆንም ቅሉ ፣ ጤነኛ ነህ ብዬ ፣ እንደ አንድ ሰው ልወቅስህ አስቤ ፣ ባንተ ላይ የጻፍኩዋቸው ጽሁፎች ፣ አሁን አንተን በደንብ ሳውቅ እና ስላንተ ስረዳ ፣ ይህንን የይቅርታ ደብዳቤ መጻፍ እናዳለብኝ ተረድቻለሁና ፣ ደብዳቤን አርቅቄ ይኸው ይደርስህ ዘንድ ይሁን።Jawar Mohamed Muslim fundamentalist
ውድ ጃዋር ሆይ ፣ እንደምን ከርመሃል ? መቼም መጻፍ አስቸግሮኝ አያውቅም ፣ ይህንን ጽሑፍ ግን ለመጻፍ ስዘጋጅ ያየሁትን ፈተና እኔና መድሃኒያለም ነን የምናውቀው ። በመጀመሪያ ፣ ስለ አንተ በደንብ ከተረዳሁ እና ካወቅሁ በሁዋላ ፣ እንዴት አድርጌ ብጽፈው ፣ ይቅርታዬ ሊገባው ይችላል ብዬ ተጨነኩ ፣ ቀጥሎ ከዚህ ሁሉ የእርማት እና ፊደል የመልቀም ሥራ በሗላስ በእውነት የጻፍኩት ይገባው ይሆን ብዬ ድጋሚ ተጨነኩ ። መቼም እንደ አንተ አይነት ወንድሜን ፣ ያለብህን ችግር እና ይሄን ሁሉ ነገር የሚያናግርህን ነገር ሳላውቅ ፣ ያን ያህል ነገር መናገር አግባብ አለመሆኑን መረዳቴ እንዴት እንደቆጨኝ ማን በነገረህ?
ውድ ጃዋር ሆይ ። እንደምታውቀው ሰሞኑን አንድ ” ፍገራ ኒውስ ” በሚል ርእስ ስር ተቀናብሮ ፣ በኢትዮ-ትዩብ በኩል ለኛ ” ለተደራስያን ” ( አድማጭ አላልኩም ) የቀረበልንን ነገር ተመለከትኩ ። ደግሜ ደጋግሜ ተመለከትኩ ። ከዚያ በራሴ እና ለራሴ ምርር ብዬ አለቀስኩ ። ለምን መሰለህ ፣ ይቺ ኢትዮጵያ ሀገራችን ሰው እንደሌላት ፍንትው ብሎ ታየኝ ። አንተን የመሰለ ሸበላ ፣ አንተን የመሰለ ሰው ፣ እንዲሁ ከበው ሲወቅሱ ፣ ሲያሞግሱ ፣ እና ወዘተ ሳይ በጣም አዘንኩ።
ጃዋር ሆይ ። እንደምታቀው ሜንጫ ማለት ቦክስ እንደማለት ነው ። ይህም ማለት እንደው ባጋጣሚ አሩሲ ውስጥ ተሳስተህ አንድ ነገር ብትናገር ፣ በሜንጫ ቦክስ ፊትህ ሊያብጥ እንደሚችል ነው ። አንዳንድ ሰዎች ግን ፣ አይ ሜንጫ ቦክስ አይደለም ፣ ሜንጫ ካራ ወይም ስለት ነው እያሉ ሲከራከሩ ሰማሁ ። ይሄማ ሊሆን አይችልም ብዬ ወገቤን ይዤ ተከራከርኩ ። ምክንያቱም “ሚኒሊክ ጡት ቆረጠ!” ብለው የሚንጫጩ ሰዎች ፣ በፍጹም ሜንጫን እና ቦክስን አንድ ሊያደርጉ ስለማይችሉ እና እኔም በግሌ ስለማውቅ ። እና ታዲያ የይቅርታዬ መጀመሪያውም መጨረሻውም እዚህ ጋ ይጀምራል ። ትዝ ይልህ ከነበር ባለፈው ፣ ” አንገቱን በሜንጫ ነው የምንለው ” ብለህ አልነበር ? እና’ልህ ህዝቡ አንገቱን በስለት ነው የምንቆርጠው ማለቱ ነው ብሎ በጣም አዝኖ ነበር ። አሁን ግን ዕድሜ ለ “ኢትዮ- ትዩብ” ሜንጫ ምን ማለት እንደሆነ አንተ በሰጠኸው መልስ ስለተረዳው እና ስላወቅሁ፣ ሜንጫ ማለት ቦክስ ማለት ከሆነ ፣ እኔም ራሴ ስቧቀስ ስላደኩ ፣ አዎ ሜንጫ ማለት ቦቅስ ማለት ከሆነ ፣ ታዲያ ጃዋር ምን አረገ ብያለሁ።
በነገራችን ላይ ጃዋር ፣ እኔ የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ እና አዲስ አበባ ሳለሁ ” የቦቅስ ፌድሬሽን ” የሚባል ነገር አውቅ ነበር ፣ እንደውም ባብዛኛው የአብነት ልጆች ናቸው የሚሳተፉት እኔ በነበርኩበት ( በማስታውስበት ) ሰዓት ማለት ነው ። እንዴት ነው አሩሲ የሜንጫ ፈድሬሽን የሚባል ነገር አለ ወይ ? ካለስ ባመት ስንት ግዜ ነው የሚደረገው ? ለውድድሩ ብቁ የሆኑ ተሳታፊዎች የመወዳደሪያ መስፈርታቸው ምን ይሆን ? አንደኛ ዲቪዚዮንን ከሁለተኛ ዲቪዚዮን የሚለየው የሜንጫው ክብደት ነውን ? ወይስ በመንጫው ኖክ አውት ታደረጉትን ሰው ብዛት ቆጥሮ ” አንተ ብቁ ነህ አንተ አይደለህም ” የሚል መስፈርት አለ ወይ ? እንዴት ነው መጀመሪያ በጩቤ እጃቸውን ካፍታቱ ወዲያ ነው ወይ ወደ ሜንጫ ዲቪዚዮን ከፍ የሚሉት ?። አንድ ወዳጄ ይህንን ጽሑፍ ስጽፍ አጠገቤ ቁጭ ብሎ ( እንዲሁ ጣልቃ እየገባ) ” በናትህ ሔኒ አሩሲ የገጀራ ፈድሬሽንስ አለ ወይ ?” በለው አለኝ ፣ እኔ እንኳ እንዲህ አይነት የልጅ ጥያቄ አንተን ለመሰለ ትልቅ ሰው ማቅረብ እንደማይገባኝ አውቃለሁ ፣ ግን ግን ሜንጫ ማለት ቦክስ ማለት እንደሆነ የታወቀ ነው ( እሱንም አንተ ወንድሜ ጃዋር ነግረኸኛል ) ፣ ገጀራስ ምን ማለት ይሆን ፣ እንዲሁ ስገምት ግን ጥፊ ይመስለኛል ። ቆንጨራስ ?ቴስታ ማለት ይሆን ? ትርጉም እኮ እንደ ተርጏምው ነው ። ሞኝ አይሙት እንዲያጫውት ያሉት አማሮች ናቸው ? እነሱንማ በሜንጫ ቦክስ ማለት ነበር ልል አልኩና ፣ ጃዋር ብሎት የለ እኔ ብደግመው ምን ዋጋ አለው ብዬ ተውኩት።
ለማንኛውም እነዛ በሜንጫ ቦክስ ታፍረውና እና ተከብረው የኖሩትን ሜንጫኞች ፣ የአኖሌ ሃውልትም በዚህ አካሄድ በጠረባ እንደተሰራ ያውቁ ይሆን አይሆን ትጠይቅልኝ ዘንድ ጠይቄ ጽሁፌን ላብቃ!

Samstag, 28. März 2015

ማሞ ሌላ ፎቶግራፉ ሌላ – የፍራንክፈርቱ የኦህዴድ ስብሰባ

በልጅግ ዓሊ
ከጥቂት ዓመታት በፊት ጀርመን ፍራንክፈርት ማርዮት ሆቴል ውስጥ “ኢንቬስተሮችን“ ለመሳብ በሚል ፈሊጥ አባዱላ ገመዳ በተገኘበት የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች ስብሰባም ተጠርቶ ነበር። በዕለቱ ተቃዋሚዎች ከደጅ ተኮልኩለው ወያኔን በመቃወም ላይ ነበሩ። በሁለት ስለት ቢላዋ መብላት የዘመኑ ብልጠት በመሆኑ፤ የቤት መስሪያ ቦታ መደለያ ለማግኘት የሚቋምጡ ሁሉ በዚህ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ነበር። በተለይ የወያኔ ደጋፊ የሆኑ “የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ኢንቬስተሮች“ አለያም በዘመኑ አጠራር የልማት ባለሃብት ተብዬዎች ማንነታቸው በሰልፈኞቹ እንዳይለይ በመፍራት ማንነታቸውን በመነጽርና ኮፍያ ውስጥ በመደበቅ ወደ አዳራሹ ይገቡ ነበር። በሌላ ስልት ደግሞ ከተቃዋሚዎች መሃል አንዳንዶች ገብተው ስብሰባውን እንዲካፈሉና የስብሰባውን ይዘትና ጭብጥ ተረድተው እንዲወጡ ተደርጎ ነበር። ቀደም ሲል በስንት ጣር በመነጽርና በኮፍያ ታግዞና እራሱን ደብቆ የገባው “ኢንቬስተር“ ተሽቀዳድሞ ወደ ሽንት ቤት በመግባት ጣጣ እንደሌለበት ሰው ኮፍያውንና መነጽሩን አውልቆ፣ አለባበሱን አስተካክሎ ወደ ስብሰባው አዳራሽ ብቅ ሲል ከውስጥ ቀደም ሲል ሆን ተብሎ ለማጥናት የገባው ተቃዋሚ ይጠብቀዋል። እንደገና ሌላ መደናገጥ ይፈጠራል። ግማሹ መግቢያ ያጣል ፣ ግማሹ እንዳላየ አይቶ ለማለፍ ይሞክራል፣ አንዳንዱ ደግሞ እንደምንም እራሱን አረጋግቶ የማስመሰል ጨዋታውን ይገፋበታል።
እንደ አጋጣሚ በእለቱ ስብሰባ ላይ በቅርብ የማውቀው ተቃዋሚ የነበረ ወዳጄ ተገኝቶ ነበር። አዳራሹ ውስጥ ከሰልፈኛው ተሽሽጎ የገባ “ግማሽ ኢንቬስተር“ “ግማሽ ተቃዋሚ“ ከሆነ ሰው ጋር ይገናኛሉ። ይህ ከሆነ በኋላ “ኢንቬስተሩ“ ሁኔታው መሰማቱ አይቀርም በሚል ብዙዎቻችን ጋር እየደወለ ሃጢአቱን ያስተባብል ጀመር። “እኔ የሠራሁት ቤት እንዳይወረስብኝ ብዬ እንጂ ሌላ ነገር ፍለጋ አይደለም። እኔ ወያኔ አይደለሁም… ወዘተረፈ ብቻ ያልለፈለፈው የለም። እኔም በውል አዳምጬው ሳበቃ ስብሰባውን ወደ ተካፈለው ሌላ ተቃዋሚ ደውዬ የስብሰባው ውሎ እንዴት እንደነበር? ብዬ ጠየቅሁት። ሃቁ ግን “ግማሽ ኢንቬስተሩ“(ልማታዊ ባለሃብቱ) እንደነገረኝ ሳይሆን እንደውም በተቃራኒው ስብሰባው ላይ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል እንደነበረና ቀንደኛ ተዋናይ ሆኖ እንደዋለ አስረግጦ ነገረኝ። የአባ ዱላ ስብሰባ “የግማሽ ኢንቬስተሩ“ “የግማሽ ተቃዋሚነት“ ሚናው የመጨረሻው ሆነ። ይህ ግማሽ “ኢንቬስተር“ ከአባ ዱላ ስብሰባ በፊት በተቃዋሚዎች ስብሰባም ላይም እንዲሁ ያዙኝ ልቀቁኝ ባይ ነው።
በአሁኑ ወቅት አያሌ ለሆዳቸው ያደሩ ባንዳ “ኢንቬስተሮች“ ከተቃዋሚው ጋር “ተቃዋሚ“ ከወያኔው ጋር ቀንደኛ ወያኔ ሆኖ የመታየት አባዜ እየተጠናወታቸው መጥቷል። ወያኔ በየጠራው ስብሰባ እየሄዱ የግል ጥቅማቸውን እንደሚያሳድዱ ሁሉ በተቃዋሚው አካባቢ ደግሞ ተቃዋሚ ሆኖ ለመታየት የማያደርጉት ጥረት የለም። በአዘቦቱ ቀን ከወያኔ ደጀሰላም (ቆንስላ) እንደማይጠፉ ሁሉ በተቀቃሚ እንቅስቃሴዎች ደግሞ እንዲሁ በለመደባቸው ቀንደኛ ተዋናይ ሆነው መታየትን ይሻሉ። ለእነዚህ አድርባዮች ዋናው ጠላታቸው ደግሞ ፎቶ ነው። መረጃ በሁለቱም(በተቃዋሚም ሆነ በወያኔ) በኩል ማስያዝ ስለማይፈልጉ ፎቶ መነሳት እርማቸው ነው።
የእነዚህ “የልማት ባለሀብቶች“ የጥፋት ተልእኮ በአሁኑ ወቅት ፍራንክፈርት ውስጥ በጣም ጎልቶ እየታዬ ነው። “የትግራይ ልማት“ አስረሽ ምችው፣ የባለ ራእዩ መሪ ተስካር፣ የወያኔ ምሥረታ በዓልና የትራንስፎርሜሽኑ ድግስና አሸሼ ገዳሜ እየተገኙ ፊታውራሪነታቸውን ለማረጋገጥ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ለዓብነት በቅርብ የተካሄደው የኦህዴድ (የወያኔ የኦሮሞ ክንፍ) 25ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በፍራንክፈርት በተከበረበት ወቅት የታየው ሁኔታ ጉልህ ማስረጃ ነው። በአካልም በቃልም ከታዘብነው ባሻገር የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ በዓይጋ ፎረም ድረ-ገጽ የተለጠፈውን አንብበናል። ግን ዜናውን ለሚያነቡ ትልቅ በዓል የተደረገ ይመስላል። እውነቱ ግን ከተራ ፕሮፖጋንዳነት ውጭ ሚዛን የሚደፋ፣ ወንዝ የሚሻገር አንዳች ጭብጥ የለውም። ሃቁ ደግሞ ወያኔ በፍራንክፈርት አትዮጵያውያንን በዘር ከቶ መከፋፈል የቻለበት አጋጣሚ እሰከዛሬ ድረስ አልተፈጠረም።
The OPDO meeting in Frankfurt በድረ ገጹ ላይ የተጻፈው የተውኔት(ተውኔት ያልኩበት ተዋንያኖቹ ስለገረሙኝ ነው) ትዕይንተ-ዜና ግን እንዲህ ይላል። “25ኛው የኦህዴድ የምስረታ በዓል በጀርመን ፍራንክፈርት ተከብሯል“ በሚል እርዕስ በፎቶ የታጀበ ዘገባ ቀርቧል። የፍራንክፈርት ነዋሪ እንደመሆኔ ዜናው ሳበኝና ለማንበብ ገጹን ከፍቼ ተመለከትኩት። ከዜናው ይበልጥ ከዜናው ጋር ተያይዞ የተለጠፈው ፎቶግራፉ ይበልጥ ስላስገረመኝ ቀልቤን ሳበው። መቼም ፍራንክፈርት ለኖርነው ፍቶው ላይ የምናያቸው “ኦሮሞዎች“ በአብዮታዊ ዴሞክራሲዊ የተሰጣቸው “የብሄር ብሄረሰብ“ ስያሜ ካልሆነ በስተቀር ለሃያ ዓመታት ሳውቃቸው የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት(ተሓህት) አባላት ናቸው። ለዚህ ነው ማሞ ሌላ ፎቶው ሌላ የሆነብኝ። ፕሮፖጋንዳውን ያነበብን ብዙዎቻችን ኦሮሞዎቹ የት አሉ? ብለን ጠይቀናል። እንደኔ እንደኔ ዜናው መሆን ያለበት “በፍራንክፈርት የሚገኙ ወያኔን የሚደግፉ የትግራይ ተወላጆች የኦህዴድን 25ኛ ዓመት ምሥረታን አከበሩ“ ቢባል እውነተኛ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም በስብሰባው ላይ የተገኙት በአብዛኛው የተሓህት አባላት መሆናቸውን በግልጽ ከፎቶው ብቻ መረዳት ስለሚቻል ነው። ያም ቢሆን በቁጥር አነስተኛ እንጅ ብዙዎቹ ሃቀኛ የትግራይ ተወላጆች በዚህ አጸያፊ ተግባር ላይ እንዳልተገኙ ፎቶግራፉ በውል ያስረዳል።
The OPDO meeting in Frankfurt ምንም እንኳን በፎቶው ላይ ባይታዩም በዚህ ስብስብ ውስጥ ጥቂት ኦሮሞዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ አውቃለሁ። እነሱም ቢሆኑ ደፍረው ግን ፎቶግራፍ መነሳት አይሹም። ሕዝብም ወያኔ መሆናቸውን እንዲያውቅባቸው አይፈልጉም። የዘመኑ የልማት ባለሃብትና የነጻ ገብያ “ኢንቬስተሮች“ ናቸውና በእንደዚህ ዓይነት ስብሰባ እንዲገኙ ደግሞ በወያኔ የፍራንክፈርት ቆንስላ ስለሚገደዱ ስብሰባ ከመምጣት ውጭ ሌላ አማራጭ የላቸውም። ድብብቆሽ ተጫውተው ይመለሳሉ። እንግዲህ እንዲህና እንዲያ እያለ ነው በፍራንክፈርት የብአዴንና የኦህደድ ኢንቬስተሮች ተግባር ። ከዚህ ውጭ በይፋ በዓል ለማክበር የሚያስችል የሞራል ጥንካሬ ከቶ የላቸውም ።
እነዚህ ለጥቅም ራሳቸውን የሸጡ ኢንቬስተሮች ከየትናውም ጎራ ይምጡ ቁጥራቸው ግን ጥቂት ነው። የሚበዛው ትግራይ ነጻ አውጪ አባላት ቁጥር ነው። ሰለሆነም ከላይ ከፎቶው እንደምንመለከተው የትሓህት(የትግራይ ነጻ አውጪ) አባላት የተሰብሳቢውን ቁጥር እንዲበዛ ወያኔ ስብሰባ በተጠራበት ሥፍራ ሁሉ በነቂስ ወጥተው ይገኛሉ። ሕውሀትን እስከጠቀመ ድረስ የወያኔ ደጋፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆችን አንዴ አማራ ሆነው፣ ሌላ ጊዜ ኦሮሞ፣ ሲያሻቸው የደቡብ ህዝብ እየሆኑ በመገለባበጥ ለፕሮፖጋንዳ ሥራ በስፋት ያገለግላሉ። የማያውቃቸው እውነት ይመስለዋል። የሚያውቃቸው ደግሞ ስቆም ታዝቦም ያልፋል።
እነዚህ ተሰብሳቢዎች “በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ” ስም ያገኙትን የግል ጥቅም እንደ ሃገር ልማት የሚቆጠሩ ናቸው። ለግል ጥቅማቸው ሲሉ በሌላው ህይወት ላይ ተረማምደው የሚሄዱ፣ ሃገር እያፈረሱ የሚነግዱ፣ በዘር ክፍፍል የሚሞዳሞዱ፣ በመጭው ትውልድ ዕጣ ፈንታ ላይ የሚቀልዱ ናቸው። በልካቸው በተሰራ የድሎት መነጽር ሀገር ስለሚቃኙ፣ ህሊናቸው በንዋይ የታወረ፣ አእምሮአቸው በጥቅም የሰከረ፣ ከህዝብ ይልቅ ለአጉራሽ፣ ከማንነት ይልቅ ላፍራሽ ያደሩ ህሊና ቢሶች ናቸው ማለት ይቻላል።
ኦሮሞ የሚኮራ ታሪክ ያለው ታላቅ ህዝብ ነው። የሚዘበትበትም አይደል። ወላድ በድባብ ትግባ የኦሮሞ እናት በካር ነች። የኦሮሞ እንኳን የራሱን የሌላ ሰው ልጅ በጉዲፈቻ ማሳደግ ያውቅበታል። ኦሮሞ ልጅ እንደሌለው አስመስሎ ጽዋውን ሌላ እንዲዘክርለት ማድረግ ወይ ማስመሰል ወይም ንቀት ነው እሚሆነው። “ቅቤ አንጣሪዋ እያለች ጎመን ቀንጣሿን ምች መታት“ የማለት ያህል ካልሆነ በቀር፣ ኦሮሞ ስለ መብቱ መቆምና መከራከርም ያውቅበታል። ይህንን ወያኔ የሚዘነጋው ሆኖ አይደለም። ኦሮሞ ስለ ሀገሩ ኢትዮጵያም ዘብ የቆመ ህዝብ ነው። ቅድመ ታሪኩ ደግሞ ለዚህ ዋቢ ነው። ስለ መብቱም ሆነ ስለ ጥቅሙ፣ ስለ ሃዘኑም ሆነ ደስታው ዛሬ ሌላ አንጋችና ጋሻ ጃግሬ የሚያስፈልገው አይመስለኝም። በራሱ እራሱን ሁኖ በኢትዮጵያዊነት ልእልና እንደወትሮው ሲታይ በእጅጉ የላቀ ውበት አለውና ተለጣፊ አያሻውም።
ያም ሆነ ይህ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ከደሃው ተነጥቆ በተሰጣቸው መሬት ላይ ቤት እየሰሩ የሚንደላቀቁ ልማታዊ ባለሀብቶች በሚያደርጉት ብረት ለበስ የደባ ፕሮፖጋንዳ መወናበድ ያለበት አይመስለኝም። ሃገራችንን በክልል ከፋፍሎ ሕዝቡን ፍትህና የዴሞክራሲ መብት ያሳጣው ወያኔ ዛሬ እኛን በውጭ ያለውን ዜጎች በተለጣፊ ድርጅቱ የመከፋፈል ስልቱ ሊለያየን ከቶ አይገባም። በነጻው የአውሮፓ ምድር እየኖርን፣ ከፖርቱጋል እስከ ስዊዲን ያለቁጥጥር እየተጓዝን፣ ሌት ከቀን በነፃነት ወጥተንና ሰርተን እየገባንና እየኖርን በጠበበ የክልል ፖለቲካ ወያኔ ሊከፋፍል መሞከሩ ሞኝነት አለያም እብደት ይመስለኛል። ወያኔ ያደገው፣ የተቃኘው በዘር ፖለቲካ ነውና ከዚያ ከቶ ሊወጣ አይችልም ። ይልቁንስ እኛ ግን ዛሬም ነገም እራሳችንን ሆነን ልንገኝ ይገባል። ከትልቅ ሰውነት አስተሳሰብ ወደ ትልቅ ተቋምነት፣ በማንነት መለዩዎች ወደ ጋርዮሽ መለዮዎች፣ ከቁጥጥር ሥርዓት ወደ መብታዊ የብዙሃን ስርዓት የሚያሸጋግሩን ጠቃሚ ሥራዎች መስራቱ ለሃገርም ለራስም የሚበጅ የዜግነት ሃላፊነት ነው።
beljig.ali@gmail.com
ስለ ሃገራችን የሚያስቡ ሁሉ በሰላም ይሰንብቱ !
ፍራንክፈርት 28/03/15

ለዓመታት የስለላ ሠራተኛና የአዲስ አበባ ቀጠና ኦፊሰር የነበረች የህወሃት አባል መክዳቷ ታወቀ።

በኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት መዋቅር ውስጥ ተመድበው የሚያገለግሉ የሰለላ ሰራተኞች በጽናት መስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተሰማ።
የጎልጉል ታማኝ የዜና ምንጮች አንዳሉት ድርጅቷ ህወሃትንና ታላቁን የአፈና ተቋም የስለላ ኦፊሰር የነበረችው የመክዳት ውጥኗ እውን የሆነላት ከስድስት ዓመት በኋላ ነው። በተደጋጋሚ ጊዚያት የዲፕሎማት ቪዛ እንዲሰጣት ፓስፖርቷን ለኢሚግሬሽን ብትልክም ያልተሳካላት ይህቺ የስለላ ኦፊሰር፣ በመጨረሻ የተሳካላት ስፔን አገር ለስለላ ስልጠና በማግኘቷ ነው።
አዲስ አበባ የሚገኙ ባልደረቦቿ “እርሷ ዕድለኛ ናት” በማለት ለጎልጉል ዘጋቢ እንዳሳበቁት፣ ኦፊሰሯ ስፔን አገር ከባልደረቦቿ ተለይታ ያመራችው ወደ አሜሪካ ነው። እዚያም እንደ ደረሰች እንደማትመለስ አረጋግጣለች። የትግራይ ክፍለ ሃገር ተወላጅና ታማኝ የህወሃት አባል የነበረችው የስለላ ሰራተኛ፣ ከቀበሌ ተነስታ ለከፍተኛ ሃላፊነት የበቃች ታማኝ ነበረች።
በብሔራዊ የደህንነት መዋቅር ውስጥ መሰላቸት፣ አለመተማመን፣ ጫና እንዲሁም ነጻ ሰዎች ሳይቀሩ የሚደረግባቸው ክትትል ጤና የነሳቸው ተበራክተዋል። በተለይም የህወሃት ያልተማሩ ነባር /አንጋፋ ባለሥልጣናት/ ታጋዮች የሚሰጡት ቅጥ ያጣ መመሪያና ወሬ ለቃሚዎቸ ከየመንደሩ ለብር እያሉ የሚያቀረቡት የሰላማዊሰዎችን ህይወት የሚያናጋ መርጃ ዕረፍት እንደነሳቸው የዜናው ምንጮች አመልክተዋል።
“በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃ ተቀምጠው የሚያገለገሉ ባብዛኛው ደስተኛ አለመሆናቸው በገሃድ ስለሚታወቅና የመውጫው ቀዳዳ ስለተዘጋ” በሁሉም አቅጣጫ መሹለኪያ ፈላጊውና በሰላም መኖር የሚመኘው ክፍል እንደሚያይል ያመለከቱተ ዜና አቀባዮች “የኢህአዴግ ዙሪያ መለሱ ቆሽሾዋል፤ የእርስ በርስ መተማመኑም ኮስሷል” ብለዋል። በማያያዝም በርካታ አመራሮች አገር ለቅቀው መውጣት እንደማይችሉ አስታውቀዋል።ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (ሚያዚያ 2፤2006ዓም/April 10,2014) “ከአገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣናት በጭንቀት ውስጥ ናቸው፤ “አሁን ያለው ኢህአዴግ ላዩ በቀለም ቀቢ የተዋበ ይመስላል”” በሚል ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ለአንባቢያን እንዲረዳ ከዚህ በታች በድጋሚ አትመነዋል፡፡ ኢህአዴግ በሙስና ስም የ”ማጥራት ዘመቻ” ማካሄዱን ተከትሎ የተከሰተው አለመተማመንና እርስ በርስ በጥርጥር የመተያየት ችግር ካድሬውን ማስጨነቁ ተጠቆመ።
ኢህአዴግን ለመሰናበት የሚፈልጉ በርካታ ካድሬዎች “ለምን” በሚል የሚቀርብላቸውን ጥያቄ በመፍራት የግድ ፓርቲውን መስለው እንደሚኖሩ ተገለጸ።
የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ቀደም ሲል ኢህአዴግን ተሰናብተው የወጡና በተለያዩ የውጪ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው በማገልገል ላይ ካሉ ያገኘውን መረጃ በመጥቀስ እንደዘገበው፣ የቀድሞ የትግል ጓደኞቻቸው “በደህና ጊዜ ተገላገልክ” በሚል በፓርቲው ውስጥ ችግር ስለመኖሩ እየነገሯቸው ነው። አብዛኞቹ ኢህአዴግን ተለይተው በሰላም ስለመኖር እንደሚያስቡ ነው የተሰማው።
የቤተሰቦቻቸው የወደፊት እድልና የነሱ በፍርሃትና በጭንቀት መኖር አሳዛኝ እንደሆነ የነገሩት የቀድሞ የኢህአዴግ ሰዎች “አሁን ያለው ኢህአዴግ በቀለም ቀቢ የተዋበ ይመስላል” በማለት አንድ በሚኒስትር ዲኤታ ማዕረግ እያገለገለ ያለ የቀድሞ ጓደኛቸው እንደነገራቸው ገልጸዋል።
ለስራ እንኳን ካገር መውጣት የማይችሉ ባለስልጣኖች እንዳሉ ዘጋቢያችን አመልክቷል። በተቀመጡበት ሃላፊነት ወደ ውጪ የሚያስኬድ አጋጣሚ ሲኖር የሚከለከሉ እንዳሉም ያገኛቸውን መረጃዎች ጠቅሶ ዘግቧል። ለሃላፊዎቹ ደህንነት ሲባል የሚሰሩበትን ተቋምና ስም መናገር እንደማይችሉ በመጥቀስ መረጃውን የሰጡት ክፍሎች “ባለስልጣኖቹ በመካከላቸው እርስ በርስ መተማማን ስለማይችሉ ችግራቸውን መወያየት እንኳን አይችሉም” ብለዋል፡፡“በጣም የሚቀርቡኝ ጓደኞቼ ገንዘብ ወደ ውጪ እንድወስድላቸው እስከመጠየቅ ደርሰዋል” ሲሉ የገለጹት የቀድሞ የኢህአዴግ ባለስልጣን፣ ፓርቲው በሙስና ስም ያካሄደው የሽግግር ወቅት የማጥራት ርምጃ የፈጠረው ስሜት አሁን ድረስ እንዳለ ጠቁመዋል።
ሰሞኑንን ወደ አሜሪካ ያቀኑ የቀድሞ የኢህአዴግ ሰው በማግኘት ተመሳሳይ መረጃ ያሰባሰበው ዘጋቢያችን “ኢህአዴግ በከፍተኛ የመበስበስ አደጋ ውስጥ ይገኛል። በዚህም የተነሳ ካድሬው ተዥጎርጉሯል” ሲል ሪፖርት አድርጓል። ኢህአዴግ በውስጥ ያለበትን ችግር ለማድበስበስ የአባይ ግድብ ላይ ትኩረት በመስጠት “የንቅናቄ ሃይል” በማስፋፋት ላይ እንደሆነም ጠቁሟል።
ድፍን ህዝብ የአባይ ግድብን አስመልክቶ ያለው ስሜት በበጎ መልኩ የሚታይ በመሆኑ ኢህአዴግ ይህንኑ የህዝብ ስሜት ለቅስቀሳና ለበሽታው መደበቂያ ለማድረግ እየተጠቀመበት እንደሆነ ተጠቁሟል። የህጻናት ፕሮግራሞች ሳይቀሩ አባይ ላይ ያነጣጠሩ ቅስቀሳዎች እያስተላለፉ መሆናቸውን ያመለከቱት ሰው፣ “ስለ አባይ ግድብ የሚባለውና የሚሰራው ፕሮግራም ችግር የለውም። በአግባቡ ቢሰራበት ብሔራዊ ስሜት ሊገነባበትም በተቻለ ነበር። ይሁን እንጂ ዓለማው የችግር ማለባበሻ እንዲሆን መደረጉ ነው” ብለዋል።
“መለስ ኢትዮጵያን ቢወድ ኖሮ ከባድመ ጦርነት በኋላ የፈረሰውን ብሔራዊ አንድነትና መግባባት መልሶ መትከል ይቻል ነበር” በማለት የተናገሩት እኚሁ ሰው “በወቅቱ ይህንን ሃሳብ ያነሱ ሰዎች ነበሩ” ሲሉ ቁጭታቸውን ይሰነዝራሉ። በማያያዝም ኢህአዴግ የአባይን ግድብ ተንተርሶ ብሔራዊ አንድነት የሚገነባበት፣ መቀራረብና በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር ብሔራዊ መግባባት የሚደረስበት፣ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ መሰረት የሚጣልበት ቢያደርገው እውነተኛው የኢትዮጵያ ህዳሴ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝን በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ለመተካት ህዋሀቶች የሚያደርጉት ሽርጉድ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ሪፖርት መቅረቡ ተሰምቷል። ይኽው ሪፖርት የቀረበላቸው ክፍሎች ቀደም ሲል እንዳደረጉት የህወሃትን ከፍተኛ አመራሮች በማነጋገር ስህተት እንዳይሰሩ እየወተወቱ ነው።
source:ጎልጉል

ኢትዮጵያዊቷ የISIS ሙሽራ እና “ጽንፈኛ” ሆነው የተገኙት አባቷ

አስደንጋጭ ዜና ነው። ራሱን የእስልምና ግዛት ISIS ብሎ የሚጠራው አክራሪ እና ጭራቂዊ ቡድንን ለመቀላቀል ከሁለት ጓደኞቿ ጋ ከለንደን ወደ ሶሪያ የሄደችው የ15 ዓመቷ አሚራ አባት የሆኑት አቶ አባስ ሁሴን Innocence of Muslims የሚለው ፊልም እስልምና እምነትን አዋርዷል በማለት በለንደን አሜሪካ ኤምባሲ ፊት-ለ-ፊት በተደረገው ሰልፍ ላይ አሜሪካ ትቃጠል፣ ሙስሊም ክሩሴድን ያጠፋል አሜሪካንና እንግሊዝን ጨምሮ…. የሚሉ መፈክሮች ጀርባ በስሜት መፈክር ሲያስተጋቡ የሚታዩበት ቪዲዮ ይፋ ሆኗል።
መፈክር ብቻ ሳይሆን የአሜሪካንና እስራኤል ባንዲራ ሲቃጠል አቶ አባስ አጃቢ ናቸው።
ልጃቸው ወደ ሶርያ ለመግባት በቱርክ በኩል ስታቋርጥ በካሜራ እይታ ውስጥ ከገባችና ሁኔታው በእንግሊዝ መንግስት በገሊ ከተነገረ በኋላ አቶ አባስ የእንግሊዝን ፖሊስ ተጠያቂ ማድረጋቸው ይታወሳል። በወቅቱ በብሪታኒያ ፖሊስ ማዕከል ስኮትላንድ ያርድ ቃለምልልስ ሲሰጡ ልጃቸው ስለአክራሪነት ፈጽሞ የምታውቅበት መንገድ ይፈጠራል ብለው እንደማያምኑ ሳግ እየተናነቃቸው ሲናገሩ ሰምተናል።
ነገር ግን አሁን ቀስቱ ወድሳቸው ዞሯል። ከ3 ዓመታት (2012) በፊት የዛሬን ጦስ ሳያስቡት እንግሊዝን ባስበረገገው የጽንፈኞች ሰልፍ ላይ ተዋናይ መሆናቸው በቀላሉ የማይታይ፣ ለልጃቸው የISIS ነፍሰ ገዳይ ለመሞሸር ድንበር ማቋረጧ በቀጥታ ተጠያቂ መሆናቸው አይቀሬ ነው። አሜሪካንም ሆነች እንግሊዝ ጉዳዩን በቀላሉ አያዩትም። ለዚህ ምክንያቴ አቶ አባስ:–
1. የአሜሪካኑን 911 እና የእንግሊዙን 7 July 2005 የሽብርተኞች ጥቃትን በአደባባይ የደገፈው ብሪታኒያዊው አካራሪ፣ አክቲቪስትና የሙስሊም ማህበረሰብ ጠበቃዎች ሊቀመንበር አንጀም ቾዳሪ የመራው ሰልፍ ላይ መገኘታቸው
2. በዛ ሰልፍ ላይ ከታደሙት መካከል Michael Adebowale የተባለ ወጣት ከዚያ የጽንፈኞች ሰልፍ አንድ ዓመት በኋላ የብሪታኒያን ወታደር Lee Rigbyን በደቡብ ምሥራቅ ለንደን በጠራራ ፀሐይ በመኪና ገጭቶ በስለት ወጋግቶ የገደለ መሆኑ
ልጃቸውን ከማጣታቸው ጋር ተደማምሮ የአቶ አባስን ቀጣይ ሕይወት መሪር ያደርገዋል።
ሆኖም ሰው የዘራውን ማጨዱ አይቀርም ቢባልም በልጃቸው ማንነት ላይ የነበራቸውን ሚና እርግጠኛ ሆኖ መናገር አዳጋች ነው።
ሆኔታው ግን ለጅምላ ፈራጆች ትልቅ ሲሳይ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴን በጎሪጥ ለሚያዩ ሰዎች፣ ህወሓት የሚሰራው ፕሮፓጋንዳ ለኀይማኖታቸው፣ ለብሔራቸው… በሚመች መልኩ በትሪ ጠረጴዛቸው ላይ ቁጭ ሲቀርብ ተስገብግበው ለሚሻሙ ሰዎች ለቁንጽል መረጃቸውና ድምዳሜያቸው ግዙፍ ርዕስ አግኝተዋል።
ድምጻችን ይሰማ በዚህ ውዥንብር ሳይደናገር ላለፉት 3 ዓመታት ያሳየንን ሰላማዊ እና ስልጡን ተቃውሞ እንደሚቀጥል ቅንጣት ታህል ጥርጥር የለኝም።
Kassa Hun Yilma

Dienstag, 24. März 2015

ኑሮ በአዲስ አበባ (ነፃነት ዘለቀ – ከአዲስ አበባ)

ትናንት ሲያቀብጠኝ ከአንድ ጓደኛየ ሞባይል እነዚያ አይሲስ የሚባሉ ጉግማንጉጎች እነዚያን 21 ክርስቲያን የግብፅ ዜጎች በሊቢያ አንድ የባሕር ዳርቻ ላይ አንገታቸውን ሲቀሉ የሚያሣይ ቪዲዮ አየሁ – እስከመጨረሻው መዝለቅ አልቻልኩምና ግን ዋናው ባራኪ በግራ እጁ የያዘውን ጩቤ ወደ እኛ ወደተመልካቾቹ ዘርግቶ እያስፈራራ ሲዝት አጠፋሁት፡፡
addis-ababa-realethiopia-141
የሰው ልጅ በሰው ልጅ ላይ እስከዚህ መጨከኑ የሚያመላክተን ዋና ቁም ነገር የዚች ምድር ሰዎች የደረስንበት አጠቃላይ መንፈሣዊና ኅሊናዊ ኪሣራ ሊቀለበስ ወደማይችል ከፍተኛ የመጨረሻ ደረጃ መድረሱን ነው፡፡ ለምግብነት የተፈቀዱልንን እንስሳት እንኳን ስናርድ የሚዘገንነንና በዚህም ምክንያት የማናርድ ብዙ እንስፍስፍ ሰዎች አለን፡፡ ሰውን የሚያህል ክቡር ፍጡር ሊያውም በሚከተለው ሃይማኖት ምክንያት ብቻ በስለት አንገቱን ቀንጥሰው ጀርባው ላይ ሲያስቀምጡ ሊሰቀጥጣቸው ይቅርና በደስታ የሚፈነጥዙ “ሰዎች”ን በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ስናይ በሰዎች ተፈጥሮ መለያየት እጅግ እንገረማለን፡፡
“A Message Signed with Blood, to the Nation of the Cross” ይላል የቪዲዮው መግቢያ፡፡ አስፈሪ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በያዙት የመስፋፋት ሂደት ከቀጠሉ ሌሎቻችንም ይህ አስቀያሚ ዕጣ የሚቀርልን አይመስለኝም፡፡ ነገሩ “የፋሲካው በግ በገናው በግ ይስቃል” እንዳይሆን ያሰጋል – እየሆነም ነው እንጂ፤ ከመካከለኛው ምሥራቅ የተነሣ እሳት አፍሪካ ጫፍ ሊቢያና የመን ሲደርስ አያድርስ ብሎ ከመጸለይ ውጪ እኛስ ምን ዋስትና አለን? ይህን ቪዲዮ ከተመለከትኩ በኋላ ለረጂም ጊዜ ሥራየን በአግባቡ መሥራት አልቻልኩም፡፡ ሰው ሆኖ የመፈጠር ዕዳ የቀሰቀሰብኝ የተስፋ መቁረጥ ስሜት መላ ሰውነቴን ወረረው – በአካልም፣ በመንፈስም፣ በኅሊናም እየኮሰመንኩ ስሄድ በምናቤ ይታየኝ ጀመር፡፡ አለመፈጠሬን የመረጥኩበት አንዱና ትልቁ አጋጣሚ ይህን ዘግናኝ ቪዲዮ በከፊልም ቢሆን ያየሁ ጊዜ ነው፡፡
ይህ በአስቀያሚነቱ ወደር የማይገኝለት ዓለም አቀፍ ክስተት በረድ እያለልኝ ሲመጣ ግን የሀገራችን አይሲስ ነጋዴዎች ታወሱኝና ስለነሱ አብዝቼ መጨነቅን ያዝኩ፤ ሁለቱ ተመሳሰሉብኝ፡፡ ደረጃውና ዓይነቱ ይለያይ እንጂ ጭካኔ ሁሉ መጠሪያውም ሆነ ጎራው ያው ጭካኔ ነው፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያጵያውያን ኢይሲሶች የምላቸው በወያኔ የተፈጠሩ የዘመናችን ኅሊና ቢስ ነጋዴዎችንና ኑሯችንን ያመሰቃቀሉትን የሙስና አበጋዞችን ነው፡፡ ከወያኔ ቀጥለው የሀገራችንን የቀብር ሥነ ሥርዓት እያፋጠኑ የሚገኙት እነዚህ የቀን ጅቦች ናቸው፡፡
ወያኔ የዘራው ትልቁና መሠረታዊው ችግር የሀገር ብሔራዊ ስሜትን ማጥፋቱ ነው፡፡ ከዚህ በተያያዘም ሰብዓዊነትን ከሀገር አጥፍቷል፡፡ በምትኩ የተስፋፋው ዘረኝነት በወንዝ ልጅነትና በጎጥ፣ በቋንቋና በቤተሰብ መሳሳብ የጥቅም ትስስርን አንግሦ ጥቂቶች በሀብትና በሥልጣን ሽቅብ ሲመነደጉ አብዛኛው ሕዝብ እንጦርጦስ እየወረደ ነው፡፡ ወያኔ ዘረኝነትን በማስፋፋት ብቻ አልተወሰነም፡፡ ለሰው ልጅ ማኅበራዊ እንስሳነት እንደ አያያዥ ስሚንቶ ይቆጠሩ የነበሩ ሃይማኖትን፣ ባህልን፣ የሞራል ዕሤቶችን፣ መተሳሰብን፣ መፈቃቀርን፣ መቻቻልን፣ አብሮ መብላት መጠጣትን፣ … በጥቅሉ አንድን ሰው ሰው ሊያስብሉት የሚችሉ ሰብኣዊና ተፈጥሯዊ ክሮችን በጣጥሶ አንድያውን ሁላችንንም እንደራሱ ዐውሬ እያደረገን ነው፡፡ ከዚህ በሀገር ደረጃ ከታወጀብን የጥፋት ውርጅብኝ ለማምለጥ የምንውተረተር ዜጎች በጣም ጥቂቶች ነን፡፡ ዛሬ የብዙ ሰው መፈክር “ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ” ሆኗል፡፡ አንድ ማስታወቂያ ነበር – “መጀመሪያ ራስህን አድን ለጫማው በኋላ ይታሰብበታል” የሚል፡፡ እኛም “‹ሀ› ራስህን አድን” በሚለው የራስ ወዳድነት መርህ እየተመራን አንዳችን አንዳችንን በልተን ልንጨረስ የቀረን ጊዜ ኢምንት ነው፡፡ በጩቤ አለመተራረድ ብቻውን ከአይሲስነት ተፈጥሮ ነፃ አያወጣም፡፡ “እሳት ካየው ምን ለየው” ነውና በምንም ይሁን በምን የዘመናችን የጭካኔ መገለጫ አይሲስ ሆኗልና ነጋዴዎቻችንና ጃዝ ባዮቻቸውም የንግዱ ዘርፍ አይሲስ ናቸው – ሥውር አራጆች፡፡
ኑሮ በአዲስ አበባ ምን ይመስላል? ሰዎች ለምንና በምን ብልሃት፣ እንዴትስ ብለው በሀብት ይከብራሉ? ብዙኃኑስ ለምን በሀብት ይደኸያሉ? የሀገራችን የሀብት ክፍፍል ምን ይመስላል?አብሮ መኖር ሲቻል መጠፋፋትን ምን አመጣው?
በአሁኑ ወቅት “ሀገራችን ወዴት እያመራች ነው?” ብሎ መጠየቅ ሞኝነት ይመስለኛል፡፡ ይልቁንስ “በጉዞዋ የት ደርሳለች? በብርሃን ፍጥነት እያስነካችው ያለችውን ጉዞ ጨርሳ ወያኔና ታሪካዊ ጠላቶቿ ወዳቀዱላት የመጨረሻ ግብ ለመድረስ ምን ያህል ጊዜ ይቀራታል?” ብሎ መጠየቅ ይመስለኛል አግባብ የሚሆነው፡፡ እንጂ ዕድሜ ለወያኔ ካሣለፍነው የሃያ አራት ዓመታት የጥፋት ጉዞ በመነሣት ወዴት እያመራን እንደሆነ ቁልጭ ብሎ የሚታይ ጉልህ ክስተት ነው፡፡
በአዲስ አበባ ስል በመላዋ ኢትዮጵያ እንደማለትም ቢቆጠርልኝ ደስ ይለኛል፡፡ ለውጥ ሊኖር ቢችልም እንኳን ያን ያህል የጎላ አይደለምና፡፡ እናም በሀገራችን ኑሮ በአሁኑ ወቅት እጅግ የሚሰቀጥጥ መሆኑን በመጠኑ እንመልከት፡፡
በደመወዝ ብቻ መኖር ከቀረ ብዙ ጊዜ አለፈን፡፡ ደመወዝ ስልህ ደግሞ ይግባህ – የመንግሥትንና በሲፒኤ ደንብ የሚተዳደሩትን ማለቴ ነው፡፡ ትላልቅ ደመወዞችን አይመለከትም፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከፈላቸው አሉና እነሱ የኑሮ ግርፋና ሰቆቃው አይነካቸውም፡፡
በአሁኑ ወቅት የዕቃዎች ዋጋ አይቀመስም፡፡ ሠራተኞች ከወር ወር መድረስ ስለማይችሉ ብዙዎች በተራድዖና በልመና እንዲኖሩ ተገደዋል፡፡ ዕቃዎች ስልህ የመብል ውጤቶችን ለማለት ነው፡፡ አንድ የመንግሥት ወይም የግል ድርጅት ተራ ሠራተኛ በሚያገኘው ደመወዝ ሌላውንና ለዘመኑ እንደቅንጦት የሚቆጠረውን ቤት መሥራትንና ማሳደስን ተውትና የምግብ ፍጆታውን እንኳን መሸፈን አይችልም – ሌላ የጎን ገቢ ካልተጨመረበት፡፡ “ሽምብራ ቆርጥሜ የሠራሁት ቤት” ይባል የነበረው ምሳሌያዊ አነጋገር አሁን የለም – ሽምብራም ከጤፍ በልጦ ተወዷል፡፡ በዚያ ላይ ሽምብራም ቆርጥም ባቄላ ከደመወዝህ ቤሣቤስቲን ተርፎህ ለክፉ ቀን አታስቀምትም፡፡ ሲጀመር ኑሮህ በብድርና በበዕዳ የተወጠረ እንጂ ከሽሮና ከጎመን ያለፈ አታስብም – ለዚህም ከበቃህ ታድለሃል፡፡ ዱሮ በአሥርና በአሥራ አምስት ብር ይገዛ የነበረው ሳልቫጅ ሸሚዝ ራሱ ዛሬ ከብር 130 በላይ ነው – በዚህ ዋጋ በቀደምለት እኔ ራሴ ስለገዛሁ ኅያው ምሥክር ነኝ – ለዚህ መብቃቴም ያስጨበጭብልኛልና እባካችሁን አጨብጭቡልኝ፤ የቢሮ ሠራተኛ – በሙስና ያልተዘፈቀ ማለቴ ነው – ሣልቫጅ ከመግዛት እንኳን አቅም ካነሰው ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ ዛሬ ሳልቫጅ ራሱ ለመለስተኛ ሀብታሞች መዘነጫ ሆኗል፡፡ የኔ ቢጤ ሠራተኛ አዲስ ሸሚዝና ጫማ ለመግዛት ዕቁብ መግባት ይኖርበታል፡፡ በሌሎች ያደጉ ሀገራት በአፍሪካም ጭምር አንድ እኔን መሰል ለ20 እና ለ30 ዓመታት ሀገሩን ያገለገለ ባለ ሁለተኛ ዲግሪ ችግሩ ቤትና መኪና ሣይሆን ሌላ ነው፡፡ እኛ ግን ምን ቀምሰን እንደምናድር የምንጨነቅ የነጋዴና የወሮበላ መንግሥት የግዳይ ሰለባዎች ነን፡፡ ቆም ብለው ሲያስቡት ያሣዝናል፡፡ ይህን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ ታዲያ ብዙ ዜጋ አግባብ ባልሆነ መንገድ ገንዘብ ለማግኘት አቅሉን ስቶ ሲራወጥ ታዩታላችሁ፡፡ ድህነት መጥፎ ነው፡፡ ድህነት ከሃይማኖትና ከጨዋ ባህል ያወጣል፡፡ ድህነት ዐውሬ ያደርጋል፡፡ ድህነት ያባልጋል፡፡
ነጋዴው እሳት ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ ነጋዴ ዐይንም፣ ጆሮም፣ ልቦናም የለውም፡፡ የለዬለት ዕውር ነው፤ የለየለት ደንቆሮ ነው፡፡ የንግድ ጽንሰ ሃሳብም የለውም፤ ምክንያቱም ወደ ንግድ የሚገባው የፊደል ዘሮች አልገባው እያሉ ሲያስቸግሩት እንጂ በትምህርትና በልምድ ዳብሮ አይደለም፡፡ ብዙው ነጋዴ በአቋራጭ መክበርን እንጂ በህጉ መሠረትና የሕዝቡን ኢኮኖሚያዊ አቅም ባገናዘበ ሁኔታ አይደለም፡፡ የሀገሪቱም ሕግ ሕግ-አልባነት በመሆኑ ማንኛውም ኅሊናቢስ ወንበዴ ወደሀብቱ የሚያደርገው ጉዞ የተቃና ነው፡፡ የመንግሥት ተብዬው ባለሥልጣናትም ከማይማን ነጋዴዎች ጋር እየተመሣጠሩ ሕዝቡን ባልተወለደ አንጀት ይገርፉታል፡፡ ማይም ባለሥልጣናትና ማይም ነጋዴዎች በእከክልኝ ልከክልህ የጥቅም ትስስር ሀገሪቷንና ሕዝቧን ወደ ገደል እየከተቷቸው ነው፡፡ አንድም ሃይ ባይ ሳይኖር ኢትዮጵያን የመሰለች የድንቅ ታሪክ ባለቤት እየጠፋች ነው፡፡ ማን ይድረስላት?
ዱሮ ስንጥቅ ትርፍ ሲባል እንሰማ ነበር፡፡ “እገሌ ስንጥቅ ትርፍ አተረፈ” ይባል ነበር፡፡ ዛሬ ግን እንደዚያ ብሎ ነገር የለም፡፡ ስንጥቅ ማለት እንግዲህ ግማሽ በግማሽ ለማለት ይመስለኛል – ለምሳሌ መቶ ብር የተገዛን ዕቃ 150 ወይም ግፋ ቢል 200 ብር የመሸጥ ያህል፡፡ አሁን ግን መቶ ብር የተገዛን ዕቃ ጊዜ እየጠበቁና ሆን ብለው እያስወደዱ ከአምስትና ስድስት ሺህ ብር በላይ ካልሸጡ የነገዱ የማይመስላቸው አይሲሶች ተፈጥረዋል፡፡ ስለዚህም አንድ ሰው ንግድ በጀመረ በጥቂት ሣምንታትና ወራት ውስጥ አንቱ የተባለ ዲታ ይሆንና መኪና እንደሸሚዝ ሲለዋውጥ ታየዋለህ፤ በዚያ ላይ ወያኔያዊ የደምና የአጥንት ንክኪ ካለው ሣምንት ቀርቶ ደቂቃዎችም ሳይፈጅበት ቀጭን ጌታ ይሆናል – ትምህርት ዕርሙ በሆነበት ድባብ ውስጥ ለሚኖር አንድ ማይም ዘረኛ ደግሞ ይህ ዓይነቱ በሀብት የመወንጨፍ ዕድል ከባድ አይደለም፡፡ ዋናው ነገር አእምሮን የማሳመን ጉዳይ ነው፡፡ የሃይማኖትና የግብረገብ ትምህርት የሌለው፣ የይሉኝታና የሀፍረት ስሜት ጨርሶ የሌለው፣ ከአንዲት ትንሽ ጎጥ በዘለለ ማሰብ የማይችል “ሰው” አጭበርብሮና አታልሎ ብቻም ሣይን ገድሎና አሥሮም ቢሆን ቢከብር የሚጠይቀው ኅሊና ወይም ምድራዊ ሕግ የለም፡፡ ሁሉም እርሱን ለመርዳት የቆመ ነውና፡፡ ሰው ደግሞ በተፈጥሮው ከኅሊናው ጋር ከተቆራረጠ የመጨረሻው ዐውሬ ነው የሚሆነው፡፡ በሁሉም መንገዶች ተጉዞ ወደሚፈልገው ማማ መውጣት ነው ጥረቱ፡፡
ትናንት ሰላጣ አማረኝ፡፡ ብዙውን ጊዜ ጥቃቅን የምግብ ፍጆታዎችን ከማንጠግቦሽ በተጓዳኝ እኔም እገዛለሁና ወደጉሊት ወጣ አልኩ፡፡ ገበያው በአንጻራዊ አነጋር ከቀደሙት የጾም ወራት አሁን ደህና ነበር ማለት እችላለሁ – በተለይ በአንዳንድ ዕቃዎች፡፡ ቀይ ሽንኩርት በኪሎ 16 ብር፣ አንዲት የጠወለገች ሙትቻ ሎሚ በአንድ ብር ከሃምሣ፣ ቲማቲም በጣም ቀነሰ ተብሎ ኪሎውን በ8 ብር፣ ቃሪያ (በጣም ጦፏል!) ግማሽ ኪሎ በ23 ብር፣ ሃቱም የተባለውን አንድ ሊትር ዘይት 78 ብር፣ አንዲት እግር ሰላጣ በ8 ብር ገዝቼ ፀጉሬን እየነጨሁ ወደቤቴ ተመለስኩ፡፡ ሰላጣ ለመብላት ስንት እንዳወጣሁ እናንተው አስሉት – ዘይቱ እርግጥ ነው ትንሽ ጊዜ ይቆያል፡፡ ይህን ኑሮ የትኛው የመንግሥት ሠራተኛ ችሎ ይኖራል? ሥጋንና ወተትንማ ጭራሽ አታስቡት፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በሉካንዳ ቤት ስናልፍ የተሰቀለን ሥጋ በሱቲ ጨርቅ እየሸፈኑ ገልጠው ለማሳየት ብቻ ሳያስከፍሉን የሚቀሩ አይመስሉኝም፡፡ ልብ አድርጉ – እኔ ባለደህና ደሞዝተኛ ተብዬው ለልጆቼ ብርቱካንና ሙዝ አንጠልጥዬ መግባት ካቆምኩ ዓመታት አልፈዋል – እንዳልዋሽ እጅግ አልፎ አልፎ በወረት ካልሆነ በስተቀር የምነግራችሁ እውነቴን ነው፡፡ አንዲት ኪሎ ሙዝ 14 ወይ 15 ብር ፣ አንድ ኪሎ ብርቱካን ከብር 22 በላይ ገዝቼ እንዴት እችላለሁ? ደግሞስ አንድና ሁለት ኪሎ መች ይበቃንና ወስፋት ላጩህ? ለመሆኑ ስንቱ ቤተሰብ ነው ሥጋና ወተትን የመሰሉ አልሚ ምግቦችን በቅጡ የሚመገበው? ብዙው ቤተሰብ ሥጋን የሚያውቀው ሃሊዮ ኮሜት በሰባ ስድስት ዓመት አንዴ እንደምትታየው ሁሉ በዓመት ሁለቴና ሦስቴ ብቅ በሚሉ ፋሲካን የመሰሉ ዐውዳመቶች ነው፡፡ ሞተናል እኮ፡፡ ገድለውናል እኮ፡፡ እንዳሰቡት ሆነንላቸዋል እኮ፡፡ ዕቅዳቸው እኛን ማጀታችን ውስጥ ወሽቀው ስለምንቀምሰውና ስለምንልሰው እንድንጨነቅ ማድረግ አልነበረም? ታዲያስ! እናሳ አልተሣካላቸውም? አለመረገማችንን የማናምን ከዚህም ባለፈ እኛ ኢትዮጵያውያን ዕድለኞች መሆናችንን አዘውትረን የምንናገር ብዙዎች ልንሆን እንችላለን – ነገር ግን ሆዱን እንኳን መቻል በሚያቅተው ማኅበረሰብ መካከል መገኘት ከመረገሞችም በላይ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡ የሰው ልጅ በሥልጣኔ የትና የት ደርሶ፣ “አውሮፓውያንና አሜሪካውያን ከማዕዳቸው ተርፎ የሚጣለው የዕለት ምግብ ለአፍሪካውያን የዚህን ያህል ጊዜ ቀለብ ይሆናል” እየተባለ ሲነገር ትንሽም የማይቆጫቸው መሪዎች ያሉን አሳዛኝ ሕዝቦች ነን – አፍሪካውያን በጠቅላላው፡፡ የኛ ደግሞ ከሁሉም በባሰ ቆሎም ባቅሙ አርሮብን፣ ልብሳችን በላያችን ላይ አልቆ፣ አጥንታችን አግጥጦ፣ … እንዲሁ ኑሮ ብለነው እንንጠራወዛለን፡፡ ሞታችንን በቁማችን ጨርሰን በትሽ በሽታ ህቅታችን ስትወጣ መቼም ወግ ነውና ሞቱ ተብለን ድንኳን ተጥሎ ይለቀስልናል፡፡
እርግጥ ነው የፊት ለፊት ስዕላችን አሁን ከምለው ለየት ያለ ሊመስልና እኔንም እንዳጋነንኩ ሊያስቆጥርብኝ ይችል ይሆናል፡፡ እኔ እያወራሁ ያለሁት እውነተኛውን በወያኔ ሚዲያ ግን የተሸፈነውን ሀገራዊ ማንነት ነው፡፡ የኔን ሕይወት፣ የወንድምና እህቶቼን ሕይወት፣ የአብዛኛውን ሕዝብ መሪር ኑሮ ነው እየተናገርኩ ያለሁት፡፡ እንጂ የተመቸው ጥቂት የማይባል ዜጋ መኖሩን አውቃለሁ፡፡ ግን ያም ምክንያት አለው፡፡ የተሻለ ደሞዝ ያላቸው፣ በሥራቸው ምክንያት እጅ መንሻ የሚያገኙ፣ ቤት የሚያከራዩ፣ ቤትና ዕቃ የሚሸጡና የሚለውጡ፣ ከዲያስፖራው ገንዘብ የሚላክላቸው(እኚህኞቹ ቀላል ቁጥር አይደለም ያላቸው)፣ መኖሪያ ቤታቸውን ወደአነስተኛ የንግድ ቤትነት ለውጠው እንደነገሩ የሚውተረተሩ፣ በስርቆት፣ በማጭበርበርና በሙስና ትልቅ ገቢ ያላቸው፣… ወገኖቻችን መሬት ላይ ከሚታየው ህንፃና መንገድ ጋር ተደማምረው እውነተኛውን ሀገራዊ ምስል ለጊዜው ሊደብቁት ቢሞክሩም እስከወዲያኛው ግን ሸፍነው ሊያቆዩት አይችሉም፡፡ ከነዚህ ከጠቃቀስኳቸው የጎን ገቢዎች የራቀው ተራው ገበሬ፣ መምህሩ፣ የመንግሥት (የቢሮ፣የጽዳት፣ የጉልበት፣ የጥበቃ…)ሠራተኛው፣ ተራው ወታደር፣ ከጉቦ ጋር ብዙም የማይወዳጀው የፖሊስና የፀጥታ ሠራተኛ፣ ሥራ አጡ ወገን፣ ህጻኑ፣ ሽማግሌው፣ ለማኙ፣ በረንዳ አዳሪው፣ ሴተኛ አዳሪው፣ ወዘተ. እንዴት እንደሚኖር ብታዩ በኢትዮጵያ ያጡ የነጡ ድሆችን ሣይሆን በምሥኪኖች ላብና ደም የከበሩ ሀብታሞችን ደኅንነት ለመጠበቅ ብቻ ተግቶ የሚሠራ ሥውር ምናልባትም መንፈሣዊ ኃይል መኖሩን እንድታምኑ ትገደዳላችሁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ ሁሉ ተነግሮ በማያልቅ የኑሮ ውጣ ውረድና መሪር አገዛዝ እያረረና እየነደደ የሚገኝ ሕዝብ ርስ በራሱ ተባልቶ እንዳያልቅ ለመርዳት ሲል ፈጣሪ ጓዙን ጠቅልሎ ኢትዮጵያ ውስጥ የከተመ እስኪመስለን ድረስ በፈጣሪ ጥበቃ እንድንገረም የሚያደርግ ሁኔታ እንታዘባለን – የዕንቆቅልሽ ምናውቅልሽ ሀገር፤ ኬንያ ወይም ደቡብ አፍሪቃ እኮ ቀን በቀን ነው ሰው የሚዘረፈው፡፡ እዚህ የምናየው ትግስት ልዩ ነው፡፡ ራሱ እየተራበ የሰው ወርቅ ሲጠብቅ የሚያድር ዜጋ የምታገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ መሆን አለበት፤ ራሱ በጠኔ እየተሰቃዬ ሀብታሞችን አንደላቅቆ የሚያኖር ሕዝብ የምታገኘውም በአፍሪቃ ቀንድ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ይመስለኛል፤ በ“አንተ ታውቃለህ”ና “አንተ ያመጣኸውን አንተው መልሰው” ነባር ጸሎት የሚኖር ብቸኛ ሕዝብ ቢኖር የኛው ሕዝብ መሆን አለበት፡፡ይሁንና ግን ጊዜ የማይወልደው ክስተት የለምና እየተንተከተከ ያለው ማኅበራዊ ቀውስና ፍትህ አልባው የሀብት ክፍፍል አንድ ቦታ ከተነፈሰ መመለሻ የለውም፡፡ “ማን እየኖረ ማን ይሞታል?” ከሚል አሳማኝ መነሻ ሆድ የባሰው ሁሉ ሀገሪቱን የሁከት ማዕከል እንዳያደርጋት ያሰጋል፡፡ ሊቢያና ሦርያም ከብዙ አሠርት ዓመታት ግፍና በደል በኋላ ነው የአሁኑን አስጠሊታ ቅርጽ ሊይዙ የቻሉት፡፡ እናም መፍራት ደግ ነው፡፡ “አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን በያዝሽ” ነው ነገሩ፡፡ የናቁት ማስረገዙ፣ የጠሉት መውረሱ፣ … ከጥንትም ነበር፡፡
የሕዝባችንን ቁስቁልና ለመረዳት እስኪ ለአብነት የአውሮፓን ካምቦሎጆዎችና የሀገራችንን ካምቦሎጆዎች በእግር ኳስ ግጥሚያዎች ጊዜ ተመልከቱ፡፡ የአዲስ አበባ ኳስ ሜዳ በምን ዓይነት ደቃቃ ሰዎች እንደሚሞላ፣ የአውሮፓውያኑ ደግሞ በምን ዓይነት ሰዎች እንደሚሞላ ታዘቡና የደረስንበትን የድቀት ደረጃ አስተውሉ፤ በአለባበስ፣ በሰውነት ይዞታ፣ በቁመት፣ በወርድ … በሁሉም አስተያዩ፡፡ ሰው ምግቡን ይመስላል፡፡ አመጋገብ ብዙ ትርጉም አለው፤ በአስተሳሰብና አመለካከት፣ በፍልስፍና፣ በሥነ ልቦና፣ በአካላዊ ዕድገትና ጤንነት፣ ወዘተ. ምግብ ወሳኝ ነው፡፡ ካለ ተመጣጣኝ ምግብ ጤናማ አእምሯዊ ዕድገት አይገኝም፤ ካለተመጣጣኝ ምግብ ቁንጅናና ውበት የለም፡፡ ካለ ተመጣጣኝ ምግብ ትምህርት መማርም የሚታሰብ አይደለም፡፡ ሆድ ባዶ ሆኖ ወይም አሸርባሸር በልቶ ትምህርት ወደአእምሮ ይገባል ማለት ዘበት ነው፤ የሆዱን ጥያቄ ባግባቡ ያልመለሰ ተማሪ አካሉ ክፍል ውስጥ ይቀመጥ እንደሆነ እንጂ መንፈሱ ወደምናባዊ ኩሽናዎች መሸፈቱ አይቀርም፡፡ ዝም ብለን “ሀበሻ ምቀኛ ነው” ብንል ዋጋ የለውም፡፡ ይልቁንስ ከአመጋገባችን አንጻርም ችግር ይታየኛልና ይህን የተጣመመ የኑሮ ገመናችንን ለማስተካከል ልዩ ኮሚቴ ካሁኑ ተቋቁሞ ይሰብበት፡፡(ይቺ ጤፍ የምትባል ነገር የምቀኝነት መንስኤ ንጥረ ነገር ሳይኖራት እንደማይቀር የሚናፈሰው ወሬም ቢጠና አይከፋም፡፡ ማን ያውቃል?)
በሌላ አቅጣጫ ጥቂቶች መሬትን ተጠይፈው ጮቤ ይረግጣሉ፡፡ ከኛ አላግባብ በሚዘርፉት ገንዘብ አዲስ አበባ ምድር ቃጤ ስትሆን ታመሻለች፤ ታድራለችም፡፡ እኔን እየራበኝና አብዛኞቹ መሠረታዊ ፍላጎቶቼ ታፍነው እነዚህ ጥቂቶች ብሩን ለየምናምኑ ሲረጩት ይታያሉ – ካለድካም የመጣ ገንዘብ ደግሞ እሳት ላይ የወደቀ ቅቤ እንደማለት ነው፡፡ ሀብታሞች ቅጥ አጡ – የኛ ድሀነትም ቅጥ አጣ፡፡ በሀገራችን ሁለት ፍጹም ተቃራኒ ጫፎች ተፈጥረው ለዳኝነት ብቻ ሣይሆን ለታዛቢም ሳይቀር አስቸገሩ፡፡ ሀብታሙ እንዴት እንደሚኖር ስናይ ድሃው ደግሞ ቆሼ ተራ ለፍርፋሪና ለሙዝ ልጣጭ እንዲያ በሺዎች እየተራኮተ ሲታይ የገነትንና የሲዖልን ኅልውና እስክንረሳ ድረስ እንደመማለን – ገነትንም ሲዖልንም በተግባር የምናያቸው ያህል ይሰማናልና፡፡ሙስናው ደግሞ ጣሪያ ያለው አይመስልም፡፡ በደሞዙ ከእኔ ታች የሆነ አንድ የቀበሌ አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ወር እስከወር ከቡና ቤቶች እንደቆርኪ ተጠርጎ ነው ውድቅት አካባቢ ወደቤቱ እየተወላገደ የሚሄደው፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ደሞዛቸውን አያውቁትም፡፡ ከትንሹ እስከ ትልቁ ባለሥልጣን ያለሙስና ቢኖሩ እስትንፋሳቸው ቀጥ የሚል ይመስላቸዋል፤ ይላልም፡፡ ሙስና የሀገራችን የደም ዝውውር ሆናለች፡፡ ካለሙስና የሚኖር የመንግሥት የሥራ ኃላፊ አለ ማለት ያስቸግራል፤ ካለም በድህነት እየተሰቃዬ በመኖር የበይ ተመልካች ለመሆን መርጧል ማለት ነው – ጥሩና አዋጪ ምርጫ፡፡ የአብዛኛው የወቅቱ ምርጫ ግን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ መክበር ነው፡፡ ጨረታና ግዢ ደግሞ ዋናዋ የግል ብልጽና ማሳለጫ ናት፡፡ በቡድንም ይሁን በግል ሀገርን መዝረፍና በአቋራጭ መክበር የብዙዎች ምኞትና የዕለት ተለት ድርጊትም ነው፡፡ ምን ይሉኝ የለም፡፡ የሚሠሩ ነገሮች ደግሞ ብዙዎቹ የጥራት ደረጃቸውን አያሟሉም፡፡ የጨረታ አሸናፊዎች ከዘርና ከሙስና ጋር በቀጥታ የተያያዙ ናቸው – ጥራትና አመክንዮ፣ ሀገርና ሕዝባዊ ወገንተኝነት ዋጋ የላቸውም፡፡ ሥራዎች ተጠናቀው ርክክብ ይፈጸማል፡፡ በሙስና የተሠራ አንድ የግንባታ ዕቅድ ወይ መንገድ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ፍርስርሱ ይወጣና ኪሣራ ብቻ ይሆናል – ያኔ ጠያቂም ተጠያቂም የለም፡፡ ለምን ቢባል ማን ማንን ይጠይቃል? ሁሉም ሌባና ራስ ወዳድ ነው፤ ሁሉም በተመሳሳይ የሙስና ቁስል የነፈረ ነው፤ ቂጥኛም ውርዴን፣ ውርዴም ቂጥኛምን የመጠየቅ ሞራላዊ ብቃትም ሆነ ሕጋዊ መደላድል የለውም – በክት ለበክት እየተጠቃቀሰ ይጠቃቀማል፤ ሀገርና ሕዝብ ግን ያለቅሳሉ፡፡ በመቶ ሺዎች ወጪ ሊሠራ የሚችል አንድ ግንባታ ብዙ ሚሊዮኖች ፈሰውበትም ከሚፈለገውና ከሚጠበቀው የጥራት ደረጃ እጅግ የወረደ ነው፡፡ በእንጨት ባላ የተደጋገፈ አንድ የሕዝብ ትምህርት ቤት አውቃለሁ – ባለ አራት ፎቅ፡፡ እንዲያ ስንጥቅጥቁ የወጣው ደሞ ገና ከርክክቡ ቀደም ብሎ ነው፡፡ ተማሪዎቹ እንዳይወድቁ ወይም ከናካቴው እንዳይደረመስባቸው ያሰጋል – በዚያ ትምህርት ቤት የዘመዴ ልጅ ይማራልና እኔም በዐይኔ አይቼ ተገርሜያለሁ፡፡ ለሀገር ማሰብና መቆርቆር ቀርቷል፡፡ የትም ፍጪው ነው የነገሠው፡፡ ሀገርህ በቁም ሞታለች፡፡ ሀበሻ በያለህበት ዕርምህን አውጣ፡፡ ነገር ግን “ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል” ነውና ተረቱ ያለች ትመስላለች – ሞታ ሳለች፡፡ ሞት ዓይነቱ ብዙ መሆኑን ተረዳ፡፡
ወደሚሰቀጥጠው ኑሯችን ልመልስህ፤ ያንተ ኑሮ የተያዘለት ሊሆን ይችላል – ማለፊያ ኑሮ ማለቴ ነው፡፡ ቢሆንም እኛም ያንተው ወገኖች ነንና እሮሮኣችንን ስማልን፤ እዘንልንም፡፡ ከአንተ በላይ ለኛ ማን ሊያዝንልን ይችላል?፡ እንደዱሮው በተወሰነ ጊዜ ጫማ መግዛት፣ ልብስ መግዛት፣ የቤት ዕቃ መቀየር፣ ወዘተ፣ ዛሬ በተራው ሠራተኛ ዘንድ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ገንዘብ ልታገኝ ትችል ይሆናል፡፡ ዘመድም ሊሰጥህ፣ ጓደኛም ሊለግስህ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሚሰጥህ የገንዘብ መጠን በመቶ ሺዎችና በሚሊዮን የሚገመት ካልሆነ በስተቀር በመቶዎችና በጥቂት ሺዎች የሚገመት ከሆነ ከተወሰኑ ቀናት የምግብ ፍጆታ ውጪ የሚያልፍ አይደለም፡፡ የገንዘቡን የመግዛት አቅም ምች አጠናግሮት ተሽመድምዷል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ብዙዎች በሚያገኙት መጠነኛ ገንዘብ ምንም ዓይነት ሻል ያለ ነገር መሥራት እንደማይችሉ ከመገንዘብ አኳያ እምብርታቸውን ወትፈው ሌት ከቀን ሲጠጡና ሲሰክሩበት የሚታዩት – ይህ ደግሞ እውነተኛ የደስታ ስሜት መገለጫ ሣይሆን የተስፋ መቁረጥ ስሜት የወለደው ጊዜያዊ መጠለያን የመሻት ፍላጎት የፈጠረው ነው፡፡ እና መጠጥ ቤቶች ሞልተው ቢታዩ አገር አማን ነው ማለት አንችልም፡፡ በነገራችን ላይ ይህን መሳይ በሁሉም ረገድ የወደቀና ከሆዱ ባለፈ ምንም ነገር ማሰብ የማይችል ሕዝብ መግዛት ለአምባገነኖች ሠርግና ምላሽ ነው፡፡ የተማረና የሠለጠነ፣ በሀብትም በትውፊትም የዳበረ ማኅበረሰብ ገዢዎቹን ብዙ ጥያቄ ይጠይቃል፡፡ መብቱን ያስከብራል፡፡ እንደኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች የሚገኙ ማይም ገዢዎች ግን ሕዝቡ እንዳይነቃና ከዕለት ጉርሱ ባለፈም ሀብት እንዳይኖረው በማድረግ እንደእንስሳ እየገረፉ ይገዙታል፡፡ የኛ ግን ባሰና ለዕለት ጉርስና ለዓመት ልብስብም መድረስ አቃተን፡፡ ፈራጁ ኃያል አምላክ በመጨረሻው የድርሻቸውን አይከለክላቸውም፡፡ በዚያ ብቻ እንጽናናለን፡፡
ሰዎች ሀብታም የሚሆኑባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ፡፡ አብዛኞቹ ግን ሕገወጥ፣ ኢ-ሞራላዊና ኢ-ሃይማኖታዊ ናቸው፡፡ በነዚህ መንገዶች ለመክበር መሞከር መጨረሻው ባያምርም ብዙዎቹ የሀገራችን ሀብታሞች ይጓዙባቸዋል፡፡
በህጋዊ መንገድ ነግደህ በአሁኑ ሰዓት አትከብርም፡፡ ምክንያቱም ውድድሩ ከባድና ፈታኝም ነው፡፡ ወያኔዎች ደግሞ የዋዛ አይደሉም፡፡ ሌሎችን ለማደኽየት፣ እነሱንና የነሱን ግን ለማክበር አጥብቀው ስለሚሠሩ የውድድሩን መንፈስ ይበልጥ ሕገወጥና አድልዖዊ ያደርጉታል፡፡ በዚህ የተንሸዋረረ ተናግዶት ነግደህ የትም አትደርስም፡፡ ለምሳሌ ቀረጥ ከፍለህ ያስገባኸውን አንድ ዕቃ ከ15000 ሺህ ብር በታች ብትሸጠው ሊያከስርህ ይችላል፡፡ አንዱ የወያኔ ንክኪ ነጋዴ ግን 10000 ሺህ ብር ሲሸጠው ታያለህ፡፡ የተያዘው ጥረት አንዱ ከሌላው ተባብሮ ለማደግ ሣይሆን አንዱ አንዱን ገድሎ በተናጠል የመመንደግ ነው – በተለይ ከዘር አኳያ የሚታየው ዐይን ያወጣ ጠንጋራ አሠራር በኢትዮጵያዊነትህ ብቻ ሣይሆን በሰብኣዊ ፍጡርነትህም እንድታፍር ትገደዳለህ፡፡ ለዚህም ነው ኢትዮጵያ የለየላት ሲዖል እየሆነችባቸው ብዙዎች የተማሩ ዜጎቿ ወደምዕራቡ ዓለም የሚሰደዱት፡፡ ለዚህም ነው ብዙም ያልተማሩት ዜጎቿ የሚያልሙት እውን ባይንላቸውም እንኳን የበረሀና የባሕር እንስሳት ሲሳይ ወይም የህገወጥ የሰውነት መለዋወጫ ሰለባ ሆኖ የመቅረትን መጥፎ ዕድል እየተረዱም ጭምር በሀገራቸው የሚገኘውን የባንዳዎች መንግሥት አምርረው ከመጥላታቸው የተነሣ ወደውጪ በገፍ የሚፈልሱት፤ በየትኛውም ሚዛን ቢለካ ከዚህ የበለጠ የሀገር ውርደት ሊኖር አይችልም፡፡ ሀገሪቱ ጠማማ ሚዛን ላይ የተቀመጠች ራሷም የተጣመመች ሆናለች፡፡ የጨረባ ተዝካር፡፡ ወደላይ ብትጮኸ የሚሰማህ የለም፤ ወደታች ብትጮኽ የሚሰማህ የለም፡፡ ጩኸትህ ሁሉ የቁራና የምድረ በዳ ጩኸት ሆኖ ይቀራል፡፡ አማራጭ ስታጣ ታዲያ ትሰደዳለህ ወይም ታብዳለህ – ሁለቱም መጥፎ አማራጮች ናቸው፡፡
የወያኔ ሰብኣዊ ንብረት ከሆንክ ቢያንስ እንዳትራብ እነሱው የሚቆጣጠሩት መቁነን ይሠፍሩልሃል – እንዳትሞት እንዳትድን፡፡ በሀብትና በሥልጣን ወደላይ ብቅ ካልክ ለነሱም እንደማትበጃቸው ስለሚገምቱ ይመስላል ያን አይፈቅዱልህም፤ አንተ ግን የማንም ሥጋት እንደማትሆን ቢያንስ ልቦናህ ያውቀዋል፤ ለምን ብለህ? ሀገር ሰፊ ናት፤ ለሁሉም ትበቃለች፡፡፡፡ እነሱ ግን በሀብትም በሥልጣንም ከነሱ አጠገብ እንዳትደርስ አጥብቀው ይከታተሉሃል፤ ይቆጣጠሩሃል፡፡ ወያኔዎች ምድራችን ከፈጠረቻቸው ክፉ ፍጡሮቿ የመጨረሻዎቹ አደገኛ የሲዖል ትሎች ናቸው፡፡ ነግድም፣ የመንግሥትን ደሞዝ አግኝም በርቀት መቆጣጠሪያቸው እየለኩ ዘወትር ስላንተ ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ ጥቃቅንና አነስተኛ በሚባሉ የሚያደራጇቸውን ምሥኪን ዜጎችም በዚህ መልክ ነው ለነሱው መሣሪያነት የሚጠቀሙባቸው፡፡ ሲፈልጉ ቸርቺል ጎዳና መሃል ላይ ድንኳን ተክለው እንዲነግዱ ሊያደርጓቸው ይችላሉ፤ ሲፈልጉ አንዱን የመንግሥት አዳራሽ ሰጥተው ለተወሰነ ጊዜ ሊያስነግዷቸው ይችላሉ፡፡ አንተን ግን ጫካ ውስጥ እንኳን ዛፍ ሥር ተቀምጠህ ልነግድ ብትል መጥተው ነግደህ ልታገኝ ከምትችለው አጠቃላይ ገቢ በዕጥፍ ድርብ የሚበልጥ ቀረጥ ይጥሉብሃል፡፡ ወያኔዎች ብልጥም ናቸው – ሂድ አይሉህም እንድትሄድ ግን ያደርጉሃል፡፡ ውጣ ላይሉህ ይችላሉ – እንድትወጣ ግን የማያደርጉብህ ግፊት የለም፤ ያኔ መሮህ እያለቀስክ ትወጣለህ – ካገርህም ጭምር ብን ብለህ ትጠፋላቸዋለህ፡፡ ሌላውና ከወያኔ ጋር የተሞዳሞደው ሀገርንም የሸጠው ወገን ግና መንገዱ ሁሉ ቀኝ በቀኝ ሆኖ በአጭር ጊዜ ይከብራል፡፡
አንዱ የመክበሪያ መንገድ እንግዲህ ወያኔን መጠጋትና በሕገወጥ ንግድ፣ ዐይን በሌለው የዋጋ ንረት በአጭር ጊዜ ቱጃር መሆን ነው፡፡ በዚህ ሂደት ከሕዝቡ አጠቃላይ ቁጥር አንድ መቶኛ የማይሆኑት ጥቂቶች ሽቅብ ሲወነጨፉ ሌሎች በቁማቸው መቀመቅ ይወርዳሉ – በሸፋፋ ጫማ፣ በነተበ ሸሚዝ፣ በቀዳዳ ሱሪ፣ በተጠገነ ፓንትና ካልሲ ወደቢሮ የሚሄዱ ዜጎችን ብታስተውል ሥርዓቱ የፈጠረው ሸፋፋ አካሄድ እንጂ የነሱ ጥፋት እንዳልሆነ ሊገባህ ይገባል፡፡ እንዲያውም እነዚህን የመሰሉ ዜጎች ሊከበሩና ሊወደሱ ይገባቸዋል፡፡ በ”ሀገርህ ስትወረር አብረህ ውረር” ፈሊጥ ተወስደው ከጠላት ጋር በማበር የድርሻቸውን ያልዘረፉና በሚያገኙት እውነተኛ ገቢ ብቻ ለመኖር የሚፍጨረጨሩ ንጹሓን ዜጎች በመሆናቸው በእጅጉ ሊከበሩ ይገባቸዋል፡፡ እነዚያኞቹ ግን ገና በታሪክ ይዋረዳሉ፤ ትውልዳቸውም አንገቱን የሚደፋባቸውና የሚያፍርባቸው ይሆናሉ፡፡
ሌላኛው የመክበሪያ መንገድ ሰይጣናዊ ነው – በለየለት ሁኔታ ማለቴ እንጂ ማንኛውም ኅሊና ቢስ አሠራር ከክፋነቱ አንጻር ሰይጣናዊ መሆኑን ዘንግቼው አይደለም፡፡ በዚህ ሥልት መተት፣ ትብታብ፣ ጥንቆላና የመሳሰሉት ይካተታሉ፡፡ ማመን አለማመን ያንተ ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ መንገድ በዓለም ደረጃ ከጥንት ጀምሮ በስፋት የሚታወቅና ብዙዎችም የሚመላለሱበት ሰፊ መንገድ ነው፡፡ በጥንቆላና በመተት -ለጊዜውና ነፍሱን ለሰይጣን ሸጦ – የሚያልፍለት ወገን እጅግ ብዙ ነው፡፡
ከሀብታሞቻችን፣ ከሯጮቻችን፣ ከአርቲስቶቻችን፣ ከባለሥልጣኖቻችን፣ ከታዋቂ ሰዎቻችን፣ ከታዋቂ የሃይማኖት አባቶቻችን … መካከል ስንቶቹ ይሆኑ በሰይጣን ጎታቾች ደጅ፣ በአውሊያና ከራማ ጠሪዎች ክድሚያ ቤት፣ በመጣፍ ገላጮች ቀየ፣ በሞራ አንባቢዎች ጎጆ ያልተንከራተቱና የሀብትና የሥልጣን ጫፍ እንዲደርሱ ያልተጎናበሱ? ገመናችን ብዙና ተቆጥሮም የማይዘለቅ ነው፡፡ ይህ ልማዳዊ ነገር ደግሞ በኢትዮጵያ ብቻ የተወሰነ ሣይሆን በመላው ዓለም በተለይም በሕንድ፣ በሱዳንና በምዕራብ አፍሪካ በጣም የተለመደ ነው፡፡ ሰይጣን በተለይ በአሁኒቷ ዓለማችን ውስጥ ትልቅ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ኃይል ነው፡፡ ያከብራል፤ ያደኸያል፡፡ ይሰጣል፤ ይነሣል፡፡ እርሱን የፈለጉ ከችሎታና ከሥልጣኑ እንዲቋደሱ ከፈጣሪ ሥልጣን ተሰጥቶታል ይባላል፡፡ በዚህም ምክንያት ለምሳሌ በአሥር ዓመት ከሚመጣ የእግዚአብሔር ፍርድ ይልቅ በደቂቃዎች ለሚመጣ የሰይጣን “በረከት” እየተሸነፉ ብዙዎች ፈጣሪን ችላ ብለው ወደዚህ ቦርቃቃ መንገድ እንደሚገቡ ይነገራል፡፡ የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ የመረጠ ይገባበታል፤ የፈራ ይመለሳል፡፡ እንደኔ የፈራ ከነድህነቱ እያከከ ይኑር፡፡ ልከክ፡፡ ሀብት ማናባቱ! (እንዲች ልጽናና አይደል?)
ይህ መንገድ እንዴት ያከብራል እነማን በዚህ ከበሩ ምን ማሟላት ያስፈልጋል … የሚሉት ጥየቄዎች ብዙ ስለሚያናግሩ ወደዚያ መግባት አያስፈልግም፡፡ እንጂ በስንቱ ሕንፃ ሥር ምንና እንዴት እንደተቀበረ፣ ማን በጅብ መንጋ መሀል እያስካካ አድሮ ሊነጋጋ ሲል ሰይጣናዊ ማንነቱን ለዋውጦ ሰው በመምሰል ወደንግድ ቤቱ እንደሚመለስ፣ እነማን በየትኞቹ ጠንቋዮችና አበጋሮች ዘንድ ሲፈናደሱ አድረው ሲወጡ እንደታዬ፣ … ብዙና ብዙ ዝግንትል ነገር ከነምሳሌዎች መናገር ይቻላል፡፡ በጥቅሉ ግን በዘመናችን ሰዎች በኑሮ ከመጨነቃቸው የተነሣ ከኅሊናቸውና ከነፍሳቸው ጋር እየተጣሉ ከጤናማ መስመር በመውጣት ወንድምና እህቶቻቸው ላይ ግፍና በደል እየፈጸሙ መሆናቸውን፤ ይህም ግፍና በደል እየቆዬ ወደራሳቸው ይዞርና በምድርም ሆነ በሰማይ የሚጎዳቸውን መጥፎ ድርጊት እያስቀመጡ መሆናቸውን በመጠቆም ባጭሩ ጽሑፌን ልቋጭ፡፡ ሰላም፡፡
ለጠቃሚ ምክርና ገምቢ አስተያየት የምገኝበት አድራሻ፡- nzeleke35@gmail.com

Montag, 23. März 2015

ህዳሴም ሆነ ዉዳሴ ክህዝብ የሚደበቅ ምንም ነገር የለም!

pg7-logoከሰሞኑ አገራችን ኢትዮጵያን በተለይም ብሄራዊ ጥቅሟንና ደህንነቷን በተመለከተ ሁለት አቢይ ዜናዎች የአገራቸን የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ጉዳዮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸዉን አገሮች የአየር ሞገደች ተቆጣጥረዉት ነበር። ከእነዚህ ዜናዎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ኢትዮጵያ፤ ሱዳንና ግብፅ የህዳሴዉን ግድብ አስመልክቶ ስምምነት ላይ ደረሱ የሚል ዜና ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ አለም አቀፍ ጋዜጠኞች የህዳሴዉ ግድብ የሚሰራበት ቦታ ድረስ ሄደዉ ባካሄዱት ጥናት መሠረት የህዳሴዉ ግድብ ፕሮጀክት ባጋጠመዉ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት የተነሳ እንዲዘገይ መወሰኑን የሚያወሳ ዜና ነዉ። አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚሰሩ ምንም አይነት ስራዎችና በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ከየትኛዉም አገር መንግስትና መንግስታዊ ካልሆነ ተቋም ጋር ለሚደረጉ ስምምነቶችና ዉሎች ሁሉ ባለቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነዉ ብሎ ያምናል፤ ስለሆነም አርበኞች ግንቦት ሰባት የኢትዮጵያን ህዝብ ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ከሚመለከቱና በሚስጢር መጠበቅ አለባቸዉ ተብሎ ከሚታመኑ አንዳንድ ጉዳዮች ዉጭ ሌላ ምንም ስራ ወይም አለም አቀፍ ስምምነትና ዉል የኢትዮጵያ ህዝብ ሳያዉቀዉና ሳይሰማዉ በድብቅ መደረግ የለበትም የሚል የጸና እምነት አለዉ። ሆኖም ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ አገዛዝ ኢትዮጵያን ከቅኝ ገዢዎች በከፋ መልኩ የሚገዛ የጥቁር ፋሺስቶች አገዛዝ በመሆኑ የሚሰራቸዉ ስራዎችና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚፈርማቸዉ ዉሎችና ስምምነቶች የኢትዮጵያን ህዝብ ብሄራዊ ጥቅም የሚጻረሩና የሚጋፉ ድብቅ ስምምነቶች ናቸዉ።
ይህ የወያኔ መሪዎች ከኢትዮጵያ ህዝብ ጀርባ ላይ ተሸሽገዉ የሚሸርቡት የድብብቆሽ ሴራ ዛሬ የተጀመረ አዲስ ክስተት አይደለም። ባለራዕዩ መሪ የሚል አላስፈላጊ የቅጽል ስም የተሰጠዉ መለስ ዜናዊ በ2004 ዓም ሐምሌ ላይ ከዚህ አለም በሞት ሲለይ ዜናዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተነገረዉ በነኀሴ ወር ማለቂያ ላይ ነበር እሱም ቢሆን ሞትን ያክል ነገር ደብቆ ማቆየት ስለማይቻል ነዉ እንጂ አይነግሩንም ነበር። ከዚህ በተጨማሪ በሰሜናዊዉ የአገራችን ከፍል ወያኔ ከጎረቤት አገር ጋር የተዋዋለዉ መሬት ቆርሶ የመስጠት ዉል የኢትዮጵያ ህዝብ ሳያዉቀዉና ሳይሰማዉ የተደረገ ዉል ወይም ስምምነት ነዉ።
አርበኞች ግንቦት ሰባት አገራችን ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ብቻ ሳይሆን ከግዛቷ ተነስተዉ ወደ ጎረቤት አገሮች በሚፈሱ አለም አቀፍ ወንዞቿና በሌሎችም የአገር ዉስጥ ወንዞቿ ላይ ግደብ የመስራት ማንም ሊጋፋዉ የማይገባ የተፈጥሮ መብት አላት ብሎ ያምናል። በሌላ በኩል ደግሞ አባይን በመሳሰሉ ድንበር ዘለል ወንዞች ላይ የሚሰሩ ምንም አይነት የልማት ፕሮጀክቶች በዛቻና በማንአለብኝነት ሳይሆን በመግባባት፤ በመመካከርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በሚያዳብሩ መልኩ መሰራት አለባቸዉ ብሎም ያምናል። አርበኞች ግንቦት ሰባት ይህንን የሚለዉ ደግሞ መሠረታዊ ኑሯቸዉ በአባይ ወንዝ ላይ አገሮች ሊያደርሱ የሚችሉትን የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ጫና በመፍራት ሳይሆን ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ከመጀመራቸዉ በፊት ፕሮጀክቶቹን አስመልክቶ ሊነሱ የሚችሉ ዋና ዋና ልዩነቶች መወገድ አለባቸዉ፤ ልዩነቶችን ለማስወገድ ደግሞ የተሻለና አዋጭ የሆነዉ አማራጭ ዲፕሎማሲ ነዉ የሚል ጽኑ አምነት ስላለን በቻ ነዉ።
የወያኔ አገዛዝ እንደ ፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር በ2011 ዓም የህዳሴዉን ግድብ ስራ ሲጀምር ከአራት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ዶላር ወይም 96 ቢሊዮን ብር በላይ የተገመተዉ ግዙፍ ግድብ ስራ ሙሉ በሙሉ ከአገር ዉስጥ የገንዘብ ምንጮች በሚገኝ ገንዘብ እንደሚሰራና አገዛዙ ግድቡንና የግድቡን ስራ አስመልክቶ ምንም አይነት ድርድር ከማንም አገር ጋር እንደማያደርግ ለለህዝብ ቃል ገብቶ ነበር። የግድቡ ስራ በተጀመረ በጥቂት አመታት ዉስጥ የግድቡ ግንባታ የአገሪቱን የካፒታል ጥሪት ሙጢጥ አድርጎ በመብላቱና በሌሎች በተጀመሩና ሊጀመሩ በእቅድ በተያዙ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ በግልጽ የሚታይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማድረግ በመጀመሩ አለም ባንክ፤ አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅትና አያሌ ኢትዮጵያዉያን ምሁራን የግድቡ ስራና ግድቡ ላይ የሚፈሰዉ የካፒታል ብዛት እንደገና እንዲታሰብበት ምክር ለግሰዉ ነበር፤ ሆኖም ምክሩ የተሰጠዉ የሚሰማ ጆሮ ለሌለዉ ለወያኔ ነበርና ሰሚ ታጣ። ዛሬ ግድቡ ከተጀመረና ወያኔም በህዳሴዉ ግድብ ላይ ከምንም ከማንም አልደራደርም ካለ ከአራት አመታት በኋላ አንደኛ የግድቡ ፕሮጀክት ስራ በገንዘብ እጥረት የተነሳ እንዲዘገይ ተደርጓል፤ ሁለተኛ ወያኔ የህዳሴዉን ገድብ አስመልክቶ ከግብፅና ከሱዳን መንግስታት ጋር ስምምነት ላይ ደርሶ የፊታችን መጋቢት 14 ቀን ስምምነቱን ለመፈረም ጎንበስ ቀና እያለ ነዉ።
ለመሆኑ ይህ ወያኔ ከሱዳንና ከግብፅ ጋር የህዳሴዉን ግድብ አስመልክቶ የሚፈራረመዉ የስምምነት ዉሳኔ ይዘት ምንድነዉ? ዉሳኔዉ በሦስቱ አገር መሪዎች ፊርማ ከመፅደቁ በፊት ለምንድነዉ የዉሳኔዉ ባለቤት የሆነዉ የኢትዮጳያ ህዝብ እንዲያዉቀዉ ያልተደረገዉ? ባለፉት አራት አመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ ምንም አይነት ገቢ ከሌላቸዉ ከተማሪዎችና ከአረጋዉያን ጀምሮ እስከ ቀን ሰራተኛዉ ድረስ ለህዳሴዉ ግድብ ግንባታ ገንዘብ አዋጣ ወይም ቦንድ ግዛ እየተባለ በሩ ያልተንኳኳ ኢትዮጵያዊ የለም። ታዲያ ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ በራሱ ገንዘብ ለዕድገቴና ለብልፅግናዬ መሠረት ይሆነኛል ብሎ የሚያሰራዉ ግድብ ስራዉ በገንዘብ እጥረት ሲተጓጎልና በዚሁ ግድብ ዙሪያ ከዉጭ መንግስታት ጋር አለም አቀፍ ስምምነቶች ሲደረጉ ምንም የማይነገረዉ ለምንድነዉ?
የወያኔ መሪዎች ከሱዳንና ከግብጽ መሪዎች ጋር የህዳሴዉን ግድብ አስመልክቶ የተዋዋሉትን ዉል እንመራዋለን ብለዉ ከሚናገሩት ህዝብ ቢደብቁም ካርቱምና ካይሮ ወስጥ ሾልከዉ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ግብፅ የህዳሴዉ ግደብ ፕሮጀክት ላይ የቁጥጥርና የማነጅመንት ድርሻ አንደሚኖራት እየተነገረ ነዉ።እንደዚህ አይነቶቹ ከዚህ ቀደም በፍጹም የማይሞከሩ ወይም የማይታሰቡ ናቸዉ ተብለዉ ሲነገሩ የነበሩ ስምምነቶችና ዉሎች ዛሬ ተደርገዉና የሶስትዮሽ ስምምነት ተደርሶባቸዉ በፊርማ የሚጸድቁት ግድቡን ሰርቶ ለመጨረስ የሚያስፈልግ ገንዘብ ለማግኘት ነዉ ወይስ ሌላ ድብቅ አላማ አለዉ? ደግሞስ ግድቡ የሚሰራዉ ለህዝብ ግድቡን የሚሰራዉም ህዝብ ሆኖ ሳለ ለምንድነዉ ይህ በዉድም በግድም ገንዘብ ካላዋጣህ ወይም ቦንድ ካልገዛህ እየተባለ ቀንና ማታ ሲጠየቅ የኖረ ህዝብ በዚህ ግድብ ዙሪያ የሚደረጉ ዉሎችንና ስምምነቶችን እንዳያዉቅና ጭራሽ እንዳይሰማ የተደረገዉ? ካይሮና ካርቱም ዉስጥ እንደሚነገረዉ ግብፅ በህዳሴዉ ግድብ ግንባታ ዙሪያ የማነጅመንትና የቁጥጥር ሚና ይኖራታል የተባለዉ ዜና እዉነት ከሆነ እኛ እራሳችን አገራችን ዉስጥ በምንሰራዉ ግድብ ግብፅ ሊኖራት የሚችለዉ የማነጅመንትና ቁጥጥር ድርሻ ዬት ድረስ ነዉ የሚሆነዉ …ለምንስ እንዲህ አይነት ሚና እንዲኖራት ተደረገ?
አርበኞች ግንቦት ሰባት የሶስቱ አገሮ መሪዎች ስምምነቱን በፊርማ ከማጽደቃቸዉ በፊት የኢትዮጵያ ህዝብ ለእንደነዚህ አይነት ቁለፍ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት አለበት ብሎ ያምናል። የኢትዮጵያ ህዝብ ኢትዮጵያን አስመልከቶ የሚደረጉ ምንም አይነት ዉሎችና ስምምነቶች ብቸኛዉ ባለቤት ነዉና ከዚህ ህዝብ ተደብቆ የሚደርግ ምንም አይነት ስምምነት ሊኖር አይገባም።ስለዚህም የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህ ከዚህ በላይ ያነሳናቸዉ ጥያቄዎች ጥርት ባለ መልኩ እንዲመለሱለት የወያኔን አገዛዝ ማስጨነቅ አለበት፤ አለዚያ ይህ ጉዳይ ዉሎ ካደረ በኋላ የሚደረገዉ ሩጫ ሁሉ “ቁጭ ብለዉ የሰቀሉትን ቆሞ ማዉረድ ያቅታል” እንደሚባለዉ ይሆናል።
ግብፅና ሱዳን የረጂም አመታት ወዳጅነትና አመታት ያስቆጠረ ወተዳራዊ ስምምነት ያላቸዉ ተጎራባች አገሮች ናቸዉ። እነዚህ ሁለት አገሮች በቅርቡ ከወያኔ ጋር የደረሱበትን ስምምነት “የግብፅን ፍላጎት የሚያረካ” ስምምነት ነዉ እያሉ ካርቱምና ካይሮ ዉስጥ አስተያየት በመስጠት ላይ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ዉስጥ ግን ሁሉም ነገር ህዝብ እንዳያዉቀዉ በሚስጢር መያዙ እየታወቀ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት “አዲስ ምዕራፍ” ተከፈተ እያለ የፈረደበትን የኢትዮጵያ ህዝብ መሸንገል ጀምሯል። በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔ ሱዳንና ግብፅ በቅርቡ ካርቱም ላይ የደረሱበት ስምምነት እዚያዉ ካርቱም ዉስጥ የፊታችን ሰኞ በሦስቱ አገሮች መሪዎች ፊርማ ይጸድቃል ተብሎ በሚጠበቅበት በአሁኑ ወቅት የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታ አል ሲሲ የዉጭ ጉዳይና የዉኃ ኃብት ልማት ሚኒስተራቸዉን አስጠርተዉ ሦስቱ አገሮች የደረሱበትን ሰነድ መርምረዉ ሪፖርት እንዲያቀርቡላቸዉ ማዘዛቸዉ ከወደ ካይሮ ተደምጧል። እንግዲህ ይታያችሁ እኛ ኢትዮጵያዉያን የሦስቱ አገሮች ስምምነት ምን እንደሆነ እንኳን ሳናዉቅ ግብፅ እሷ እራሷ የደረሰችበት ስምምነት አልጥም ብሏት ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጣት ጠይቃለች። ይህ የሚያሳየን አገሮች ለብሄራዊ ጥቅማቸዉና ደህንነታቸዉ ምን ያህል እንደሚጨነቁና አርቀዉ የሚመለከቱ አስተዋይ መሪዎች ደግሞ የሚጨንቃቸዉና የሚያሳስባቸዉ ይህ አሁን የሚመሩት ህዝብ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በተከታታይ የሚመጣዉ ትዉልድ ጭምር መሆኑን ነዉ።እኛ ኢትዮጵያዉያን ግን ለእንደዚህ አይነት መሪዎች አልታደልንም። የኛ መሪዎች እንኳን ለሚመጣዉ ትዉልድ ሊጨነቁ ለዛሬዉም ትዉልድ “እኛ ከሞትን ሠርዶ አይበቀል” የሚሉ ስግብግቦች ናቸዉ።
ወያኔ ከራሱ ዉጭ ማንንም የማይሰማ፤ልዩነትን የማያስተናግድና የሌሎችን ሃሳብ ከሱ ሀሳብ የተሻለ መሆኑን እያወቀም ቢሆን የማይቀበል ችኮ መሆኑን በተደጋጋሚ አሳይቶናል። ዛሬ ላይ ቆመን ወደ ኋላ ዞር ብለን የትናንቱን ስንመለከት ወያኔ በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያም ገና ከጥንስሱ ጀምሮ ያሳየን ይህንኑ ችኮነቱንና “እኔን ብቻ ስሙ” ባይነት ዕብሪቱን ነዉ። በተለይ የህዳሴዉን ግደብ በተመለከተ አባይ ወንዝ ላይ የሚገነባዉ ግድብ ከዚህ ቀደም በማንም ኢትዮጵያዊ ያልታሰበና የልተወጠነ ፍጹም አዲስ የሆነ ወያኔ ለኢትዮጵያ ያበረከተዉ ገጸ በረከት መሆኑን ለማሳየት ብዙ ጥሯል፤ አንዳንድ የዋሆችን ደግሞ አሳምኗል።ወያኔ ሁሌም ቢሆን ጥረቱና ፍላጎቱ እራሱን ከብጤዉ ከደርግ ጋር እያወዳደረ የተሻለ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነዉ እንጂ የተሻለ ስራ መስራት ስላልሆነ በህዳሴዉ ግድብ ላይም አብዛኛዉን ግዜ ያጠፋዉ “አባይን የደፈረ” ተብሎ ለመጠራት ስለሆነ ዛሬ ግድቡ ግንባታዉ አልቆ አገልግሎት መስጠት በሚጀምርበት ወቅት የግድቡ ስራ ከመጀመሩ በፊት ተሰርተዉ ማለቅ የነበረባቸዉን ስራዎች እየሰራ ነዉ።
በቅርቡ አንድ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች ቡድን ግድቡ የሚሰረባት ቦታ ድረስ በመሄድ የፕሮጀክቱን እንቅስቃሴ በተመለከተ ጥናት አትንቶ የግድቡ ስራ በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት የተነሳ ይዘገያል ብሎ ሪፖርት ማቅረቡ የሚታወስ ነዉ። ጉዳዩን በቅርብ ለምናዉቀዉ ለኛ ለኢትዮጵያዉያን ግን እዉነቱ ከዚህ በላይ ነዉ። የህዳሴዉ ግደብ የሚዘገየዉ በገንዘብ እጥረት ብቻ አይደለም። የዚህ ትልቅ ፕሮጀክት ድህረ ጥናት ሁኔታዎችን የላጤነና ቅደም ተከተሎችን ያላገናዘበ ጎደሎ ጥናት ነበር፤ ከዚህ በተጨማሪ ሩጫዉና ግርግሩ የተጀመረዉ የህዳሴዉን ግደብ የመሰለ ግዙፍ የ96 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት በይድረስ ይድረስ ሰርቶ ለመጨረስ ነበር።
የብዙ አለም አቀፍና የአገር ዉስጥ ኤክስፐርቶች ግምት በግልጽ እንደሚጠቀመዉ የህዳሴዉን ገድብ ግንባታ ጨርሶ አግልግሎት የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ፕሮጀክቱ በዕቅድ ከተያዘለት በጀት ከሃምሳ በመቶ በላይ ሊያስፈልገዉ ይችላል። ይህ ደግሞ ዛሬ ወያኔን ስለምንቃወም የምናወራዉ ተራ የፕሮፓጋናዳ ጨዋታ ሳይሆን የዛሬ አራት አመት ወያኔ ከበቂ ጥናትና ዝግጅት ዉጭ አባይን እገድባለሁ ብሎ ሲፎክር የዛሬዋ ቀን እንደምትመጣ አዉቀን በተከታታይ ያስጠነቀቅነዉ ማስጠንቀቂያ ስለሆነ ነዉ። ይህ ሁሉ የሚያሳየን ወያኔ አስቀያሚ መልኩን ለማሳመር ሲል ብቻ በኢትዮጵያ ህዝብ ገንዝብና ጉልበት የህፃን ጨዋታ መጫወቱን ነዉ። ሆኖም ዛሬ የሚያስፈራን ይህ ወያኔ የተጫወተበት መጠነ ብዙ የህዝብ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ግድቡን ሰርቶ ለመጨረስ ተጨማሪ ገንዘብ ለማግኘት የሚያደርገዉ አጉል መቅበዝበዝ ነዉ። በእኛ እምነት የህዳሴዉ ግደብ ተሰርቶ ሲያልቅ ኢትዮጵያን ከጥገኝነት ነፃ ማዉጣት ነዉ ያለበት እንጂ ሌላ አላስፈላጊ የሆነ የፖለቲካ ጥገኝነት ዉስጥ ይዞን መግባት የለበትም። ለዚህም ነዉ አርበኞች ግንቦት ሰባት ወያኔ፤ ግብፅና ሱዳን በአባይ ወንዛችን ላይ የሚሰራዉን ግድብ አስመልክቶ ደረስን የሚሉትን ስምምነት ምኑም ሳይደበቅ ለኢትዮጵያ ህዝብ በግልጽ መነገር አለበት እያለ ህዝብንም ወያኔንም የሚያስጠነቅቀዉ። የግብፅና የሱዳን መንግሰታት አገራቸዉ ዉስጥ ህዝብ የሚወዳቸዉ ወይም የሚጠላቸዉ መንግስታት ሊሆኑ ይችላሉ፤ ሆኖም ከዉጭ መንግሰታት ጋር በሚያደርጉት ምንም አይነት ድርድርና ዉይይት ሽንጣቸዉን ገትረዉ የሚቆሙት ለአገራቸዉ ጥቅም ብቻ ነዉ እንጂ ሌላ ከህዝብና ከአገር የተለየ አጀንዳ የላቸዉም። ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ አገዛዝ በተለይ ባለፉት ሃያ አራት አመታት ብቻዉን ስልጣን ተቆጣጥሮ የኖረዉ ህወሓት ግን ከኢትዮጵያ ህዝብ ዘለቄታዊ ጥቅም የተለየ የራሱ የሆነ አጀንዳ አለዉ። አርበኞች ግንባት 7 ህወሓትንና ይህንን ከህዝብና ከአገር የተለየ አጀንዳዉን የማቆሚያዉ ግዜ ዛሬ ነዉና ጉልበት ያለህ በጉልበትህ፤ ገንዘብ ያለህ በገንዘብህ፤ እዉቀት ያለህ ደገሞ በእዉቀትህ ነገ ሳይሆን ዛሬ ህዝባዊዉን ትግል ተቀላቀል እያለ አገራዊ ጥሪ ያስተላልፋል።

ማንኛውም ተቃዋሚ ድርጅት ስርዓት ከሌለው ከርቸሌ እንከተዋለን የሚል ማስፈራርያ ኃይለማርያም ደሳለኝ አሰሙ

ማንኛውም ተቃዋሚ ድርጅት ስርዓት ከሌለው  ከርቸሌ እንከተዋለን ይህንንም ለማድረግ አቅም አለን የሚል ማስፈራርያ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አሰምተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንትና በጅማ ከተማ ተገኝተው ይህን አድርገን ነጻነት አመጣን ዲሞክራሲን እየቀዳን ለህዝቡ አከፋፈልን አሉ። የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪወች እንዳደረሱኝ መረጃ ከሆነ ሚኒ ኃይለማርያም ኔትወርክ አዘግተው በጅማ ዩኒቨርስቲ ውስጥ አድረዋል ።
ከንግግራቸው ውስጥ ፈገግ ካሰኘኝ ልለፍ ፣ሚኒ ኃይሌ እንዲህ አሉ ማንኛውም ተቃዋሚ ድርጅት ስርዓት ከለለው አቅም አለን ከርቸሌ እንከተዋለን አቤት አቤት ወግ መዓረጉ እንዳይቀር እኮ ነው የትኛው አቅም ነው ? ትልቅ መስኮት የሌለው ቤት ሰርቶ እስረኛ ማጠራቀሜውን ነው ፣ሠላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ንጹህን ህዝብ በፖሊስ ማስደብደቡን ነው ?? ድንቄም አቅም አያ!!!!! ባዶ እጁን ከሚታገል ህዝብ ጋር መሳሪያ ታጥቆ አቅም አለን ሲል ከአንድ መሪ ተብሎ ከተወከለ አሻንጉሊት የማይጠብቅ የቂል ንግግር ።
የዩኒቨርስቲ ተማሪወችን ስብሠባ እንዳይካፈሉ አግደዋቸዋል ።
አቅማችሁን ለኤርትራ መንግስት አሳዩ እንጅ ከእኛ ላይ ቦተሊካችሁን አትንፉብን ።
ለማንኛውም በተያየዘ ዜና ላይ በኤርትራ የጦር ማካማች ሎጀስቲካ ላይ ያአደረሱት የአየር ጥቃት መግለጫው ጅማ ላይ ሳይሆን ቢቢሲ ወይም አልጀዚራ ላይ ቢሆን አሸናፊነትን አልያ ውድቀትን ሊያመጣ ይችላል እንላለን።

Samstag, 21. März 2015

ምርጫ ማላገጫ መሆኑ ማክተም ይኖርበታል። ምርጫ ያጣ ትውልድ!

SC
ብሶት ወለደኝ የሚለውና ጫካ መወለዱን የማይክደው ህወአት መራሹ የወያኔ መንግስት በምርጫ ተመርጬ ነው አገር የምመራው እያለ በከንቱ ሲመጻደቅ የአንድ ትውልድ ዕድሜ መቆጠሩ ነው። ህገ-መንግስቱ ባማሩ ቃላት ያሸበረቀ ጥራዝ ከመሆኑ ባሻገር ለህዝብ የፈየደው ጆሮ አደንቋሪነቱ ብቻ ነው። በተግባር የማይተርጎም ገዢዎች እንደፈልጉ የሚተረጉሙት ህገ -መንግስት የደብተራ ድግምት ከመሆን አይዘልም። ስልጣን የህዝብ መሆኑን ያላሳየ ስግብግብ ስርአት የነገሰባት አገር በትርጉም አልባ ምርጫ የአገርና የህዝብ ገንዘብና ጉልበት እንዲሁም የማይተካው ወርቃማ ጊዜ ለካድሬዎችና አለቆቻቸው ዕድሜ መቀጠያ እየሆነ የዕውር ድንብር መጓዙ ማክተም ይኖርበታል። አዲሱ ትውልድ የራሱን ዕድል ራሱ የሚወስንበት ጊዜ ዛሬ ነው።አሁን። በፕሮፓጋንዳና በቁጥር ጋጋት ዳቦ መሆን ያልቻለ ዴሞክራሲና ነጻነት የትም አገር የለም። “ምርጫ” በህዝብ መልካም ፈቃድ በነጻ የውድድር ሜዳ ላይ በግልጽና ፍትሃዊ መንገድ ተከናውኖ ህዝብ የመረጠውን ለእንደራሴነት የሚሰይምበት መድረክ እንጂ ለአፈጮሌዎች ዕድሜ ልክ ስልጣን ላይ መደላደያ የአንድ ሰሞን የልጆች ሆያሆዬ መስል ባህላዊ ግርግር አይደለም። የመጻፍ፥የመናገር፥የመደራጀትና የሚፈልጉትን የፖለቲካ አስተሳሰብ በነጻነት ማራመድ ወንጀል በሆነባት የዛሬይቱ ኢትዮጲያ ምርጫ በትውልዱ ዕጣ ፈንታ ላይ መቀለጃ የብልጣብልጥ የፖለቲካ ቡድኖች የደራ ገበያ መሆኑ ማክተም ይኖርበታል።በህዝብና አገር መቀለድ የለበትም። አገሪቱ የሁላችንም አገር እንድትሆን ስር ነቀል ለውጥ የግድ ይላል። እስር ቤቶች ለአገራቸው ቅን በማሰባቸውና በሰላማዊ መንገድ ሃሳባቸውን በመግለጻቸው በተለይም ተጽፎ ባልተተርጎመው “ህገመንግስታዊ መብታቸው” በመጠቀማቸው ወንጀለኞች ተብለው በህግ ሽፋን መብታቸው ተገፎ የስቃይ ሰለባ ሆነዋል። የአገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በትውልዱ መልካም አስተሳሰብ ተቀርጾ ከኋላቀርና በታታኝ አመራር ተላቆ የአፍሪቃ ቀደምት ታሪካዊ ህዝብ መሆናችንን ለማደስ የሰቆቃ ስርአቱን ከጥፋት ግስጋሴው ልናስቆመው ግድ ይለናል። ስርአቱ የህዝብን ጥያቄ እስካልተቀበለ ድረስ ሊወገድ ይገባዋል። ባዶ የሚዲያ ዲስኩርና የአድገናል ከንቱ ቀረርቶ ቆሞ ትውልዱ ፍትህና ነጻነቱን አረጋግጦ ለሁሉም ኢትዮጲያዊ “የጋራ እናት የሆነች አገር “በነጻ አስተሳሰብ የምትመራ ህግ የሚከበርባት እውነተኛ አገር ወጣቱ እንዲመሰርት ማነቆውን መበጣጠስ ይገባል፡፡ ረሃብ፥ስደት፥ሰቆቃና ጭፍን ጥላቻ ተወግደው በመረጥናቸውና አመኔታ ስናጣባቸው በህዝባዊ ውሳኔ ልንተካቸው በምንችል የህዝብ ወኪሎች አገር እንድትመራ የነጻነት ጎዳናውን ለመጥረግ እጅ ለዕጅ ተያይዘን የምንጓዝበት ጊዜው ዛሬ ሳይሆን አሁን ነው። ያኔ ምርጫ በኢትዮጲያ ምድር ዘወትር በናፍቆት የምንጠብቀው የአለም ዋንጫችን ይሆናል። ወጣቱ ትውልድ ታሪክ ሰሪነቱን የሚያረጋግጥበት ጊዜ አሁን ነው።ከእንግዲህ ምርጫ ያጣ ትውልድ ሆነን መቀጥል አንችልም፡፡ ምርጫው በዕጃችን ነው።ህዝባዊ ንቅናቄ በማድረግ አማራጭ ያሳጡንን ሃይሎች በቃችሁ ልንል ጊዜው ግድ ይለናል።ተነሱ።እንነሳ።

Freitag, 20. März 2015

ወያኔን በብዕር ሳይሆን በጠብመንጃ

ወያኔ ኢህአዴግ 24 አመታት ሊሞላው እነሆ የሁለት ወራት ገደማ አድሜ ብቻ ቀረው፡፡
በእነዚ 24 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ከላይ ለተዘረዘረው ችግር ሁሉ ምንጭ የሆነው ወያኔ-ኢህአዴግ በጉልበቱ የቀማውን ሉኣላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን ለማስመለስ ትግል አካሂዷል፡፡ በዚህም ምክንያት እልፍ አዕላፎች ወደ ወህኒ ተግዘዋል፤ በርካቶች የሚወዷት አገራቸውን ጥለው ተሰድደዋል፤ ብዙዎች ከቀያቸውና ቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፤ ስፍር ቁጥ የሌላቸው አካላቸው ጎድሏል መንፈሳቸው ተመርዟል፤ አለፍ ሲልም ህልቆ መሳፍርቶች ውድ ህይወታቸውን ከፍለዋል…
ከወያኔ-ኢህአዴግ ጋር የተደረጉት ልዩ ልዩ ትግሎች በአብዛኛው በሰላማዊ ትግል ስልቶች ማዕቀፍ ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉ ብቻ ናቸው፡፡ በተጨሚሪም ተመጣጣኝ ባለመሆናቸው የሚፈለገውን ስር ነቀል ለውጥ በሚፈለገው ጊዜ ለማምጣት የሚያስችሉ አልነበሩም፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያን ህዝብ ዋጋ ብቻ እያስከፈሉ ኢትዮጵያ ልትወጣው ትችል ከማትመስልበት በእሳተ ገሞራ የቀለጠ አለት ከሚፈልቅበት የፖለቲካዊ፡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሸለቆ ውስጥ ተወርውራ ከገባችበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡
አዎ ብዕራቸውን አንስተው በነፃው ፕረስ ትግል ሜዳ ገብተው የተፋለሙ የዘላለም ጀግኖች ናቸው፤ ነገር ግን ወያኔ በብዕር ሳይሆን በጠብመንጃ አረር ሲያነዳቸው ሳይወዱ በግድ በረሃ ወርደዋል፡፡
አዎ ፓርቲ መስርተው ወደምኒልክ ቤተ መንግስተ በታንክ የገባውን ወያኔ በካርድ አናስወጣዋለን ብለው የታገሉ ዛሬም የሚታገሉ ብፁዓን ናቸው፤ ነገር ግን ወያኔ በካርድ ሳይሆን በክላሽን ኮቭ የእሳት ሰደድ ሲያራውጣቸው የታሰሩት ታስረው የሞቱት ሞተው የቀሩት ደግሞ ጫካ ገብተዋል፡፡
ማህበር አቋቁመው ባንድነት ለመታገል የቆረጡ እጅግ ፅኑዎች ናቸው፤ ነገር ግን ወያኔ በመርዛም አስለቃሽ ጭስ በታትኗቸው ዛሬ ተራሮችን እየማሱ ዋሻ ውስጥ ሆኗል ቤታቸው፡፡
አዎ እውነት ነው! ዛሬ ሁሉም የሰላማዊ ትግል አማራጭ በሮች በታላቅ የብረት በር ክርችም ብለው ተዘግተው በጉዋጉንቸር መቆለፋቸው ለሁሉም ሰው ግልፅ ነው፤ ነገር ግን ሁሉም የሰላማዊ ትግል መንገዶች የመጨረሻ መዳረሻቸው በረሃ መሆኑን ሁሉም ሰው በጊዜ ሊገነዘበው ይገባል፡፡ደግነቱ ዘውዱ አበባው

Donnerstag, 19. März 2015

በአርበኞች ግንቦት 7 – ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ!

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracyህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስለሚያደርሰው ዘርፈ ብዙ በደል ብዙ የተነገረለትና የተፃፈበት ብቻ ሳይሆን እየኖርንበት ያለ ሀቅ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚደርስበትን ስቃይ መታገስ ወደማይችልበት ጫፍ መድረሱ በሰበብ አስባቡ በሚፈነዳዱ ተቃውሞዎች የሚታይ ሀቅ ሆኗል።
በሌሎች አገሮች እንዲህ ዓይነት የሕዝብ ምሬት ሲኖር በጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ጥሪ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ይወጣል። ከሕዝብ አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊትና ፓሊስ ከተበደለው ሕዝብ ጎን በመቆም አምባገነኖችን አስወግዶ የሽግግር መንግሥት ያቆማል። በቅርብ ጊዜያት በሕዝባዊ እምቢተኝነት መንግሥት በተቀየረባቸው አገሮች ያየነው እንደዚህ ዓይነቱን ሀቅ ነዉ።
አገራችን ውስጥ ያለው ሁኔታ ግን ከዚህ በእጅጉ ይለያል። ህወሓት ኢትዮጵያ ውስጥ የገነባው የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አመራር በዘር የተደራጀ በመሆኑ የሕዝቡን አጠቃላይ ብሶት ደግፎ ሊቆም ይችላል ብሎ መጠበቅ አይቻልም። ሠራዊቱ እንደ ተቋም ከተበደለው ሕዝብ ጎን እንዲቆም በመጀመሪያ በራሱ በሠራዊቱ ውስጥ ሥር ነቀል ለውጥ መካሄድ አለበት።በዚህ አቅጣጫ የሚሠሩ ሥራዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ ሠራዊቱ ዘረኛ ገዢዎቹን አስወግዶ እስኪመጣ መጠበቅ አይቻልም፣ አይገባምም። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት በሕዝባዊ አመጽ መታገዝ አለበት የሚለው ሁለገብ የትግል የትግል ስትራቴጂ ተመራጭ እንዲሆን ያደረገው ዋነኛ ምክንያት የሠራዊቱ ዘረኛ አወቃቀር ነው። በመረጥነው የትግል ስትራቴጂ መሠረት በሁለቱም ግንባሮች – ማለትም፣ በሕዝባዊ አመጽ እና በሕዝባዊ እምቢተኝነት ግንባሮች ሥራዎች መሠራት አለባቸው። ሁለገብ የትግል ስትራቴጂ እምንፈልገው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ላይ እንዲያደርሰን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁለቱም የትግል ስትራቴጂዎች አኳያ መደራጀት ይኖርበታል። ሕዝባዊ የአርበኛ ሠራዊት ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ሁሉ በኢትዮጵያከተሞችና ገጠሮች፤ በሥራና በመኖሪያ አካባቢዎች በምስጢር የተደራጁ ሕዝባዊ የአርበኛ ሲቪል ክበቦችም በብዛት መደራጀት ይኖርባቸዋል።
በዚህም ምክንያት አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ከህወሓት ዘረኛ ፋሽስታዊ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት የሚመኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲደራጅ ጥሪ ያቀርባል! እያንዳንዱ ነፃነት ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ከሚያምነውና ከሚመስለው ወዳጁ ጋር ይቧደን፤ ቡድኑንም በሥርዓትና በሚስጢር ያደራጅ።
ከእንግዲህ “ምን እንሥራ? ትግሉን እንዴት እንርዳ?” እያሉ ለሚጠይቁ ወገኖቻችን በሙሉ መልሳችን “ከቻላችሁ ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ” የሚል ነው። ድርጅት ኃይል ነው። መደራጀት በራሱ ትልቅ ሥራ ነው። ድርጅት ድርጅት የሚሆነው ደግሞ በሥርዓት ሲዋቀርና በሥነሥርዓት ሲመራ ነው። ስለሆነም ነፃነት ናፋቂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ አደራጅና አስተባባሪ እንዲመጣለት ሳይጠብቅ በራስ አነሳሽነት እንዲደራጅ ይህ ጥሪ ተላልፏል።
በሥርዓት የተደራጀ ስብስብ ሲኖር የሚሠራ ሞልቷል። ይህንን መንገርም አያስፈልግም። የተደራጀ ስብስብ ራሱ ሥራዎችን አቅዶ መሥራትም ይችላል። የሚከተሉት ነጥቦች ለአብነት ተዘርዝረዋል።
  1. የተደራጀ ስብስብ ጠላትና ወዳጁን ይለያል። የጠላቱን ጥንካሬና ድክመቱን ከራሱ ጥንካሬና ድክመት ጋር መዝኖ የወገን ኃይልን ጥንካሬ የሚያጎለብቱ፤ ድክመቶቹን የሚቀንሱ እርምጃዎችን በመውሰድ አቅሙን ይገነባል።

  2. የተደራጀ ስብስብ የጠላትን እንቅስቃሴ እየሰለለ መረጃ ለነፃነት ኃይሎች እንዲደርስ ያደርጋል።

  3. የተደራጀ ስብስብ የተቀናጀ የሕዝባዊ እንቢተኝነት ተግባራትን ይፈጽማል። ለምሳሌ፣በሥርዓቱ የደረሰበትን ምሬት በወረቀት ገንዘብ፣ በአስፋልት፣ በታክሲዎችና በግድግዳዎች ላይ ይጽፋል፤ ገንዘቡን የኤፈርት ንብረት ከሆነው ውጋጋን ባንክ ያስወጣል፤ መዋጮዎችና ግብር ያጓትታል ከዚያም አልፎ አልከፍልም ይላል።

  4. የተደራጀ ስብስብ በሥርዓቱ ላይ ለማመጽ ሁኔታዎችን ያመቻቻል። ሁኔታች ተሟልተው አመጽ ሲቀሰቅስ ደግሞ ትግሉ ግቡን ሳይመታ እንዳይበርድ ፀንቶ ይቆማል።

  5. የተደራጀ ስብስብ ወዳጆቹን አስተባብሮ በጥንካሬው ላይ ተመርኩዞ በአካባቢው ባለ የህወሓት ኃይል ላይ ክንዱን ያነሳል።

በአርበኞች ግንቦት 7 እምነት የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተባባሪና መመሪያ የሚጠብቅበት ጊዜ አልፏል። ህወሓት የዘረጋው የአፈና ሥርዓት የጠበቀ ትስስርና ቁጥጥር ያለው ድርጅት ማቆም እንዳይቻል አድርጓል። ስለሆነም ያለን አማራጭ በርካታ ያለዘወትር የበላይ አካል ክትትል ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር የሚችሉ ስብስቦችን በመላው የአገራችን ክፍሎች በአፋጣኝ ማደራጀት ነው። ይህንን ደግሞ ማድረግ ይቻላል።
ወቅቱ ህወሓትን ከጫንቃችን ላይ ለማውረድ የምንደራጅበት ነው። ድርጅት ኃይል ነው፤ አደራጅና አስተባባሪ ሳንጠብቅ በራስ ተነሳሽነት ዛሬውን እንደራጅ!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ኢሕአዴግ ዓለም አቀፍ ፍርድቤቱን ለምን ይፈራዋል ?


ከአንደኛው የዓለም ጦርነት መባቻ ጀምሮ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት የማቋቋም ጥረት አንዳንዴ ተፋፍሞ ሲግም በሌላ ጊዜ ደግሞ ሲሟሽሽ ቆይቶ ከሰባ ዓመት ያልተቋረጠ ጥረት በኋላ እ.አ.አ በ1998 ዓ.ም ጀሮም ስምምነት በፈረሙ አራት ሀገራት እ.አ.አ በ2ዐዐዐ ዓ.ም በሄግ ከተማ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍ/ቤት ተመሰረተ::
የዚህ ፍርድ ቤት መቋቋም የሰው ልጅ የህግ የበላይነት ለማስፈን ከወሰዳቸው እርምጃዎች እንደዋነኛ ስኬት ተቆጥሮአል:: ይህ ፍርድ ቤት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ተንሰራፍቶ ያለው ባለስልጣናት ለሰሩት ወንጀል ተጠያቂ ያለ መሆን ባህል (Culture of impunity) ይሰብራል በሚል እምነት በህግ ምሁራን፤ ለፍትሕ ከበሬታ ባላቸው ህብረተሰብና መንግስታት ዘንድ በትልቅ ደስታ ተቀባይነት አገኝቶአል:: በአንጻሩ ደግሞ ለሰው ልጅ ሕይወትና መብቶች ደንታ የሌላቸው መንግስታት ይህንን ፍርድ ቤት በመደበኛ ጠላትነት ፈርጀውት ለውድቀቱ ሌት ተቀን ይኳትናሉ:: ለዚህ ፍርድ ቤት ምስጋና ይግባውና የአንድ አገር መሪ እንደቀድሞው በማን አለብኝነት ሰውን እንዳሰኘው ጨፍጭፎ የአንድ ዘመን ወጣት ጭዳ አድርጎ ዙምባቡዌ ጐዳና ላይ መንሸርሸር ቀርቶአል:: ዛሬ እንደ መንግስቱ ኃይለማርያም ያሉ ጨፍጫፊዎችና ሌሎችም ይህንን ሰይጣናዊ ድርጊታቸው ከመፈጸማቸው በፊት ከጀርባቸው ይህ ፍርድ ቤት መኖሩና ለወንጀል ድርጊታቸው አንድ ቀን ተጎትተው በዚሁ ፍርድ ቤት ፊት ቀርበው ከፍትህ ጋር እንደሚፋጠጡ ስለሚያውቁ ከእርኩስ ድርጊታቸው ይታቀባሉ::
አምባገነን መሪዎች ይህንን ፍርድ ቤት ምን ያህል እንደሚፈሩት በአንድ ወቀት በሱዳኑ መሪ በአልበሽር የደረሰው ጥሩ አመላካች ነው:: በዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦበት መጥሪያ የሚያሳድደው አልበሽር ኢትዮጵያን ጎብኝቶ ወደ አገሩ ሲመለስ እግረ መንገዱን መቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ያርፋል:: የተሳፈረበት አይሮፕላን መጠነኛ ችግር ስለገጠመው ጥገና እስኪደረግለት ትንሽ ይዘገያል:: አልበሽር አይሮፕላኑ ውስጥ እየጠበቀ ሳለ አንድ የአሜሪካን አይሮፕላን ቀስ ብሎ የአልበሽርን አይሮፕላን ይጠጋል:: አልበሽር ይህንን የአሜሪካን አይሮፕላን ባየ ጊዜ እኔን ለመያዝ የመጣ ነው በሚል በፍርሃት ይርድ እንደነበር ሁኔታውን የታዘቡ ሰዎች ገልጸዋል:: የአንድ አገር መንግስት የዚህ ፍርድ ቤት ሥልጣን መቀበልና አለመቀበል በአገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት መኖር አለመኖር ልኬት ነው:: ስለሆነም ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚከተሉ አገራት አፍሪቃንም ጨምሮ የዚህ ፍርድ ቤት አባል ሲሆኑ በአምባገነኖች ደግሞ የፍርድ ቤቱ አባላት ካለመሆናቸው በላይ ፍርድ ቤቱን በማውገዝ ግምባር ቀዳሚዎች ናቸው:: ይህንን ፍርድ ቤት የሚያወግዙ መሪዎች እንዲህ የሚሆኑት በፈጸሙት በወንጀል አንድ ቀን እዚሁ ፍርድ ቤት እንቀርብ ይሆናል ከሚል ፍርሃታቸው የመነጨ መሆን አለበት እንጂ ይህንን ለሰው ልጆች መብት ዘብ የቆመ ፍርድ ቤት የማያወግዙበት ሌላ ምን ምክንያት ሊኖር ይችላል?
ይህንን ፍርድ ቤት ከማንኛቸውም መሪዎች በላይ የሚያወግዙት የብቸኛዋ የተባበሩት መንግስታት መመስረቻ ቻርተር የፈረመችው አፍሪቃዊት አገር፣ የዓለም አቀፍ ህግጋት በመቀበል በቀዳሚነት ትታወቅ የነበረችዋ ኢትዮጵያ፣ የዛሬዎቹ መሪዎች ናቸው:: እነዚሁ የኢትዮጵያ መሪዎች ከማንም በላይ ይህንን ፍርድ ቤት ለመዝለፍ በተለያዩ መድረኮች ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ምን ፈርተው ነው ከሚለው ጥያቄ መሸሽ አይቻልም:: የኢትዮጵያ መሪዎች ከማንም በላይ ይህንን ፍ/ቤት በማብጠልጠል በፍርድ ቤቱ የጥላቻ ዘመቻ ለመክፈታቸው ማስረጃዎቹ እነሆ::
1.በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በኒውዮርክ በተባበሩት መነግስታት ጉባዔ ተገኝተው ኢትዮጵያውያንን ባሸማቀቀ መልኩ ይህንን ፍርድ ቤት ሲዘልፉ፣ ሱያንኳስሱ ሰሚ ሁሉ እኚህ ሰውዬ ምንን ፈርተው ነው ይህንን ፍርድ ቤት እንዲህ የሚያብጠለጥሉት ብሎ መየጠቁ አይቀርም:: ፍርድ ቤቶች በነጻነት የፍትህ ስርዓቱን የሚያስተናግዱበት ዴሞክራሲ ሰፍኖ ሕዝብ የስልጣን ባለቤት የሆነበት አገር መሪ አቶ ኃይለማሪያም በፍርድ ቤቱ ላይ ያዘኑበት ዓይነት ነቀፌታ ቢሰነዘር ምናልባት ሰሚ ያገኝ ይሆናል:: እንደ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የውሃ ሽታ የሆነበት አገር በፍርድ ቤቱ ላይ የሚሰነዝረው ነቀፌታና እሮሮ የቁራ ጩኸት ከመሆን አይዘልም::
2.የኢትዮጵያ መሪዎች በፍርድ ቤቱ ላይ የቋጠሩት ቂም በዚህ ብቻ አላበቃም:: አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከኒው ዮርክ ጠቅላላ ጉባዔ መልስ በአዲስ አበባ በተደረገው የአፍሪቃ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ይህንን ፍርድ ቤት ሲያወግዙ በሃፍረት እየተሸማቀቅን አድምጠናል:: ቂሙና ጥላቻው የከረረ በመሆኑ እነዚህ ውርጅብኞችም በቂ ሆነው አልተገኙም::
3.በጥር 25 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም አዲስ አበባ በተደረገው የአፍሪቃ የመሪዎች ጉባዔ በፍርድ ቤቱ ክስ ቀርቦባቸው በቂ መረጃዎች እያሉ እነዚህ ማስረጃዎች ባለመገኘታቸው ክሱ ከተነሣላቸው ከኬኒያው ፕሬዚዳንትና የፍርድ ቤት መጥሪያ ከሚያሳድዳቸው ከሱዳን መሪ አልበሺር ቀድመው የኢትየጵያ ተወካዮች ፍርድ ቤቱን ለማውገዝ አጀንዳ አስያዙ:: ኢትዮጵያ የፍርድ ቤቱን ስልጣን ካልተቀበሉ ጥቂት የአፍሪቃ አገራት አንድዋ መሆንዋ አንሶ የኢትዮጵያ ተወካዮች በምንም መልኩ ሳይነኩ በማያገባቸው ገብተው ሲፈተፍቱ ማየት ከማስገረሙም በላይ ያሳፍራል:: ለፍትህ ከበሬታው በላቸው የአፍሪቃ መሪዎችም ትዝብት ላይ መውደቃቸውም አያጠራጥርም:: ሌላም አስገራሚና የውድቀት ምልክት መሆኑ የሚያረጋግጠው የኢትዮጵያን ውግዘብ ደግፎ በተራው ፍርድ ቤቱ ያብጠለጠለው ማን መሆኑ ታውቃላችሁ? ሙጋቤ:: ባልተለመደ መልኩ በወቅቱ ሙጋቤ እንደልማዱ አላሸለበም ነበር:: የኢትዮጵያ መሪዎች የሙጋቤ ድጋፍና አቋም የአይጥ ምስክር ድምቢጥ አይነት ነው:: ፈረንጆች ወዳጅህ ማን እንደሆነ ብትነግረኝ አንተን ማን እንደሆን እነግርሃለሁ (tell me who your friends are and will tell you who you are) የሚለው ብሂል የኢትዮጵያና የዚምባቡዌ መዎች ማንነት ይገልጻል::
በጉባዔው ላይ ኢትዮጵያ መሪዎች ያቀረቡዋቸው ሃሣቦች ፣ጉባዔው በፍርድ ቤቱ ላይ የፀና አቋም እንዲወስድ፣ ፍርድ ቤቱ በተለይ በአፍሪቃ መሪዎች ላይ ማተኮሩ የዓለም ሕብረተሰብ እንዲያወግግ፣ ወንጀለኛ መሪዎችን የሚዳኝ አፍሪቃዊ ፍርድ ቤት ይቋቋም የሚሉ ነበሩ:: ከእነዚህ ጥያቄዎች አንዱም ውሃ የሚቋጥር አይደለም:: በመጀመሪያ የትኛው የአውሮፓ መሪ ነው መሣሪያ ሳይዙ ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ዜጐች ላይ ጥይት የሚያርከፈክፈው? አሜሪካን ውስጥ ነው ወይስ ኢትዮጵያ አንተ የዚህ ዘር አባል አይደለህም ከዚህ ጥፋ፣ አንተ የዚህ ሃይማኖት ተከታይ ስለሆንክ የሃይማኖት ነጻነት የለህም የሚባለው?
በፍርድ ቤት የተከሰሱት እኮ በነጻ ምርጫ ለስልጣን የበቁት የታንዛኒያ ወይም የደቡብ አፍሪቃ ወይንም የጋና ፕሬዝዳንቶች ሳይሆኑ ሕፃናት ለጦርነት አሳልፎ ያስፈጀው ቻርለስ ቴለር፣ በዳርፉር ጭፍጨፋ ተጠርጥረው ሕይወታቸው የቆጥ ላይ እንቅልፍ የሆነባቸው የሱዳኑ አልበሽር፣ በኃይማኖት ስም ህዝብን ያፈናቀለውና የጨፈጨፈው ዩጋንዳዊው ኮኒ ሲሆኑ እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ ወንጀል የፈጸሙ ወንበዴዎች ናቸው:: ፍርድ ቤት ከቀረቡት ከአስር በላይ አፍሪቃውያን ፕሬዝዳንት አልበሽር ብቻ ክስ እንዲቀርብባቸው ጉዳያቸው ዐቃቤ ህጉ እንዲያጣራ ጥያቄ ያቀረበው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ሲሆን፣ ሌሎች በሙሉ ምርመራው እንዲካሄድባቸውና ክስ እንዲቀርብባቸው ጠያቂዎቹ ኃያላን መንግስታት ሳይሆኑ የየአገራቸው መንግስታት ናቸው:: እንዲያውም ፍርድ ቤቱ በአፍሪቃውያን ወንጀለኞች ላይ ብቻ ቢያነጣጥር እንኳን ለአፍሪቃውያን ፍትሕ እስከቆመ ድረስ ይህ በራሱ ለአፍሪቃውያን ትልቅ ቁም ነገር አይደለም ወይ? ካምቦድያ ውስጥ ወንጀለኞች ስላልተከሰሱ የአፍሪቃ ወንጀለኞች በነጻ ይሂዱ ማለት በዓለም አቀፍ ሕግ ቀርቶ በየአገራቱ ሕግ የተፈቀደ አይደለም:: በነገራችን ላይ በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ ዐቃቢ ህግ አፍሪቃዊ ያለልሆኑ ጉዳዮች ይከሰሱ አይከሰሱ የሚለውን ለመወሰን ከአስር መዝገቦች በላይ በመመርመር ላይ ይገኛል::
ፍርድ ቤቱን የመሰረተው የሮማ ህግ በሚዘጋጅበት ጊዜ የአፍሪቃውያን ተሳትፎ ከየትኛውም አህጉር የበለጠ ነበር:: ከየትኛውም አህጉር በላይ አፍሪቃ አገራት የፍርድ ቤቱ አባል ሆነዋል:: ነገር የተበላሸውና መሪዎቿ ከአቋማቸው ሽብርክ ያሉት አንዳንድ የአፍሪቃ መሪዎች ከዚህ በፊት ልማዳዊ ህግ ሆኖ የቆየውና በሰፊው ሲሰመራበት የነበረው የአንድ አገር መሪ በስልጣን እስካለ ድረስ አይከሰስም የሚለው ሕግ ተለውጦ አሁን ግን በህጉ በተጠቀሱት ወንጀሎች የተጠረጠረ መሪ ከተጠያቁነት አይድንም የሚለው በወንጀል ህጉ ላይ ከሰፈረ ወዲህ ነው::
ሌላው በፍርድ ቤቱ ላይ የሚሰነዘረው ስሞታ ፍርድ ቤቱ የኃያላን መሳሪያ ሆኖአል የሚል ሲሆን ሀቁ ግን ይህንን አያረጋግጥም:: የፍርድ ቤቱ ዋና አቃቢ ህግ የጋምቢያ ተወላጅ ሴት ወይዘሮ ሲሆኑ በፍርድ ቤቱ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የያዙ አፍሪቃውያን በብዛት ይገኛሉ:: የኢትዮጵያ መሪዎች ፍርድ ቤቱን ከመዝለፋቸውም በላይ እግረ መንገዳቸው ለአፍሪቃ የወንጀል ፍርድ ቤት በአፍሪቃውያን ይቋቋም ያሉት የምራቸው እንዳልሆነ ማንም ይገነዘበዋል:: በእውነት አሁን የአፍሪቃ መሪዎች ከጥቂቶቹ በስተቀር የዚህ የሚቋቋመው ፍርድ ቤት መጥሪያ አክብረው ፍርድ ቤት ቀርበው ለቀረበባቸው ክስ መልስ ይሰጣሉ? የተባበሩት መነግስታት የጸጥታው ምክር ቤትና መላው የሰለጠነው ዓለም ከጀርባው ያሳለፈው ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንኳን የመያዝ ትዕዛዝ የወጣበትን አልበሺር በአፍሪቃ በኩራት እንደልቡ ሲንሸራሸር የፍርድ ቤቱ አባል የሆኑ አገራት ይዘው ማስረከብ ሲገባቸው አንዳቸውም ለመያዝ አልሞከሩም::
ይህ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት አባል ለሆኑ አገራት ህዝቦች ከጨቋኝ መሪዎቻቸው የሚጠብቃቸው ከለላ ሲሆን የኢትዮጵያ መሪዎች በኢትየጵያውያን ላይ ለሚፈጽሙ ወንጀሎች ግን ለዓለም አቀፍ ሰላም ጠንቅ እስካልሆኑ ድረስ ኢትዮጵያውያን ምንም አይነት ከለላ የላቸውም:: በህግ ያለተገደበ ስልጣን አደገኛነቱ የተረጋገጠ ነው:: አንድ አምባገነን መሪ ከኋላዬ ህግ አለ እጠየቅበቃለሁ ካላለ ማንን ፈርቶ ከድርጊቱ ይታቀባል? ስለሆነም እንደ ማንኛውም የዓለም ህዝብ ኢትዮጵያውያን የህግ ከለላ ያስፈልገናል:: የዚህ ፍርድ ቤት አባል መሆን ይገባናል:: የጠበቆች ማህበር፣ የህግ ምሁራን፣ የሴቶች ማህበርና የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ኢትዮጵያ የዚህ ፍርድ ቤት አባል እንድትሆን በመንሥስት ላይ የሚችሉትን ያህል ግፊት ማድረግ ይኖርባቸዋል::

Dienstag, 17. März 2015

ከምርጫው በፊት ልናደርገው የሚገባ ሌላ ምርጫ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና)

Gezahegn Abebeበኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ስርዓት በማስመልከት በተለያዩ ድረገጽ እና የዜና አውታሮች ላይ የህዝብን ንቃተ ህሊና ሊይጎለብቱ የሚችሉ የተለያዩ ዘገባዎች ይቀርባሉ። በተለይም ደግሞ ፍትህ፣ነጻነት፣እኩልነትን አስመልክቶ እንዲሁም ሊጀመር ጥቂት ጊዜያት የቀረውንና የኢትዮጵያዊያንን አዕምሮ በያዘው የሀገራችን ምርጫ ዙሪያ መነጋገሩ፣ መከራከሩ እና  ከምርጫው በፊት  መስተካከል የሚገባችውን ነገር ማውሳቱ የሰሞኑ ዓቢይ ጉዳይ ሆኗል። በርግጥ የ1997ቱ ምርጫ የህዝብ ቅስም የተሰበረበት እና እስከአሁንም ድረስ የኢትጵያ ህዝብ ስብራት ያላገገመበት ሁኔታ በስፋት ይታያል። በመሆኑም እንደ እኔ እምነት ፍትህ ከሌለበት ሀገር ከፊታችን ካለው ምርጫ ምንም ይፈጠራል ብዬ የምጠብቀው ነገር ባይኖርም ግን ጥቂት የሚባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች  ምርጫውን አስመልክቱ እየሰሩት ያለው ቅስቀሳ እና ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የወያኔን መንግስት ከስልጣኑ በማውረድ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት እየከፈሉት ያለው መስዋትነትና ሊያስመሰግናቸው ይገባል ባይ ነኝ ።  እርግጥ ነው ከሁሉም አቅጣጫ የሚስተጋባው የኢትዮጵያዊ ድምጽ ሀገርን ከመውደድ እና ለሀገር ነጻነት እንዲሁም ሉአላዊነት የሚከፈል መስዋዕትነት እስከሆነ ድረስ ትግሉ ይፋፋም ይቀጥል ያስብላል። ፍትህ የሰፈነበት ምርጫ ሊካሄድ የተገባ መሆኑን ሁላችንም እንስማማበታለን። የሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች ናፍቆት ሰላም የሰፈነባት ሀገር ላይ ምርጫው የህዝብ እንዲሆን ነው። ይህም ህልም በምድራችን ላይ ተጨባጭ ይዞታ ኖሮት  ተግባራዊ ቢሆን ሀገራችን ምን አይነት ቅርጽ ሊኖራት እንደሚችል ማሰብ ከባድ አይደለም። ስለሆነም በአሁን ወቅት   በምድሪቷ ላይ እየገነነ የመጣው ግፋዊ  አገዛዝ ወደበለጠ ደረጃ ደርሶ እጅግ ከመክፋቱ በፊት የትውልድ ሁሉ ናፍቆት የሆነውን እኩልነት እና  ህዝብ ለብዙ ጥፋት ታልፎ በተሰጠበት እንዲሁም ከሀገሪቷ ፊት ለፊት ታላቅ የሆነ ክስረት ተጋርጦ ባለበት የአምባገነን ስርዐት ዘመን የሰከነና የተረጋጋ ህይወትን በኢትዮጵያ ላይ ለማምጣት ታላቅ የሆነ ርብርቦሽ ያስፈልጋል። ይህንን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የዘቀጠ የፓለቲካ ስርዐት ወደኋላ ከተጎተተበት ኢፍትሐዊ አሰራሩ ተናጥቆ ለማውጣት እና የሰለጠኑ ሀገራት ወደደረሱበት የነጻነትና እና የእኩልነት ክልል ለማድረስ ከጨዋታ ውጪ የተደረጉት የኢትዮጵያ ምሁራን እና ከማንኛውም የእድገት  እንቅፋቶች የጸዳ አላማ ያላቸው ሀገር ወዳዶች የተዘጋባቸው በር ክፍት ሆኖ  በሁሉም ሀገራዊ አቅጣጫ ጉዳይ ላይ ለምድራቸው የሚቻላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉ በተለይም ደግሞ ከፊት ለፊታችን በወያኔ ቁጥጥር ስር ያለው ምርጫ በህዝብ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የኢትዮጵያ ሊሂቃን እድሉ ያለምንም ተጽእኖ በነጻነት ተሰጥቷቸው እንዲሳተፉ ማድረግ ተመራጭነት አለው። ይህን መሰሉ ተግባር በምድሪቷ ላይ የጸና እስከሚሆን ድረስ  እንዲሁም የገዥውን ቡድን እድሜ መቀጠል ፣ የተመዘበሩ ኮሮጆዎች እና የምርጫ ዕቃ ዕቃ ጨዋታ ወቅታቸውን እየጠበቁ ያለፈውን ልማዳቸውን ለመድገም የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ተፈጻሚ ከመሆናቸው በፊት በሁሉም አቅጣጫ መታገል እንደሚገባን እና ከምርጫው በፊት ህዝባዊ አመጽ እንደ አማራጭ ከመውሰድ  በስተቀር በሌላ መንገድ ወያኔን ማክሸፍ እንደማይቻል ሊታወቅ ይገባል። እውነታውን በመሸፋፈን  ወያኔ በምግብ ራሳችንን ችለናል እያለ  በሚቀልድበት በዚህ የረሀብ ዘመን ዘወትር ሽቅብ እየወጣ ሰማይ ለመንካት እየተመነጠቀ ስላለው የኑሮ ውድነት ህዝቡም ሲያወራ ወያኔም ስለ ‹‹11%›› እድገት ሲደሰኩር፣ ህዝብ ስለ ስራ-አጥነት እና  እርዛት ሲያወራ ወያኔ ‹‹ስለኢንቨስትመንት መስፋፋት›› ሲያብራራ፣ ህዝብ ስለረሃብ ሲያወራ መንግስት ‹‹ስለጥጋብ›› መፈክሩን ሲያሰማ ፤ ህዝብ ስለዳቦ ሲጮህ የወያኔ መንግስት ‹‹ስለመሰረተ ልማት›› እያወሩ እርስ በርስ መግባባት ተስኗ ቸው 23ኛ አመት ዐመት አልፎ ተጋምሷል ። ይህ ያላቻ ጋብቻ ይባላል። በድግሳቸው ቀን  አንዱ የደስታ ሌላኛው የሃዘን ሻማ በማብራት አክብረው አሳልፈዋል፡፡ ከእንደዚህ አይነት ስርዓት አልባ ገዢ ጋር ፍቺ ብቸኛ አማራጭ ነው። ምርጫውም ፍትሀዊ እና የህዝብ ካልሆነ በስተቀር ለኢትዮጵያዊያን የሚያመጣው ምንም አይነት ፈውስ እንደሌለው የታወቀ ይሁን። ይልቁኑም የከዚህ በፊቱን ውሸት እና ማስመሰል ረቀቅ ባለ ማደናገሪያው ለመድገም እየተሯሯጠ መሆኑ ግልጽ በሆነበት በዚህ ወቅት አምባገነኑን ወያኔን ከምርጫው ውጭ ለማድረግ በየትኛው ጎዳና ብንሔድ በትግላችን ግቡን እንደምንመታ  እና የተለያዩ የትግል ልምድ ስልቶች ልውውጥ አድርገን ሀይላችንን በማጠናከር በአንድ የተባበረ ኢትዮጵያዊ ክንድ ከምርጫው በፊት ህዝባዊ አመጽን  የሁላችን ምርጫ ይሁን በማለት መነሳት አለብን። የኔ የግል ምልከታዬ በአሁን ሰአት ሀገራችን ባለችበት ደረጃ የትግላችን ኢላማ እና መድረሻው መሆን የተገባው አስቀድሞ በሐስት የወያኔ ነቢያቶች ለተነበዩለት   ምርጫ ተባባሪ ሆኖ በመሰለፍ አምባገነኑ አገዛዝ እንዲቀጥል አስተውጽኦ ማበርከት ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚወስነውሀገር የምትተዳደርበት ልማታዊ የሆነ ህግ በምድሪቷ ላይ የበላይ እንዲሆን የዜጎች እኩልነት እና ሰብዓዊነት የሚከበሩባቸው ስርዓት በማስፈን ወያኔ በጭቆና የተቆጣጠርውን ስልጣን በመቀማት የህዝብ የስልጣኑ ባለቤት ሆኖ  ፍጹም የሆነ ብሩህ ተስፋ የሚታየባትን ኢትዮጵያን መፍጠር  ነው። መቼውንም ቢሆን ወያኔ ለነጻ ፍትሀዊ ምርጫ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ የበላይነት ለምን አልቆመም ተብሎ አይጠየቅም። ምክንያቱም ይህ ቡድን “ከጅብ ጅማት የተሰራ ክራር ምንጊዜም ቅኝቱ እንብላ እንብላ ነው” እንዲሉ ከፅንሰቱም ፀረ ኢትዮጵያዊ መሆኑ የታወቀ ነው። ከዚህ አስከፊ ስርዓት መልካም የሆነ አስተዳደር መጠበቅ የሚታሰብ አይደለምና እንደገና ሌላ ምዝበራ በሀገርችን ላይ ከመፈፀሙ በፊት ምርጫው ጋር ሳንደርስ በፊት የህዝባዊ አመፅ ትግልን በመምረጥ ወደ ውጤት እንጓዝ።  ምርጫው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመርጠው እና የሚወዳደረው እንጂ ለተሳትፎ ብቻ ብቅ ብሎ በወያኔ ሻጥር የሚሸነፍበት ሊሆን አይገባም። ለውጥ የግድ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሁሉንም የማይጠቅም ቢሆን እንኳን ለብዙኃኑ ሲባል የግድ መምጣት አለበት፡፡ የለውጥ ፍርሐትን አስወግደን በቂ ዝግጅት በማድረግ በተገቢው መንገድ ወያኔን ማስወገድ  ይቻላል፡፡ ለውጥ የሚመጠበትን መንገድ ፈርቶ እና ህዝባዊ አምፅን  ተቃውሞ  ለውጥን መጨበጥ ዘበት ነው፡፡ ‹‹መፍራት ያለብን ፍርሐትን ራሱን ነው›› እንዲሉ ፍራንክሊን ሩዝቬልት፡ የትኛውንም ወደኋላ የሚጎትተንን ፍርሀት ትተን ድጋሚ በምርጫው ከመጭበርበራችን በፊት አስቀድመን በህዝባዊ አመጽ መታገንልን እንምረጥ። ከምርጫው በፊት የኢትዮጵያውያን ምርጫ  በህዝባዊ አመጽ ትግል ለዘመናት በአንባገነንነት በስልጣን ላይ ተቀምጦ ህዝብን በማሰር ፣ በመግደል ላይ ያለውን አረመናዊ መንግስት ከስልጣን ላይ ማውረድ ይሆን ነው  መልዕክቴ ። gezapower@gmail.com የሕዝብ ትግል ያቸንፋል !!!

ልዩነታችን ጌጣችን፤ አንድነታችን ህልውናችን ነው

pg7-logo
ኢትዮጵያ ስንል ብዙ የተለያዩ ዘውጎች፤ ብዙ የተለያዩ ቋነወቋዎችና ሀይማኖቶች በአንድነት ይዛና አስተሳስራ ብዙ ፈተ ናዎችን በማለፍ ለረጅም ዘመናት ህልውናዋን ጠብቃ የቆየች ሀገር መሆንዋ መታወቂያዋ ሀገር ማለት ነው። እንዳ ሳለ ፈችው ረጅም ዘመናት ሁሉ እንደየዘመኑ በህልውናዋ ላይ ይቃጣ የነበረውን ጥቃት እነዚያ በዘውጎች፤ በቋነወቋዎችና ሀይ ማኖቶች የተንቆጠቆጡት ልጆችዋ በአንድነት በመሰለፍ ብሎም ድል በመምታት ህልውናዋን አስጠብቀው መዝለቃቸው የነጻነት ሀገር የመሆን መለያዋ ምክንያቶች መሆናቸውንም የሚያሳይ ነው።
ይህ ልዩነታችንን ጌጡ አድርጎ ያስተሳሰረን ኢትዮጵያዊነት በነፃነት የዘለቀ ህዝብ ከማድረግ አልፎ በአንድ ወቅት የስልጣኔ ምንጭና የአለማችን ሀያል ህዝብ ከመሆን ጫፍ አድርሶን እንደነበር አይዘነጋም። በዚያው ልክ ይህ በልዩነታችን ላይ የተገነባ አንድነታችን ሲላላ ህልውናችን ከገደል አፋፍ ላይ የደረሰበት ዘመንም በታሪካችን ውስጥ መታየቱ አልቀረም። “ዘመነ-መሳፍንት” በመባል የሚታወቀው ጥቁር የታሪካችን ክፍል አንዱ ተጠቃሽ ሲሆን ሌላው ዛሬ የምንገኝበት የወያኔ ዘረኛ ዘመን ነው። ትናንት በዘመነ መሳፍንት ህልውናችን አደጋ ላይ ወድቆ ነበር፤ ዛሬም በወያኔ ዘረኞች ዘመን ህልውናችን ከከፋ አደጋ ላይ እንዲገኝ ተደርጓል። በአጭሩ ልዩነታችን ጌጣችን አንድነታችን ደግሞ የህልውናችን ማስጠበቂያ ዋነኛው ቁልፍ መሆኑን መገንዘብ ለማናም አያዳግትም።
ሌላው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በታሪካችን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በህልውናችው ላይ የከፋ አደጋ ያንዣበበት ወቅት ላይ መገኘታቸው ከማንም የተሰወረ አይደለም። ዘመነ መሳፍንት ትናንት ቋንቋ ዘውግና ሀይማኖት ሳይለይ በእያንዳዱ ኢትዮጵያዊ ህይወት ላይ አስከትሎት የነበረውን ችግርና በሀገሪቱም ከአዘቅት የከተተ ከመሆኑም በላይ ይኸው እስከዛሬ ድረስ ውደ ቀድሞ ታላቅነቷ ለመመለስ ከባድ መሰናክል ተክሎ ማለፉን ከትናንት ታሪካችን መረዳት እየተቻለ ዛሬ በእኛ ዘመን ዳግም ከትናንቱ የከፋ ጥልቅ አዘቅት ውስጥእንድንፈቅ በዘረኞች እየተገፋን መሆኑንና ሊያስከትል የሚችለውንም ውጤት ለመረዳት የተለየ እውቀት አይፈልግም። ዛሬ ይህ ልዩነትን እያጎሉና ቂም በቀልን እየዘሩ መጓዛ የጥቂቶች ፍላጎት መሆኑ ባይካድም ከዚህ ቀደም ያስከተለውንና ዛሬም እየታየ ያለውን አደጋ ተገንዝቦ ከወዲሁ መከላከል የእያንዳዳችን ሀላፊነት ሊሆን ይገባል።
ጥቂቶች የህዝብ አሳቢ በመምሰል የሚረጩት የልዩነት መርዝ በሌሎች ሀገራት ላይ ያስከተለውን ፈተናም እንዲሁ ቆ ም ብሎ መፈተሽና ውጤቱንም መመዘን የፈሰሰ ውሀን አፋሽ ከመሆን ማዳኑን መጠራጠር የለብንም። የሶቭየት ህብረት መ ፍረስ፤ የዩጎዝላቪያ እርስ በርስ መባላት፤ የሶማልያ መቋጫ ያጣ ትርምስ ……. ወዘተ ንፁሀንን በገፍ የበላና ዜጎችን ለኢኮኖሚ ድ ቀት የዳረገ፤ በገፍ ስደትን ያስከተለ፤ የጦርነቶቹ መዘዝ ከልጅ ልጅ የማይታረቅ ቂም እያስቋጠረ መገኘቱ ሲታይ ዛሬ በእ ኛም ሀገር ጥቂት የመገንጠል አባዜ የተጠናወታቸው ይዘውን ሊጓዙ የሚፈልጉበትን መንገድ የት ሊያደርሰን እንደሚችል ከራ ሳችንም ያለፈ ታሪክ ሆነ በአለማችን ላይ የታዩ ክስተቶች ውጤት የሆነውን ትርምስና ሽብር በመመልከት ልንማርበትና ከወዲሁ አንድነታችንን በማጠናከር ለመከላከል መስራት ግድ ይለናል።
ከላይ እንደ ምሳሌ የተጠቀሱት ሀገራት በመበታተን ያተረፉተረ ሽብረ፤ ጦርነት፤ ስደትና ድህነት መሆኑ የታዘብነው የዘመናችን ክስተት ሲሆን ቀደም ሲል ለሁለት ተከፍላ የነበረችው ጀርመን ዳግም ከሁለትነት ወደ አንድነት መምጣቷዋ በሰጣት ሁለንተናዊ ጥንካሬ የዓለምችን ታላላቅና ሀብታም ሀገራት በኢኮኖሚ ውድቀት ሲመቱ ያለአንዳች ጭግር የፈተናውን ወቅት ያለፈች ሀገር ለመሆን መብቃትዋን ከአንድነት ሊገኝ የሚችለውን ሁለንተናዊ ጥንካሬ አጉልቶ የሚያሳይ ነው። ሌላው ከሀ ገራችን ህልውናን የማስጠበቅ ፍልሚያ ታሪኮች ውስጥ ጎላ ብሎ የሚታየው የአድዋ ጦርነትና ድል የአንድነትን ዋጋ ከፍ አድርጎ የሚያሳይ አኩሪ ታሪክ ነው። በዘመናዊ የጦር መሳሪያ ተማምኖ የመጣውን ወራሪ የኢጣልያ ጦር በተመጣጣኝ የጦር መሳሪበ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ተማምኖ የመጣውን ወራሪ የኢጣልያ ጦር በተመጣጣኝ የጦር መሳሪያና የሰለጠነ ሰራዊት ሳይሆ ን ቋንቋ፤ ዘውግና ሀይማኖት ሳይለያቸው ሁሉም በአንድነት ለሀገራቸው ህልውናና ለነፃነታቸው በአንድነት በመቆማቸው የተ ገኘ ድል መሆኑም መዘንጋት የለበትም።
ኢትዮጵያችን ደሀ ናት? አዎ ደሀ ናት። ህዝቧም ለዘመናት አንባገነን ስርአቶች እየተፈራረቁበት ህይወቱ የስቃይና የመከራ ሆኖ ቆይቷል? አዎ ቆይቷል። ሀገራችንን ከድህነትና ከዃላ ቀርነት፤ ህዝቧንም ከስቃይና ከመከራ ህይወት አውጥቶ የተሻለ ሀገር፤ ለመፍጠር ዛሬ የወያኔ ዘረኛ ቡድን የሚያራምደው የመንደር ፖለቲካ እውን መፈትሄ ነውን? ብለን ስንጠይቅ ያለፉት 23 የወያኔ የስልጣን ዘመናት እውነቱን ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ። በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ህዝብ በጅምላ ስደት፤ ለቁጥር በሚታክት ሁኔታከመኖሪያ ቀዬ መፈናቀል፤ እስር ቤት በእስር ቤተረ መገንባት፤ እናትና ልጅ ተፈራርተው መመካከር ያልቻሉበት ዘመን፤ ድህነት ከሚባለው ደረጃ ተወርዶ ጭራሽ የሆቴል ትርፍራፊ በጉርሻ የሚሸጥበት ዘግናኝ ወቅት ላይ ለመገኘት ምክኒያት ከመሆኑም በላይ ሀገር አለኝ ብሎ መኩራት እንኳ ከማይቻልበት ህልውናችን ከከፋ አደጋ ላይ የሚገኝበት ወቅት ሆኖ እናገኘዋለን።
ዜጎችን ነቋንቋ በዘውግና በሀይማኖት ከፋፍሎ ለመግዛት የሚያራምደው በታኝ የጥፋት ፖለቲካ ሌላው ቢቀር ዛሬ በቀን ሶስት ጊዜ በልቶ የማደር ሰዋዊ መብት እንኳ ማስከበር ከማይቻልበት ሁኔታ ላይ መደረሱ ከእያንዳዱ ኢትዮጵያዊ የተሰወረ አይደለም። በአንባገነኖች የተጫነበትን የአገዛዝ ቀንበር አስወግዶ የነፃነት አየር የሚተነፈስበት፤ ፍትህ የሰፈነበትና መብቶች የተከበሩበት ሀገር ለመፍጠር በተከፊለ የህዝብ ልጆች የህይወት ዋጋ ለስልጣን የበቃው ወያኔ በማር በተለወሰ መርዘኛ የዘር ፖለቲካው ሳቢያ የተገኘው ውጤት የእለት ጉርስን እስከማጣት የደረሰ ሆኗል ማለት ነው።
በአጭሩ ዛሬ ከ23 አመታት በዃላ እንደ ትናንቱ ሁሉ ይህን ርእሰ-ጉዳይ ማንሳታችን ያለ ምክንያት አይደለም። ይህ በለዩነታችን መካከል ለመገንባት ደፋ ቀና የሚባልለት የልዩነት አጥር እስካሁን የተፈለገውን ያህል ባይሳካም በጠንካራው አንድነታችን ላይ ያጠላው ጥላ ለምን አይነት አሰቃቂ ህይወት የዳረገን መሆኑና ጥያቄዎቻችን ለሆኑት ፍትህ፤ እኩልነትና ነፃነት ምላሽ ከማስገኘት ይልቅ ይባስ ለከፋ አፈናና አገዛዝ የዳረገን መሆኑን ተገንዝበን ቀኑ ሳይመሽ ከወዲሁ ለመፍትሄው በጋራ መስራትብቸኛ አማራጭ መሆኑን ሁሉም እንዲገነዘበው ነው።
3000 ዘመን ያለ ፈተና የተቆጠረ የነፃነት ዘመን አይደለም። የገጠሙን ፈተናዎች በሙሉ በልዩነቶቻችን ላይ በተገነባው ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ተጠብቆ የተገኘ እንጂ…… ዛሬም ቢሆን ዜጎች ልዩነቶቻቸውን የጥንካሬያቸው መሰረት በማድረግ በአንድነት ነፃነታቸው የተረጋገጠበት፤ መብቶቻቸው የተከበሩበት፤ ፍትህ የሰፈነበት ሀገር ለመፍጠር የተጀመረውን ሁለገብ ትግል በማጀብ ከዳር ለማድረስ ለመነሳት ያለፉት 23 አመታት ከበቂ በላይ መሆኑን አጢነን በቃ የምንልበት ወቅት ላይ እንደምንገኝ ለማሳሰብ ነው።
ትናንትም ዛሬም ነገም ልዩነቶቻችን ጌጣችን አንድነታችን ህልውናችን መሆናቸውን ተረድተን ሳይመሽ ሁላችንንም በእኩልነት የማታስተናግድ የሁላችንን ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ!!!!!
ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር!!!!

“ኢህዴን (የአሁኑ ብአዴን) የህወሓት የአማርኛ ዲፓርመንት ነው”

EPRDF11ዚህን አባባል እውነትነት/ሐሰትነት ሊያረጋግጡልን የሚችሉት አቶ ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) በፌስቡክ ላይ አሉ፡፡ ነገር ግን አቶ ያሬድ “ኢህዴን እንደዚያ የሆነው እኔ ከወጣሁ በኋላ ነው” የሚል እይታ ነው ያላቸው፡፡
እኔ አቶ ስየ አብረሃም “ህወሐት የአንድ ሰው አምባገነናዊ ድርጅት የሆነው እኛ ተገፍተን ከወጣን በኋላ ነው” ዓይነት ነገር ሲጠርቁልን ነበር፡፡ አምባገነን የተባለው ሰውዬ አሁን ሞቷል፡፡ እና አሁን ያለው ህወሐት ምን ሊባል ነው?…. አቶ ስዬ “እኛ እንኳን ታሪክ ጦርነት መስራት እንችላለን” በማለት ሲያፈራሩ እንደነበረ የረሳነው መስሎአቸዋል እንበል እንዴ?
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳም “ኦፒዲኦ የተበላሸው እኔ ከድርጅቱ አመራር ጋር በ1993 ከተጣላሁ በኋላ ነው” የሚል አነጋገር ይደጋግማሉ፡፡ ወቼ ጉድ! ክቡር ዶ/ር ነጋሶ ሆይ! እርስዎ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚመረጡ የኢትዮጵያ ህዝብ ያወቀው ገና በታሕሳስ ወር 1987 ላይ ነበር እኮ! ይህም ምርጫው ከመካሄዱ ከአምስት ወራት በፊት መሆኑ ነው፡፡
እነዚህ የቀድሞ አውራዎች “ንስሐ ገብተናል! ከህዝቡ ጋር ወግነናል” ሲሉን ነበር፡፡ ህዝቡም እንደ ዜጋ የመኖር መብታቸውን ተቀብሎታል፡፡ ንስሐውን የእውነት ይሁን የውሸት ማጣራት የኛ ፈንታ አይደለም፡፡ ለራሳቸው ይያዙት፡፡ ይሁንና በየጊዜው የማይገባ ነገር እየለጣጠፉ ይነካኩንና “ዛሬም እንደ ድሮው ሳይሆኑ አይቀሩም” እያልን እንድንጠረጥራቸው ያደርጉናል፡፡
አቶ ያሬድ ናቸው ይህንን ሁሉ ያስለፈለፉኝ፡፡ አላህ ሂዳያ ይስጣቸውና!! በተለይ አቶ ያሬድ ያኔ የለመዱትን ሐቅን የመደበቅ አባዜ ዛሬ ለወጥ አድርገውት መጡ …. እና (አይ….ይቅር አቦ! ንዴት ጥሩ አይደለም፤ ስንረጋጋ ብንነጋገር ይሻላል…)
በነገራችን ላይ ኮብልለው ከወጡት የኢህአዴግ ሰዎች መካከል ከሞላ ጎደል ሐቅን ለመናገር ሲደፍር ያየነው አቶ ኤርሚያስ ለገሠን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ሁሉ አጭቤ ነው፡፡ አጭቤ!! የሌለ ተረት እየፈጠረ ነው ሊያሞኘን የሚፈልገው፡፡ ይህንን ሁሉ ሳይ “እንኳንም ፖለቲከኛ አልሆንኩኝ” እላለሁ፡፡

Montag, 16. März 2015

የኢትዮጵያ (የተደፈረው)ካንጋሮ ፍርድ ቤት ረዳት አብራሪ ሃይለመድን አበራን በሌለበት ከሶ በሌለበት ጥፋተኛ አለ

10411182_10153157222096411_5647246092494119793_n
የኢትዮጵያ ካንጋሮ ፍርድ ቤት ረዳት አብራሪ ሃይለመድን አበራን በሌለበት ከሶ በሌለበት ጥፋተኛ አለ
አዲስ አበባ፣ 07/07/07
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 20ኛው ወንጀል ችሎት ረዳት አውሮፕላን አብራሪው ሃይለመድን አበራ ከተመሰረቱበት ሁለት ክሶች በአንዱ ጥፋተኛ ሲለው ሁለተኛውን ውድቅ አደረገ።
ተከሳሹ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከግንቦት 2000 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በረዳት አውሮፕላን አብራሪነት ተቀጥሮ ይሰራ እንደነበር የክሱ መዝገቡ ያስረዳል።
ለካቲት 10 2006 አጥቢያ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ከ30 ሲሆን የበረራ ቁጥሩ ኢቲ 702 የሆነውን ቦይንግ አውሮፕላን 202 ተሳፋሪዎችን ጭኖ በጣሊያናዊው ዋና አብራሪነት ከአዲስ አበባ በሱዳን በኩል ወደ ጣሊያን ሮም ጉዞ ጀምሯል።
ዋናው አብራሪ ካፒቴን ወደ መፀዳጃ ቤት እንደወጡ ተከሳሹ የበረራ መቆጣጠሪያውን ክፍል በውስጥ በኩል በመቆለፍ አውሮፕላኑን በቁጥጥሩ ስር ማደረጉ በክሱ ተጠቅሷል።
የበረራ ቡድኑ በሩን እንዲከፍት ሲጠይቁት አርፋቹህ የማትቀመጡ ከሆነ በአውሮፕላኑ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ብሎ በማስፈራራት የአውሮፕላኑን መዳረሻ ያለአግባብ በማስቀየር ወደ ሲውዘርላንድ ጀኔቫ እንዲያርፍ አድርጓል።
በዚህም የፌደራል አቃቤ ህግ ተከሳሹ በሌለበት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 20ኛ የወንጀል ችሎት በህገ ወጥ መንገድ በጉዞ ላይ ያለን አውሮፕላን መያዝ ወይም ማገት ብሎም አውሮፕላኑን አየር ላይ ሁለት ጊዜ ከፍ ዝቅ በማድረግ የመንገደኞችን ምግብ ማቅረቢያ ቁሳቁሶች እንዲገለባበጡ አድርጓል የሚለውን በመጥቀስ በፈፀመው በህገ ወጥ መንገድ በጉዞ ላይ ያለን አውሮፕላን አስጊ ሁኔታ ላይ መጣል በሚሉ ወንጀሎች ከሶታል።
ተከሳሹ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ቢደረግለትም ባለመገኘቱ በሌለበት የአቃቤ ህግ ምስክር ተሰምቷል።
በመሆኑም ዛሬ ችሎቱ መዝገቡን መርምሮ በአንደኛው ክስ ጥፋተኛ ሲለው በሁለተኛው ክስ ቁሳቁስ ተገለባበጠ ከሚለው ውጭ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ባለመኖሩ አቃቤ ህግ እንደ ክሱ አላስረዳም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎታል።
ተከሳሹ ጥፋተኛ በተባለበት በአንደኛው ክስ ቅጣት ለመጣል ለመጋቢት 11 ቀን 2007 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
(ኤፍ.ቢ.ሲ)

የኦሞ ስኳር ፕሮጀክቶች ግጭቶችን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አለማቀፉ ቡድን አስጠነቀቀ

የተለያዩ የአለም አገራትን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክንና ለጋሽ ተቋማትን ጨምሮ27 አባላትን የያዘውዲቨሎፕመንት አሲስታንስ ግሩፕ የተባለ አለማቀፍ ቡድን፤ በደቡብ ኦሞ በመከናወን ላይየሚገኙ ሰፋፊ የመንግስት የስኳር ፕሮጀክቶች በአካባቢውግጭቶችን ሊቀሰቅሱ እንደሚችሉ ባለፈው ረቡዕማስጠንቀቁን ብሉምበርግ ዘገበ፡፡
የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር / ሽፈራው ተክለ ማርያም በበኩላቸው፤ በደቡብ ኦሞ የሚከናወኑ የልማትስራዎች ግጭትን ለመከላከል ያለሙእንደሆኑና በአካባቢው የሚኖሩ ማህበረሰቦችም የልማት ዕቅዶቹንበተመለከተ በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል በስፋት መሰራቱን ከብሉምበርግጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅተናግረዋል፡፡ 
የስኳር ኮርፖሬሽን ከቻይና ልማት ባንክ ባገኘው ብድር በደቡብ ኦሞ አካባቢ ስድስት የስኳር ፋብሪካዎችንለመገንባትና 150 ሺህ ሄክታር ላይየሸንኮራ አገዳ ልማት ለማከናወን እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የጠቆመውዘገባው፣ የሸንኮራ አገዳ ልማቱ የአካባቢውን ነባር ነዋሪዎች አኗኗርሊያቃውስ ይችላል ተብሎ እንደሚሰጋ ቡድኑማስታወቁን ገልጧል፡፡
በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች በስኳር ፕሮጀክቶቹ ውስጥ ለመስራት ከሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ወደ አካባቢውመግባታቸውም፣ በአካባቢው የጎሳግጭቶችን ሊቀሰቅስ ይችላል ያለው ቡድኑ፤ ፕሮጀክቶቹ  በአካባቢውየሚከናወኑ የንብ ማነብ፣ የከብት እርባታ፣ የእርሻና የመሳሰሉ ስራዎች ላይተጽዕኖ ሊፈጥሩ እንደሚችሉምባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የስኳር ፕሮጀክቶቹ ተግባራዊ በሚደረጉበት የደቡብ ኦሞ አካባቢ የሚኖሩ አርብቶ አደር ጎሳዎች፣ በፕሮጀክቶቹሳቢያ የግጦሽ መሬት እጥረትሊያጋጥማቸው እንደሚችል፤ ፕሮጀክቶቹ በጥድፊያ መከናወናቸውም በአካባቢውግጭቶች የመከሰት ዕድላቸውን ከፍ በማድረግ ረገድ አስተዋጽኦእንደሚያደርግና ጉዳዩ በአግባቡ ካልተያዘምበአካባቢው አለመረጋጋት ሊከሰት እንደሚችል ቡድኑ ስጋቱን መግለጹንም ዘገባው አመልክቷል፡፡
መንግስት በአካባቢው የሚያከናውናቸውን የስኳር ፕሮጀክቶች በተመለከተ ግልጽነትን ማሳደግ፣ የማህበረሰቦችንሃሳብ ማስተናገድና የፕሮጀክቶቹትግበራ ላይ የሚታየውን ጥድፊያ በመቀነስ የልማት ሽግግሩ ግጭትንበማያስከትል መንገድ እንዲከናወን ማድረግ ይገባዋል ብሏል ቡድኑ፡፡
የቡድኑ አመራሮች ባለፈው ነሃሴ ወር ያደረጉትን ጉብኝት ጨምሮ ባለፉት ሶስት አመታት በተደጋጋሚ ወደ ደቡብኦሞ በማቅናት፣ ከስኳርፕሮጀክቶች ጎን ለጎን በመከናወን ላይ የሚገኘውን የመንግስት የመልሶ ማስፈር ፕሮግራምተጽዕኖ በተመለከተ ግምገማ ሲያደርጉ መቆየታቸውንምአክሎ ገልጧል፡፡