አዝናለሁ ዶክተር ነጋሶ !
ህገ መ ን ግ ስ ት ማ ር ቀ ቅ ና መ ተ ግ በ ር በኢትዮጵያ እርሰዎ እንዳሉት አ ሉ ት አ ይ ደ ለ ም
ክቢላል አበጋዝ፡ ዋሽግቶን ዲ፡ሲ
March 01, 2015
ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ሶላን በዋሽግተን ዲሲ ተገኝተው ስለወያኔ መሩ መንግስት
አመጣጥና ዛሬም ቀድሞም በወሬ ብቻ ስላለው ህገመንግስት ገለጻ አድርገው ነበር::`ሟቹ መለስ ዜናዊን በንግግር ጥፊ የመቱበት “ዛሬስ ሊቀ መንበር መንግስቱንመሰልክኝ” ንግግርዎም ተነስታ ነበር።እንዳው ለማስታወስ ከእርሶ ጥፊ ተጀመረና አበበ ገላው በቁጣ መብረቅ ጨረሰው በዚችው ዋሽግተን ዲሲ ከተማችን! ባመኑበት መናገርዎ ሲያስከብርዎ ይኖራል:: ባጋጣሚ እንኳን ወደ ዳያስፖራ ዋና ክተማ በደህና መጡ! እንኴን በስልጣን እያሉ ክዚህ አላደረሰዎ:: ወያኔዎች የደረሰባቸውን አስታውሼ ነው:: ይችን አጭር አስተያየት ባክብሮት ላቅርብ ብዬ ነው:: ዘለፋ አያድርጉብኝ:: ያለፉትን አስክፊ ስርዓቶች ለማስወገድ ሲታገሉ የነበረ መሆኑን ታሪክ ያውሳው:: የዛሬይቱ ኢትዮጵያውስ? ወዴት እየሄደች ነው?ሶማልያ: ሱዳን:የመን:ኢራቅ ሶርያ:ሊቢያ:ግብጽ: እነዚህ አገሮች ባይነ ህሊና ይዘን ነው ሳላነሱት አቢይ ርእስ ብናሰላ የሚበጀው:: እንቀጥል::
የጥናትዎ ርእስ “ህገመንግስት ብዙ ብሄሮች ባሉበት ዲሞክራሲያዊ መንግስት:: የኢትዮጵያ ጉዳይ “ የሚል ነው:: ለኢትዮጵያውያን ሁሉ መወያያ መሆን አለበት:: እኔም እንድጽፍ ያረገኝ እንደዜጋ ያገባኛል፡ እሰማለሁ ብዬ ነው:: ታዲያ ህገመንግስት ዋዛ ነገር አይደለም:: እሶ : መለስና ጀሌዎቹም ወደ አገራችን መጀመሪያ ያመጡትም አይደለም። ተማሪ ሆነው ያስታውሱ ከሆነ ህገ መ ን ግ ስ ትም ፓርላማም ነበሩ። ክርክር የነበረበት ፓርላማ ነበር።የወያኔን ሲያቀርቡ ለምን አላነሱትም ? አምስት ወር የጥናት ጊዜ ተሰጥቶዎ:: የጥናትዎን ውጤት ማቅረብዎ ክሆነ አዝናለሁ:: ያሳፍራል:: ያቀረቡት የመረጡት ርእስዎ አይመጥንም:: ባገራችን ሪፑብሊክ ስለማቌቌም ያልሙ የነበሩ በታሪካችን አሉ:: ህግ እና ህገመንግስት በኢትዮጵያ ረጂም ታሪክ አላቸው:: የስዎም ለዚህ ትልቅ ጉዳይ ጥናት ተለይተው መጋበዝዎ አስደማሚ ነው:: አጠገብዎ የነበረው ፕሮፌሰር ጆን አርቢሶን ከርሶ ካገሬው ሰው በበለጠ ህገመንግስቱ ውክልና የለውም:: ሁሉን ወገን አላካተተም ሲል:: ወያኔ ክጫወታ ውጭ ካደረገዎ በኌላ እንኴን ከወያኔ አቌም ራቅ አላሉም:: ፖለቲክኛ ነዎትና ምነው እንዳዲስ መጀመር አለብን ቢሉ ?ጅሉ ስብሃት ነጋ ብቻ ቢሆን ምን አለ “ህገመንግስት” እያለ ማሰልቸቱን የሚቀጥል ? የስብሃት ነጋ የስካር ነው:: የእርሶ ትምህርት እንክን አይወጣለት። በምሁርነቱ መጠይቅ አቅጣጫ ፍተሻ ቢያደርጉ ምነው? ጠበብ አድርገው እንዲያው የቡድን አምባ ገነንነት እንዳይመጣ የኛ የወደፊቱ ህገመንግስት ምን ይታክልበት? ዓይነትን ጥያቄን ቢታገሉት ኖሮ።
ካለኝ ጠቅላላ ትንሽ እውቀት ህገመንግስት አቢይ የመንግስት መሰረት:የአገሬው ተወላጅ የነጻነት ፍላጎቱ
ነጸብራቅ:የመብቱ:የሀይሉ ምንጭ ነው::መተዳደሪያውና:እብሪተኛ እንዳይነሳበት
መከላከያው:መሞገቻው ነው:: የአገር ዜግነቱ ኮንትራክት ነው:: የደረሰበትም የድገት ደረጃ አንዱ መለኪያ ነው:: የአገር ድንበር ጠባቂው ወታደርም ግዴታው ድንበር መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ህገመንግስቱን ማክበር
እንዲክበርም ማድረግ ነው:: ጸጥታ የሚያስከብረውም ተጠሪነቱ እንዲሁ የህገመንግስቱ ነው::
ህገመንግስትየህዝብ ነው::በህዝብ ነው::ሁሉም ያከብረዋል ሁሉም በኩልነት ይተዳደርበታል:: የህጎችም መሰረት ነው።የኢትዮጵያ ሁኔታ ከዚህ በፍጹም የተለየ ነው:: በኢትዮጵያ ህገመንግስት ሳይሆን:ህገመንግስት የሚባል ቧልት ነው ያለው:: እስዎም የዚያ ድራማ ተዋናይ ነበሩ። አሁንም ያው! አርፈው ቢቀመጡ ምነው?
ህገመንግስት ላንዱ የህብረተሰቡ ክፍል ብቻ አገልጋይ አይደለም:: ተንኮል እያሰቡም የሚረቀቅ አይደለም:: እርስዎ ስደት ሰልችትዎ እፎይ ማለት ፈልገው ክጀርመን አገር ሲገሰግሱ ሌላውም አፈሰማይ ወደ ወያኔ ማዕድ ጎረፈ:: አድር ባዩ ሁሉ ተኮለኮለ:: ይህ ስብስብ ነው የወያኔውን ህገ መ ን ግ ስ ት ያረቀቀ(ወይም የቅጅ የሰራ የሰራው) የህዝብ ተወካዮች ቀርበው አይደለም:: የጥንት ታሪክ አይደለም የምናወራው:: ትላንት ስለሆነ ጉዳይ ነው። ዋቢ መጽሀፍ የሚያስደረድር አይደለም::
ክሁሉ አስቂኙ “የብሄሮች ምብት፡ነጻነት እስክ መገንጠል” የሚለውን አሁንም አምንበታለሁ ብለው ማቅረብዎ ነው:: አስገመተዎ:: ምሁራዊ\ጥናታዊ አቀራረቡ “ሁለት አሰርት ዓመታት ሞክረነው የሚበጅ ነገር ያፈራ አይመስልም “ ማለት ነበር::የኦሮሞ ህዝብ በደል በስደት ካኖረዎ:በህወሃት አገዛዝ የኦሮሞ ህዝብ ምን ተረፈው ? ይህ ህገመንግስት አባዱላን አይነት ወራቤሳዎች አፈራ እንጂ ለኦሮሞ ህዝብ ምን ፈየደው? መሬቱን የተቀማውን አርሶ አደር ስለ ወያኔው ህገመንግስት ሊነግሩት ነው? “የብሄሮች መብት፡ነጻነት እስክ መገንጠል” ሌኒናዊ ስታሊናዊ ደብተራዊ ደንቃራ ነው:: ለራስዋ ለሩሲያ ሰርቷል ? ናሽናል ዔንዳውመት ፎር ዲሞክራሲ የለገሰዎን የጥናት ጊዜ ለምን በክንቱ አባከኑት ? ድፈሩና አዲስ ነገር አስቡ:: ከወያኔ በኌላ ስለምትተዳደረዋ አገራችን አስቡ:: በእኩልነት:በነጻነት:በህብረት ባንድነት ላይ ስለምትቆመዋ አገራችን እናውራ:: መገንጠል መገነጣጠል የድሮ የስድስት ኪሎ ፋሽን ነው:: ይህ ዘመን የብሄራዊ አንድነት:የኩልነት:የፍትህ የዲሞክራሲ ዘመን እንጂ የክልል የጎጥ አይደለም::
ወያኔ መሩ መንግስት ሲቆም በጠመንጃ መጥቶ በጠመንጃ ገዛ ከመባል ህገመንግስት:ምርጫ እያለ መብለጥለጡ የሚያዋጣው መሆኑን ለይቶ በእቅድ ሲሰራ አዳማቂ ይሻው ነበር:: (እነመለስ ምእራቡን ዓለም ለመደለል ወይም በውጭ ሀይላት እየተመሩ) አዝናለሁ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አዳማቂ ነበሩ:: ይህ ሁሉ ውጣ ውረድ ያላስተማረዎ ሌላ ምን እንዲረዱት ያረግዎ ይሆን?መካሪ ጔደኛ ዘመድ የሎትም ?
ህገመንግስቱ ሲረቀቅ ሁሉም ተቃዋሚዎች ተካፍለዋል ብለው እንደዋቢ ያነሷቸው ሰዋች ስማቸውን እንኳን እዚህ ለመጻፍ የሚቀፍ ናቸው:: እንኴን ተቃዋሚዎችን ሊያሳትፍ እንደርሶ አምነው ለመጡትም እንዳልሆነ እራስዎ ተናግረዋል።ኦ ዔል ኤፍ ጥሎ መውጣቱን አስታውሰዋል:: ይህ ታዲያ የወያኔ አውቅላችኌለሁ ማለት ውጤት አልነበረም? እስዎን ብቻ የሚያወቅስ አይደለም ወራቤሳዎች ዛሬስ እየተመለሱ አይደል ? መጥኔ ለኦሮሞ ህዝብ ! መጥኔ ላገራችን:: እንግዲ እነሱም ስለ”ህገ መንግስት” ሊያሰለቹን አይደል?
አንቀጽ 39ን በግሌ አምንበታለሁ ብለዋል:: መልካም::መብትዎ ነው:: የዘነጉት ግን የሚሊዮን ህዝቦችን እጣ ፈንታ መወሰኛ መሆኑን ነው:: ይህ ክልል ብሎ ነገርን ያመጣው ጠንቅ ማንን በጀ? ኦሮሞ መሆንዎን አውቃለሁና ለኦሮሞ ህዝብ በጀ ወይ ብዬ ብጠይቅዎ ምን ይላሉ? መሬቱን የተቀማ ኦሮሞ:: እስር ቤት የታጎረው ኦሮሞ:: ቱባው ወያኔ ግትሩ ስየ አብረሃ እንደመሰክረው:: የተሰደደው:ባህር የበላው ኦሮሞ:: ለዚህ ህዝብ አንቀጽ 39ን ያስገኘሁልህ እኔ ነኝ ሲሉት አያሳዝንም? በስብሰባው ያስተናገደዎ ፈረንጅ ቶማስ ጀፈርሰን ብሎ እንደሸነገለዎ ልናገርዎ አልፈቅድም:: እርስዎ ያገሬ ሰው ነዎት:: ቶማስ ጀፈርሰን የአሜሪካ መንግስት መስራች ህግ አርቃቂ የነበር ነው። የውስጣችንን ውጥንቅጥ ለማያቅ ፈረንጅ ግልጽ ሊሆን አይችልም:: አዝናለሁ ዶክተር ነጋሶ ! ይህ ሙገሳ ለእርሶ አይሆንም:: ቶማስ ጀፈርሰን የገዛ አገሩ መገጠል እያለ አልዶለተም::
እኔ እንደ ህግ አርቃቂ አገር ወዳድ ምሁር የምወድልዎ የነበረው፡”ዛሬ ባዲስ እንጀምር:: ሁሉንም እንፈትሽ::እስካሁን የጠፋውን አይተን ያለ አንዳች ጫና ምን መተለም እንችላለን ?”ቢሉ ነበር:።በኔ እምነት ወደፊትም ይሆናል ብዬ እንደማምነው ያለውን ሽረን:የህዝቡን የውነት ተወካዮች ይዘን እንዴት ያለ ህገ መንግስት እናረቃለን ቢሉ ነበር:: አሁንም ጊዜ አለዎት። ማን ያውቃል የምሩ ህገመንግት ሲረቀቅ ወደፊት ውክልና ካገኙ ይመክሩ ይሆናል:: እስተዚያው ግን አእምሮአችንን እናሰራው::
ያ ሆዳሙ ፈረንጅ ትዝ ይሎታል? ስሞን በረክት ምሳ አበላኝ ያለው። እሱ የፈረኝጅ ወራቤሳ ነው ፡ መናጢ! ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በድገት መጥቃለች ያለው:: እርሶ በትንሹ ነው የተናገሩት። አጠገብዎ የነበረው ጆን ሀርቢሶን የኢትዮጵያን በደል ባለችው ጊዜ ቶሎ አቀረበው የድህነት መለኪያው እግርጌ እንዳለች: የመሬት ቅሚያንም አነሳው እግዜር ይስጠው:: እርስዎም ተዘጋጅተው መምጣት ነበረብዎ:: ናሽናል ዔንዳውመት ፎር ዲሞክራሲ የለገሰዎ የጥናት ጊዜ ብዙ ነበር::
ከዝግጅቱ ጊዜ ማነስም እንጂ አቢይ ጥያቄዎች ተነስተዋል:: አንቀጽ 39፡ 105፡ የስልጣን ገደብን ጨምሮ:: ሌላም በተለይ፡ የቡድን መብት ቀርቶ የየግለሰብ መብት ለምን አቢይ መወያያ አይሆንም ተብሎ የተጠየቀው የሚታወስ ነው:: አዝናለሁ ዶክተር ነጋሶ ! ለአንዱ ጥያቄ እንኴን የህገ መንግስት ምሁር መልስ አልነበረዎም። እርሶአንቀጽ 39 አርበኛ አድረገው ራስዎን ማቅረብዎን ነው ያዩት እንጂ አሁንም አነታራኪ መሆኑን አላስጨበጡም።ጆን ሀርቢሶን እንደገና ህገ መንግስቱ ህዝብ ላይ በጫና የመጣ መሆኑን የኤርትራ መገንጠል አሁንም “መራራ ኪኒን” መሆኑን ተናግአል:: ምሁር እንዲያ ነው ሁሉን አቅጣጫ ለማየት የሚሞክር:: ወደፊት እንዲህ ያለው የጥናት እድል ሲመጣ ለአዲሱ ትውልድ ይተላለፍልኝ ይበሉ። አደራ::
ሁላችንም ካለብን ምሁራዊ ስንፍና ተላቀን ችግራችንን ለመፍታት እንነሳ:: ኢትዮጵያን የዚ ቴክኖሎጂ አቀራርቦት የሚገሰግሰው ዓለም አካል ሆና እንድትጔዝ የሚያደርጋት፡ሰላም መደላደል የሚፈጥርላት ህገመንግስት እዴንት እንዲኖራት ማድረግ ይቻላል ብሎ በሰፊው ማሰቢያ ጊዜ ነው። ወያኔ ማክተሚያ ስለቀረበ ይህ ጊዜ እማይሰጥ ነው:: የተማረ ያልተማረ አይልም። የሁሉም ዜጋ ጉዳይ ነው:: በተለይ ወጣቱ በዚህ ርእስ በሰፊው መማር መወያየት አለበት:: ዜግነት አላፊነት ጋር ይመጣል:: ይህን አስበው ከነመለስ ተቧድነው ስለበደሉ ህዝብ አስቡ:: እያስተዋለን ነው:: እየታዘበን:: ደህና ሁኑ:: ከዘለፋ ይሰውርዎት::
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen