በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በሃገራችን ፍትሃዊና ዴሞክራስያዊ ምርጫ ሊካሄድ እንደማይችል አስቀድሞ ሰለተገነዘበው የምርጫ ካርድ ሊወስድ ከሚገባው ነዋሪ ህዝብ ከግማሽ በታች እንደተመዘገበ ታወቀ፣
በዚህ መሰረትም ከግማሽ በላይ የሚሆን ህዝብ ስላልተመዘገበና ሊመዘገብ የሚገባው ነዋሪ ህብረተሰብ ሳይመዘገብ ጊዜ በማብቃቱ ምክንያት የዞኑ አስተዳደር የካቲት 12/ 2007ዓ/ም ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁን ለማወቅ ተችሏል፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሃገራችን የምርጫ ካርድ የወሰደ 34 ሚልዮን ስምንት መቶ ሺህ ህዝብ ተመዘገበ እየተባለ በህወሓት-ኢህአዴግ ቴሌቬዥን የቀረበው አሃዝ ፈፅሞ ከሃቅ የራቀ ነው ሲሉ ቡዙዎች ያገባናል የሚሉት ዜጎቻችን እየተነጋገሩበት እንዳሉ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፣
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen