Netsanet: መድረክ “በፌዴራሊዝም ” ጉዳይ እንዳይከራከር ታገደ

Donnerstag, 12. März 2015

መድረክ “በፌዴራሊዝም ” ጉዳይ እንዳይከራከር ታገደ

የኢህአዴግ ምርጫ ቦርድ እንደገለፀው በነገው ዕለት በቴለቪዥን የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ይጀመራል፡፡ የነገው ክርክር ሰብኣዊ መብትና መድብለ ፓርቲ የተመለከተ ሲሆን ነገ ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ተደርጎ ቀን ሙሉ ኢህአዴግ እማይጥመውን ንግግር በመቀስ ሲቆርጦው ከዋለ በኋለ ማታ ከ 2 ሰዓት ዜና በሁዋላ ይቀርባል ተብለዋል፡፡
በተያያዘ ዜና መድረክ በፌዴራሊዝም ላይ በሚደረግ ክርክር እናዳይከራከር ተከልክለዋል፡፡ ህዝብ ከህዝብ ጋር እያናቆረ ያለው አሸባሪው የኢሀአዴግ ፍረዳሊዝም እንዳንተቸውና አማራጭ ፌዴራሊዝማችን እንዳናቀርብ በጠበንጃ አምላኪዎች ታግደናል፡፡ በእውነቱ መጣም አሳዣኝ ነው፡፡ በዚህ ወሣኝ ርአስ ላይ እንዴት እንከለከላለን?
መድረክ እኔና ዶክተር መረራ ጉዲናን በፌዴራሊዝም ጉዳይ ላይ እንድንከራከር ወኩሎን ነበር፡፡ ሆኖም ግን ኢህአዴግ በኔ ሳንባ ከሚተነፍሱ ቅልብ ፓርቲዎች ጋር ብቻ ነው የምከራከረው ብሎ እምቢ በማለት ህገወጥነቱን ቀጥሎበታል፡፡ ኢህአዴግ ከክርክሩ የጨረገደን በክርክሩ እንደምንዘርረው ስላወቀ ነው፡፡ አምስት አመት ሙሉ ጠብቀን ለመድረክ የተሰጠው 6 ደቂቃ ብቻ ነው ግን ኢህአዴግ 6 ደቂቃዋም በጣም ስለፈራት ከለከለን፡፡ አጃኢብ!
ለማንኛውም ነገ ሰብኣዊ መብትና መድብለ ፓርቲ በሚል ዶክተር መረራና የመድረክ የወጣቶች ክንፍ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አብርሃም ሳልህ መድረክን ወክለው ይቀርባሉ፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen