ዚህን አባባል እውነትነት/ሐሰትነት ሊያረጋግጡልን የሚችሉት አቶ ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) በፌስቡክ ላይ አሉ፡፡ ነገር ግን አቶ ያሬድ “ኢህዴን እንደዚያ የሆነው እኔ ከወጣሁ በኋላ ነው” የሚል እይታ ነው ያላቸው፡፡
እኔ አቶ ስየ አብረሃም “ህወሐት የአንድ ሰው አምባገነናዊ ድርጅት የሆነው እኛ ተገፍተን ከወጣን በኋላ ነው” ዓይነት ነገር ሲጠርቁልን ነበር፡፡ አምባገነን የተባለው ሰውዬ አሁን ሞቷል፡፡ እና አሁን ያለው ህወሐት ምን ሊባል ነው?…. አቶ ስዬ “እኛ እንኳን ታሪክ ጦርነት መስራት እንችላለን” በማለት ሲያፈራሩ እንደነበረ የረሳነው መስሎአቸዋል እንበል እንዴ?
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳም “ኦፒዲኦ የተበላሸው እኔ ከድርጅቱ አመራር ጋር በ1993 ከተጣላሁ በኋላ ነው” የሚል አነጋገር ይደጋግማሉ፡፡ ወቼ ጉድ! ክቡር ዶ/ር ነጋሶ ሆይ! እርስዎ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚመረጡ የኢትዮጵያ ህዝብ ያወቀው ገና በታሕሳስ ወር 1987 ላይ ነበር እኮ! ይህም ምርጫው ከመካሄዱ ከአምስት ወራት በፊት መሆኑ ነው፡፡
እነዚህ የቀድሞ አውራዎች “ንስሐ ገብተናል! ከህዝቡ ጋር ወግነናል” ሲሉን ነበር፡፡ ህዝቡም እንደ ዜጋ የመኖር መብታቸውን ተቀብሎታል፡፡ ንስሐውን የእውነት ይሁን የውሸት ማጣራት የኛ ፈንታ አይደለም፡፡ ለራሳቸው ይያዙት፡፡ ይሁንና በየጊዜው የማይገባ ነገር እየለጣጠፉ ይነካኩንና “ዛሬም እንደ ድሮው ሳይሆኑ አይቀሩም” እያልን እንድንጠረጥራቸው ያደርጉናል፡፡
አቶ ያሬድ ናቸው ይህንን ሁሉ ያስለፈለፉኝ፡፡ አላህ ሂዳያ ይስጣቸውና!! በተለይ አቶ ያሬድ ያኔ የለመዱትን ሐቅን የመደበቅ አባዜ ዛሬ ለወጥ አድርገውት መጡ …. እና (አይ….ይቅር አቦ! ንዴት ጥሩ አይደለም፤ ስንረጋጋ ብንነጋገር ይሻላል…)
በነገራችን ላይ ኮብልለው ከወጡት የኢህአዴግ ሰዎች መካከል ከሞላ ጎደል ሐቅን ለመናገር ሲደፍር ያየነው አቶ ኤርሚያስ ለገሠን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ሁሉ አጭቤ ነው፡፡ አጭቤ!! የሌለ ተረት እየፈጠረ ነው ሊያሞኘን የሚፈልገው፡፡ ይህንን ሁሉ ሳይ “እንኳንም ፖለቲከኛ አልሆንኩኝ” እላለሁ፡፡
በነገራችን ላይ ኮብልለው ከወጡት የኢህአዴግ ሰዎች መካከል ከሞላ ጎደል ሐቅን ለመናገር ሲደፍር ያየነው አቶ ኤርሚያስ ለገሠን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ሁሉ አጭቤ ነው፡፡ አጭቤ!! የሌለ ተረት እየፈጠረ ነው ሊያሞኘን የሚፈልገው፡፡ ይህንን ሁሉ ሳይ “እንኳንም ፖለቲከኛ አልሆንኩኝ” እላለሁ፡፡
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen