Netsanet: ኢትዮጵያ እና የወያኔ ዘረኛ አካሄድ (ያሬድ ጥበቡ)

Samstag, 7. März 2015

ኢትዮጵያ እና የወያኔ ዘረኛ አካሄድ (ያሬድ ጥበቡ)

ያሬድ ጥበቡ
ከቤተ መፃህፍቴ መስኮት ውጪ የማርች አቦ ጥጥ በረዶ ይነሰነሳል ። ጎረቤቴ ውሻዋን ለማናፈስ ወጥታለች ። እኔ እንኳንስ የውጪውን በረዶ የውስጤንም መቋቋሙ ከብዶኛል ። ውስጤን የበረደኝ ያለምክንያት አይደለም ። ትናንትና ማታ አዲስ ከተሰደዱ ወጣቶች ጋር በሲልቨር ስፕሪንጉ የሉሲ ሬስቶራንት ራት እየበላን ሳለ፣ በኢትዮጵያ አየርመንገድ ውስጥ እየተከናወነው ስላለው ዘረኝነት የሰማሁት እንቅልፍ ነስቶኝ አደረ ። እንቅልፍ ባጣ፣ በዚያውም የሰማሁትን ከማምናቸው ምንጮች ለማጣራት፣ ባህርዳር ደውዬ ሃሎ አልኩ ። ማታ የሰማሁትንም አረጋገጥኩ ። ከመለስ ሞት ወዲህ እየተጠናከረ በመጣው የወያኔ ዘረኝነት የተነሳ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 85 በመቶ የሚቀጥረው ትግሬዎችን ብቻ መደረጉንና ፣ ይህንንም የአቶ ተወልደ ወያኔያዊ እርምጃ በመቃወም አዲሱ ለገሰ ከቦርድ ሊቀመንበርነት መልቀቁንና በቦታውም አባዱላ መተካቱ ተነገረኝ።Tigrayan People's Liberation Front (TPLF)
ይህ ለምን አስፈለገ? ለሚለው ጥያቄዬም፣ ከመለስ ሞት ወዲህ ላደረባቸው የበታችነት ስሜትና ፍርሃት፣ አማራጭ አድርገው የወሰዱት ወያኔን እንደ ድርጅት ማጠናከር ፣ ከድርጅቱ ተባረው የነበሩትን መመለስ ፣ ትግሬዎችን በሁሉም መንግስታዊ ድርጅቶች የበላይነታቸውን ማረጋገጥና፣ በአይን አውጣነት በስፋት ትግሬዎችን እንዲቀጥሩ ማድረግ ፣ የተያዘው ስልት ይሄ መሆኑን አጫወተኝ ። ከተባረሩት መሃል ለመመለስ በሚደረገው ጥረትም፣ ለምሳሌ የትግራይ ፕሬዚደንት የአቶ አባይ ወልዱ ታላቅ ወንድም የሆኑት አምባሳደር አውአሎም አባይ፣ በአቶ መለስ ዘመን የተባረሩ ቢሆንም፣ በቅርቡ የመንግስት ቪላ እንዲሰጣቸው ተደርጓል ።
የሚያሳዝነው በቪላው ውስጥ ላለፉት 20 አመታት ነዋሪ የነበሩት አንድ የቀድሞ ረዳት ሚኒስትር በ3 ቀናት ውስጥ ቤቱን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል አለኝ ። ይሄ ሁሉ ሲሆን ብአዴኖች ምን እያደረጋችሁ ነው ስለው፣ እኛማ የአማራ ክልልን መሬት ለመንጠቅ የሚጋፉንን የትግራይ ክልል ወራሪዎች ስንከራከርና የህዝቡን ቁጣ ለማብረድ ላይ ታች ስንል፣ እነርሱ ፌዴራል መንግስቱን ትግራዋይ የማድረግ ስራቸውን እያፋጠኑ ነው አለኝ ። ከወልቃይት ሌላ ምን መሬት ፈለጉ? ብዬ ስጠይቅ፣ “ወልቃይት ትላለህ ጠገዴን አልፈው ሳንጃ እኮ ደርሰዋል ። ችግሩ በጣም ስለተባባሰ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ ራሱ መጥቶ ካድሬዎችን ሰብስቦ እስከማናገር ደርሷል ።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen