የተለያዩ የአለም አገራትን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክንና ለጋሽ ተቋማትን ጨምሮ27 አባላትን የያዘውዲቨሎፕመንት አሲስታንስ ግሩፕ የተባለ አለማቀፍ ቡድን፤ በደቡብ ኦሞ በመከናወን ላይየሚገኙ ሰፋፊ የመንግስት የስኳር ፕሮጀክቶች በአካባቢውግጭቶችን ሊቀሰቅሱ እንደሚችሉ ባለፈው ረቡዕማስጠንቀቁን ብሉምበርግ ዘገበ፡፡
የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም በበኩላቸው፤ በደቡብ ኦሞ የሚከናወኑ የልማትስራዎች ግጭትን ለመከላከል ያለሙእንደሆኑና በአካባቢው የሚኖሩ ማህበረሰቦችም የልማት ዕቅዶቹንበተመለከተ በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል በስፋት መሰራቱን ከብሉምበርግጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅተናግረዋል፡፡
የስኳር ኮርፖሬሽን ከቻይና ልማት ባንክ ባገኘው ብድር በደቡብ ኦሞ አካባቢ ስድስት የስኳር ፋብሪካዎችንለመገንባትና በ150 ሺህ ሄክታር ላይየሸንኮራ አገዳ ልማት ለማከናወን እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የጠቆመውዘገባው፣ የሸንኮራ አገዳ ልማቱ የአካባቢውን ነባር ነዋሪዎች አኗኗርሊያቃውስ ይችላል ተብሎ እንደሚሰጋ ቡድኑማስታወቁን ገልጧል፡፡
በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች በስኳር ፕሮጀክቶቹ ውስጥ ለመስራት ከሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ወደ አካባቢውመግባታቸውም፣ በአካባቢው የጎሳግጭቶችን ሊቀሰቅስ ይችላል ያለው ቡድኑ፤ ፕሮጀክቶቹ በአካባቢውየሚከናወኑ የንብ ማነብ፣ የከብት እርባታ፣ የእርሻና የመሳሰሉ ስራዎች ላይተጽዕኖ ሊፈጥሩ እንደሚችሉምባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የስኳር ፕሮጀክቶቹ ተግባራዊ በሚደረጉበት የደቡብ ኦሞ አካባቢ የሚኖሩ አርብቶ አደር ጎሳዎች፣ በፕሮጀክቶቹሳቢያ የግጦሽ መሬት እጥረትሊያጋጥማቸው እንደሚችል፤ ፕሮጀክቶቹ በጥድፊያ መከናወናቸውም በአካባቢውግጭቶች የመከሰት ዕድላቸውን ከፍ በማድረግ ረገድ አስተዋጽኦእንደሚያደርግና ጉዳዩ በአግባቡ ካልተያዘምበአካባቢው አለመረጋጋት ሊከሰት እንደሚችል ቡድኑ ስጋቱን መግለጹንም ዘገባው አመልክቷል፡፡
መንግስት በአካባቢው የሚያከናውናቸውን የስኳር ፕሮጀክቶች በተመለከተ ግልጽነትን ማሳደግ፣ የማህበረሰቦችንሃሳብ ማስተናገድና የፕሮጀክቶቹትግበራ ላይ የሚታየውን ጥድፊያ በመቀነስ የልማት ሽግግሩ ግጭትንበማያስከትል መንገድ እንዲከናወን ማድረግ ይገባዋል ብሏል ቡድኑ፡፡
የቡድኑ አመራሮች ባለፈው ነሃሴ ወር ያደረጉትን ጉብኝት ጨምሮ ባለፉት ሶስት አመታት በተደጋጋሚ ወደ ደቡብኦሞ በማቅናት፣ ከስኳርፕሮጀክቶች ጎን ለጎን በመከናወን ላይ የሚገኘውን የመንግስት የመልሶ ማስፈር ፕሮግራምተጽዕኖ በተመለከተ ግምገማ ሲያደርጉ መቆየታቸውንምአክሎ ገልጧል፡፡
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen