በኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት መዋቅር ውስጥ ተመድበው የሚያገለግሉ የሰለላ ሰራተኞች በጽናት መስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተሰማ።
የጎልጉል ታማኝ የዜና ምንጮች አንዳሉት ድርጅቷ ህወሃትንና ታላቁን የአፈና ተቋም የስለላ ኦፊሰር የነበረችው የመክዳት ውጥኗ እውን የሆነላት ከስድስት ዓመት በኋላ ነው። በተደጋጋሚ ጊዚያት የዲፕሎማት ቪዛ እንዲሰጣት ፓስፖርቷን ለኢሚግሬሽን ብትልክም ያልተሳካላት ይህቺ የስለላ ኦፊሰር፣ በመጨረሻ የተሳካላት ስፔን አገር ለስለላ ስልጠና በማግኘቷ ነው።
አዲስ አበባ የሚገኙ ባልደረቦቿ “እርሷ ዕድለኛ ናት” በማለት ለጎልጉል ዘጋቢ እንዳሳበቁት፣ ኦፊሰሯ ስፔን አገር ከባልደረቦቿ ተለይታ ያመራችው ወደ አሜሪካ ነው። እዚያም እንደ ደረሰች እንደማትመለስ አረጋግጣለች። የትግራይ ክፍለ ሃገር ተወላጅና ታማኝ የህወሃት አባል የነበረችው የስለላ ሰራተኛ፣ ከቀበሌ ተነስታ ለከፍተኛ ሃላፊነት የበቃች ታማኝ ነበረች።
በብሔራዊ የደህንነት መዋቅር ውስጥ መሰላቸት፣ አለመተማመን፣ ጫና እንዲሁም ነጻ ሰዎች ሳይቀሩ የሚደረግባቸው ክትትል ጤና የነሳቸው ተበራክተዋል። በተለይም የህወሃት ያልተማሩ ነባር /አንጋፋ ባለሥልጣናት/ ታጋዮች የሚሰጡት ቅጥ ያጣ መመሪያና ወሬ ለቃሚዎቸ ከየመንደሩ ለብር እያሉ የሚያቀረቡት የሰላማዊሰዎችን ህይወት የሚያናጋ መርጃ ዕረፍት እንደነሳቸው የዜናው ምንጮች አመልክተዋል።

“በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃ ተቀምጠው የሚያገለገሉ ባብዛኛው ደስተኛ አለመሆናቸው በገሃድ ስለሚታወቅና የመውጫው ቀዳዳ ስለተዘጋ” በሁሉም አቅጣጫ መሹለኪያ ፈላጊውና በሰላም መኖር የሚመኘው ክፍል እንደሚያይል ያመለከቱተ ዜና አቀባዮች “የኢህአዴግ ዙሪያ መለሱ ቆሽሾዋል፤ የእርስ በርስ መተማመኑም ኮስሷል” ብለዋል። በማያያዝም በርካታ አመራሮች አገር ለቅቀው መውጣት እንደማይችሉ አስታውቀዋል።ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (ሚያዚያ 2፤2006ዓም/April 10,2014) “ከአገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣናት በጭንቀት ውስጥ ናቸው፤ “አሁን ያለው ኢህአዴግ ላዩ በቀለም ቀቢ የተዋበ ይመስላል”” በሚል ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ለአንባቢያን እንዲረዳ ከዚህ በታች በድጋሚ አትመነዋል፡፡ ኢህአዴግ በሙስና ስም የ”ማጥራት ዘመቻ” ማካሄዱን ተከትሎ የተከሰተው አለመተማመንና እርስ በርስ በጥርጥር የመተያየት ችግር ካድሬውን ማስጨነቁ ተጠቆመ።
ኢህአዴግን ለመሰናበት የሚፈልጉ በርካታ ካድሬዎች “ለምን” በሚል የሚቀርብላቸውን ጥያቄ በመፍራት የግድ ፓርቲውን መስለው እንደሚኖሩ ተገለጸ።
የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ቀደም ሲል ኢህአዴግን ተሰናብተው የወጡና በተለያዩ የውጪ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው በማገልገል ላይ ካሉ ያገኘውን መረጃ በመጥቀስ እንደዘገበው፣ የቀድሞ የትግል ጓደኞቻቸው “በደህና ጊዜ ተገላገልክ” በሚል በፓርቲው ውስጥ ችግር ስለመኖሩ እየነገሯቸው ነው። አብዛኞቹ ኢህአዴግን ተለይተው በሰላም ስለመኖር እንደሚያስቡ ነው የተሰማው።

የቤተሰቦቻቸው የወደፊት እድልና የነሱ በፍርሃትና በጭንቀት መኖር አሳዛኝ እንደሆነ የነገሩት የቀድሞ የኢህአዴግ ሰዎች “አሁን ያለው ኢህአዴግ በቀለም ቀቢ የተዋበ ይመስላል” በማለት አንድ በሚኒስትር ዲኤታ ማዕረግ እያገለገለ ያለ የቀድሞ ጓደኛቸው እንደነገራቸው ገልጸዋል።
ለስራ እንኳን ካገር መውጣት የማይችሉ ባለስልጣኖች እንዳሉ ዘጋቢያችን አመልክቷል። በተቀመጡበት ሃላፊነት ወደ ውጪ የሚያስኬድ አጋጣሚ ሲኖር የሚከለከሉ እንዳሉም ያገኛቸውን መረጃዎች ጠቅሶ ዘግቧል። ለሃላፊዎቹ ደህንነት ሲባል የሚሰሩበትን ተቋምና ስም መናገር እንደማይችሉ በመጥቀስ መረጃውን የሰጡት ክፍሎች “ባለስልጣኖቹ በመካከላቸው እርስ በርስ መተማማን ስለማይችሉ ችግራቸውን መወያየት እንኳን አይችሉም” ብለዋል፡፡“በጣም የሚቀርቡኝ ጓደኞቼ ገንዘብ ወደ ውጪ እንድወስድላቸው እስከመጠየቅ ደርሰዋል” ሲሉ የገለጹት የቀድሞ የኢህአዴግ ባለስልጣን፣ ፓርቲው በሙስና ስም ያካሄደው የሽግግር ወቅት የማጥራት ርምጃ የፈጠረው ስሜት አሁን ድረስ እንዳለ ጠቁመዋል።
ሰሞኑንን ወደ አሜሪካ ያቀኑ የቀድሞ የኢህአዴግ ሰው በማግኘት ተመሳሳይ መረጃ ያሰባሰበው ዘጋቢያችን “ኢህአዴግ በከፍተኛ የመበስበስ አደጋ ውስጥ ይገኛል። በዚህም የተነሳ ካድሬው ተዥጎርጉሯል” ሲል ሪፖርት አድርጓል። ኢህአዴግ በውስጥ ያለበትን ችግር ለማድበስበስ የአባይ ግድብ ላይ ትኩረት በመስጠት “የንቅናቄ ሃይል” በማስፋፋት ላይ እንደሆነም ጠቁሟል።
ድፍን ህዝብ የአባይ ግድብን አስመልክቶ ያለው ስሜት በበጎ መልኩ የሚታይ በመሆኑ ኢህአዴግ ይህንኑ የህዝብ ስሜት ለቅስቀሳና ለበሽታው መደበቂያ ለማድረግ እየተጠቀመበት እንደሆነ ተጠቁሟል። የህጻናት ፕሮግራሞች ሳይቀሩ አባይ ላይ ያነጣጠሩ ቅስቀሳዎች እያስተላለፉ መሆናቸውን ያመለከቱት ሰው፣ “ስለ አባይ ግድብ የሚባለውና የሚሰራው ፕሮግራም ችግር የለውም። በአግባቡ ቢሰራበት ብሔራዊ ስሜት ሊገነባበትም በተቻለ ነበር። ይሁን እንጂ ዓለማው የችግር ማለባበሻ እንዲሆን መደረጉ ነው” ብለዋል።
“መለስ ኢትዮጵያን ቢወድ ኖሮ ከባድመ ጦርነት በኋላ የፈረሰውን ብሔራዊ አንድነትና መግባባት መልሶ መትከል ይቻል ነበር” በማለት የተናገሩት እኚሁ ሰው “በወቅቱ ይህንን ሃሳብ ያነሱ ሰዎች ነበሩ” ሲሉ ቁጭታቸውን ይሰነዝራሉ። በማያያዝም ኢህአዴግ የአባይን ግድብ ተንተርሶ ብሔራዊ አንድነት የሚገነባበት፣ መቀራረብና በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር ብሔራዊ መግባባት የሚደረስበት፣ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ መሰረት የሚጣልበት ቢያደርገው እውነተኛው የኢትዮጵያ ህዳሴ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝን በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ለመተካት ህዋሀቶች የሚያደርጉት ሽርጉድ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ሪፖርት መቅረቡ ተሰምቷል። ይኽው ሪፖርት የቀረበላቸው ክፍሎች ቀደም ሲል እንዳደረጉት የህወሃትን ከፍተኛ አመራሮች በማነጋገር ስህተት እንዳይሰሩ እየወተወቱ ነው።
source:ጎልጉል
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen