Netsanet: አስር የድረ-ገጽ አዘጋጆች ቴድሮስ አድሃኖም ውሸታቸውን እንዲያርሙ አሳሰቡ

Mittwoch, 11. März 2015

አስር የድረ-ገጽ አዘጋጆች ቴድሮስ አድሃኖም ውሸታቸውን እንዲያርሙ አሳሰቡ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ቁጥር አንድ የኢትዮጵያ ፒኖሾ” የሚል ስያሜ አግኝተዋል

ጋዜጣዊ መግለጫ
ዋሽንግተን ዲሲ፤ አስር የድረ-ገጽ አዘጋጆች በአንድነት በመሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በመንግስት መገናኛ ብዙሃን እና በፌስቡክ ገጻቸው የተናገሩትን አጸያፊ እና ሃላፊነት የጎደለው ውሸት እንዲያርሙ ጠይቀዋል። ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በመገናኛ ብዙሃን (ስለ) ታዳጊ ወጣት በሪቱ ጃለታ የተናገሩትን የ20 ሚልዮን ዶላር የፈጠራ ታሪክ እስካሁን ባለማረማቸውና ህዝብን ይቅርታ ባለመጠየቃቸው፣ የድረገጽ አዘጋጆቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን በአንድ ድምጽ “ቁጥር አንድ የኢትዮጵያ ፒኖሾ” የፈጠራ ገጸ-ባህርይ የሚል ስያሜ ሰጥተዋቸዋል።Ethiopian foreign minister
የአቡጊዳ፣ የአዲስ ቮይስ፣ የኢካድ ፎረም፣ የኢትዮፎረም፣ የኢትዮ ፍሪደም፣ የኢትዮ ሜድያ፣ የኢትዮጵያን ሪቪው፣ የቋጠሮ፣ የሳተናው እና የ ዘሃበሻ ድረ-ገጽ አዘጋጆች በጋራ በመሆን ይህንን አቋም የወሰዱት፣ ሚኒስትሩ በህዝብ ፊት በመቅረብ ነዋሪነትዋ በሜልቦርን ስለሆነው የ14 አመት ተማሪ ብሪቱ ጃለታ በተናገሩት ፍጹም ሃላፊነት የጎደለው ቅጥፈት የተነሳ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሳምንታት በፊት ከታዳጊ ወጣትዋ ጋር በቢሮአቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ “ነዋሪነቷ ሜልበርን ከተማ አውስትራልያ የሆነችው የ14 ዓመት ታዳጊ ወጣት በቅርቡ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳድራ 20 ሚልዮን የአውስትራልያ ዶላር ተሸላሚ ስትሆን፤ ያገኘችውን ገንዘብ በኢትዮጵያ ለልማት ለማዋል ወስናለች። በሪቱ በዚህ ዕድሜ ይህን ያህል ከፍተኛ ገንዘብ ለሃገር በማበርከት ተወዳዳሪ የሚገኝላት አይመስለኝም” ማለታቸው የሚታወስ ነው። ይህ መግለጫ ከእውነት የራቅ ነው። የተጠቀሰው ባደን ኮሌጅ መግለጫው ሃሰት እንደሆነ ታናግሯል። የሽልማቱን ገንዘብ ሰጡ የተባሉት ሮታሪ ተቋም እና የአውስትራሊያ መንግስት መግለጫው ሃሰት እንደሆነ እና ለጉዳዩ እንግዳ መሆናቸውን ገልጸዋል።
“ሚኒስትሩ በአስቸኳAይ ይህንን ሃላፊነት የጎደለውን መግለጫ እንዲያስተባብሉ እና ያለምንም ማንገራገር ሕዝቡን ይቅርታ እንዲጠይቁ እናሳስባለን።” ሲሉ አስሩ የድረ-ገጽ አዘጋጆች ጠይቀዋል።
ይህ መግለጫ ፍጹም ሃስት የሆነ ታሪክ እና ፈጠራ መሆኑ በመረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ሚኒስትሩ ጥፋቱን በታዳጊዋ ህጻን ላይ ማመካኘቱን ትተው ራሳቸው ሃላፊነቱን እንዲወስዱም የደረ-ገጽ አዘጋጆቹ አሳስበዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ባለፈው ቅዳሜ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ በለቀቁት ጽሁፍ፤ በሪቱ ጃለታን በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ መልኩ ለመኮነን ሞክረዋል። “እንደምታውቁት በሪቱ የ14 ዓመት ታዳጊ ናት። ህፃናትና ታደጊዎች የዋሆች እንደሆኑ ክፋት እንደሌላቸው ከኔ ጋር የምትስማሙ ይመስለኛል። በዚህ ምክንያትም ህፃናትና ታዳጊዎች የሚነግሩኝን ማመን እመርጣለሁ። ስህተትም ቢኖራቸው ከየዋህነት ካልሆነ ከክፋት አይመነጭም። ህፃናትን ማመን ስህተት ከሆነ መሳሳትን እመርጣለሁ። “ ብለዋል። ‘ለዚህ ተወዳዳሪ ላልተገኘለት ውሸት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ቁጥር አንድ የኢትዮጵያ ፒኖሾ” የሚለው ስም ይገባቸዋል!’ ሲሉ የድረ-ገጽ አዘጋጆቹ ተስማምተዋል።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen