Netsanet: ዝቋላ ገዳም ስላለው የእሳት ቃጠሎ ተከታይ ዜና

Donnerstag, 5. März 2015

ዝቋላ ገዳም ስላለው የእሳት ቃጠሎ ተከታይ ዜና

የሄሊኮፕተር እርዳታ እጅግ ወሳኝ እና አማራጭ የሌለው መኾኑን ከስፍራው የደረሰው ዜና ያመላክታል፡፡ አሁንም እሳቱ እንዳሰቸገረ ነው፡፡ ለማጥፋት የሚቻልበትም ሁኔታ ከሰው አቅም በላይ እንደኾነ እየተነገረ ነው፡፡ በተለይም በአዱላላ ከተማ አዋሳኝ አቅጣጫ በኩል የሚገኘው ገደል ውስጥ እሳቱ የገባ በመሆኑ ሰው እዚያ ውስጥ ለመግባት የማይችልበት ስለኾነ ሌሊቱን ሙሉ ሲደክሙ ያደሩት እሳቱን በማጥፋት ነፍሳቸውን እንኳን ለመስጠት የተዘጋጁት ነገር ግን አሁንም የድረሱልን የርዳታ ጥሪ የሚያሰሙት ወገኖች ተጨንቀዋል፡፡
ገደል ውስጥ ያለው እሳት እዚያው ታፍኖ የሚቀርበት ዘዴ ካልተበጀ በስተቀር ድንገት በሚነሣው ነፋስ አማካይነት የፈነዳ እንደኾነ ለመቆጣጠር የሚያዳግት ውጤት ይኖረዋል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ እንደ ርችት በየአቅጣቻው የመበተን ዕድሉ ከፍተኛ ስለሚኾን ከወዲሁ ባለበት አምቆ ለማስቀረት የአየር ኃይል ርዳታ እጅግ ወሣኝ ነው፡፡
በሌላ በኩል ሌሊቱን ሲጠራራ ያደረው ሕዝብ በደብረዘይት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ በየጀሪካሉ ውኃ እየሞላ ለመንቀሳቀስ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡ ይኽንን ቁጥሩ በርከት ያለ ሕዝብ በፍጥነት ወደቦታው አድረሶ የደከሙትን እንዲተካቸው ወይንም እንዲያግዛቸው ባለመኪኖች እባካችሁ ተባባሩ፡፡
የቤተ ክርስቲያን ልጅነት ዛሬ ነው፡፡ ከዛሬም አሁን ነው፡፡ ጥሪያችንን እየሰማችሁ በመንቀሳቀስ ላይ ያላችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ያበርታችሁ፡፡
abayneh_kasse‬
'ዝቋላ ገዳም ስላለው የእሳት ቃጠሎ ተከታይ ዜና

እንዴት አደራችሁ?

#abayneh_kasse'

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen