Netsanet: 2014

Dienstag, 30. Dezember 2014

በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ የወያኔ አገልጋዮች ስም ዝርዝር

ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ንብረትና ቤት አልባ አድርጎ በአንጻሩ ደግሞ በውጭ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ በአገሩ ውስጥ ያለውን አፋኝና አምባገነን አገዛዝ እንዳይታገል ለማድረግ በርካታ የማታለያና የማደናገሪያ ዘዴዎችን ይጠቀማል። ከነዚህም ዘዴዎች አንዱ በውጭ የሚኖረውን (ዲያስፖራውን) አገር ውስጥ ካለው ወገኑ በሚነጠቀው ቦታ ላይ ቤት እንዲሰራና በዚህም ምክንያት የወያኔ ደጋፊና ተላላኪ እንዲሆን ማድረግ ነው። የዚህ የወያኔ መሠሪነት አብዛኛው በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የተገነዘበ ቢሆንም ጥቂቶችን ግን ከወያኔ ወጥመድ ውስጥ ከመግባት አላመለጡም። ከነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ በጭፍን ዘረኝነት ተለክፈው ለአገዛዙ ድጋፍ የሚሰጡ የአንድ አካባቢ ተወላጆች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ “ያባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ስግብግብነት ተነሳስተው ጥቅም አስክሯቸው የተሰለፉ ነው።

የወያኔ አላማ በዲያስፖራ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አገር ውስጥ ቤት ንብረት ካፈሩና ማንነታቸው ታውቆ ከተመዘገቡ ከተቃዋሚነት እራሳቸውን ያገላሉ፤ ከተቻለም ለወያኔ ወሬ ለቃቃሚ ይሆናሉ የሚል ነው። በእርግጥ ይህንን የሚያመላክቱ አንዳንዳ ተጨባጭ መረጃዎች አሉ። በውጭው ዓለም ተቃዋሚ የነበሩና ብዙ አስተዋጽኦ ሲያበረከቱ  የነበሩ ወገኖች በወያኔ ማታለያ ተጠልፈው አገር ቤት ገብተው አንዲት ዛኒጋባ ሲቀይሱ፣ በአንድ ጀንበር ተቃዋሚነታቸው ቀርቶ “ከለማበት የተጋባበት” እንደሚባለው ለወያኔ ጆሮ ጠቢነትና አለቅላቂነት አለእፍረትና አለይሉኝታ ሲያካሂዱ ይታያሉ። ወያኔ በከፍተኛ ደረጃ በጀትና የሰው ኃይል መድቦ “በከተሞች መልካም አስተዳደር አቅም ግንባታ ቢሮየሕዝብ ተሳርፎና ያልተማከለ አስተዳደር ማጠናከር መምሪያ የዲያስፖራ ተሳትፎ ኬዝ ቲም“ በሚል በዲያስፖራ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ያዘጋጀው የግለሰቦች የግል መረጃ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።  በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ የወያኔ አገልጋዮች ስም ዝርዝር http://www.ethiopianreview.com/amharic/wp-content/uploads/%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%88%88%E1%8B%AB%E1%8B%A9-%E1%8A%A0%E1%8C%88%E1%88%AE%E1%89%BD-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%8A%96%E1%88%A9-%E1%8B%A8%E1%8B%88%E1%8B%AB%E1%8A%94-%E1%8A%A0%E1%8C%88%E1%88%8D%E1%8C%8B%E1%8B%AE%E1%89%BD-%E1%88%B5%E1%88%9D-%E1%8B%9D%E1%88%AD%E1%8B%9D%E1%88%AD.pdf

ኢትዮጵያ ለወሲብ ንግድና ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር መነሻ አገር ሆናለች ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ


December 30, 2014 Leave a comment
የአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው የ2014 ሪፖርት ኢትዮጵያ ለግዳጅ ሥራ፣ ለወሲብ ንግድና ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የተዳረጉ ወንዶች፣ ሴቶች እና ሕፃናት መነሻ፤ በተወሰነ ደረጃም መዳረሻ አገር ናት ብሎአል።

አዲስ አበባ የሚገኘው ዋና የገበያ ማዕከል ከአፍሪካ ቀዳሚው የወሲብ ንግድ ቤቶች መገኛ ነው የሚለው ሪፖርቱ፣ ዕድሜያቸው እስከ 8 ዓመት የሚሆኑ ልጃገረዶች በነዚህ ቤቶች በሴተኛ አዳሪነት ተሰማርተዋል ይላል።

ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶች ከኢትዮጵያ ውጪም በተለይ በጂቡቲ፣ደቡብ ሱዳን እና በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ውስጥ በቤት ሠራተኝነት እና በሴተኛ አዳሪነት እንዲሰሩ እንደሚገደዱ፣ ኢትዮጵያውያን ወጣት ወንዶች ደግሞ ጂቡቲ ውስጥ በሱቅ ሰራተኝነት፣ በተላላኪነት፣ በቤት ሰራተኝነት፣ በስርቆት እና በጎዳና ላይ ልመና ለግዳጅ ሥራ ተዳርገዋል ብሎአል።

በርካታ ወጣቶች ሥራ ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሲሰደዱ ጂቡቲ፣ ግብጽ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን ወይም የመንን እንደመሸጋገሪያ ይጠቀማሉ የሚለው ሪፖርቱ፣አንዳንዶቹ ሊሄዱ ካሰቡበት አገር ሳይደርሱ እንደመሸጋገሪያነት ባረፉበት አገር ተይዘው ለብዝበዛ፣ለእስራት፣ለግዳጅ ስራ እና ለመታገት ይዳረጋሉ ብሎአል።

በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት በቤት ሰራተኝነት የተሰማሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች አካላዊ እና ወሲባዊ ጥቃት፣ ደሞዝ ክልከላ፣ እንቅልፍ መነፈግ፣ የፓስፖርት መያዝ፣ በቤት ውስጥ መታገት እና ግድያን ጨምሮ አስከፊ ጥቃቶች እንደሚደርስባቸው፣ በአንዳንድ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያውያን ሴቶች ስራ ፍለጋ ከአገር ከወጡ በኋላ፣ በወሲብ ንግድ ቤቶች፣ በማዕድን ማውጫ ቦታዎች፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚገኙ ነዳጅ ዘይት ማውጫ አካባቢዎች ለወሲብ ንግድ ብዝበዛ ይዳረጋሉ ብሎአል።

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀን እስከ 1500 የሚደርሱ ኢትዮጵያውን በሕጋዊ መንገድ ከአገር እንደሚወጡ ቢገልጽም፣ ይህ ቁጥር ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ከሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ30 እስከ 40 በመቶ ብቻ የሚወክል ብሎአል። ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆኑት ሠራተኞች በሕገ ወጥ ደላሎች አማካኝነት ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወይንም ስደት እንደሚዳረጉ ጠቅሷል።

መንግስት በአስቀጣሪ ኤጀንሲዎች ላይ ክልከላ ቢጥልም ክልከላውን ተከትሎ በሱዳን በኩል የሚደረግ ሕገወጥ የሰራተኞች ፍልሰት መጨመሩን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት ጠቁሟል። እ.ኤ.አ. ከሕዳር 2013 ጀምሮ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ከ163 ሺ 000 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ከአገሩ ያስወጣ ሲሆን ከነዚህም መካከል ከ94 ሺ 000 የሚበልጡት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ የተሰማሩ ወንዶች፤ ከ8 ሺ 000 የሚልቁት ደግሞ በእረኝነት እና በቤት ሰራተኝነት የተቀጠሩ ሕጻናት ናቸው ብሎአል።

መንግሥት ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማስወገድ የተቀመጡትን ዝቅተኛ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ባያሟላም፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል የሚለው ሪፖርቱ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 106 ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የፈጸሙ ወንጀለኞች ሕግ ፊት ቀርበው እንዲቀጡ ያደረገ ሲሆን፤ከዓለምአቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበርም ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች መጠለያ እና የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ አድርጓል ሲል አትቷል።

መንግስት የሕገወጥ ዝውውር ሰለባ የሆኑትን ጨምሮ ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከሌሎችም አገራት የተባረሩ ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የማመቻቸት ስራ ቢሰራም፣ የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ ሳያደርግ የውጭ አገር ድርጅቶች ይወጡት በማለት ሃላፊነቱን ለእነሱ መተውን ገልጿል።

መንግስት ውጭ አገር በሚገኙ ዲፕሎማቲክ ሚሽኖች የሰራተኛ ጉዳዮችን የሚመለከቱ አታሼዎችን አለመመደቡ፤በኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች በሚሰጡ የዜጎች ደህንነት አገልግሎቶች ላይም ማሻሻያ አለማድረጉም ተጠቅሷል፡፡

መንግስት የሕጻናት የወሲብ ንግድን እና ሌሎች በአገር ውስጥ የሚፈጸሙ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀሎችን በሕግ ማስከበር፣ ከለላ በመስጠት እና በመከላከል በኩል በቂ ሥራ አልተሰራም በሚል ስቴት ዲፓርመንት ትችት አቅርቧል።

Sonntag, 28. Dezember 2014

እሺ አሁንስ ባህር ዳር ላይ ደግሞ ወገኖቼን ለምን ገደላችሗቸው

December 27, 2014
ለዚህ ደርግ ኢሰፓ ዜጎችን አይደለም ዝነብ አይገልም

ዳዊት ዳባ

የባህር ዳር ህዝብ ይህን ቦታ እጅግ ለረጅም አመታት ለአምልኮ ስንጠቀምበት የነበረ ነው። ለባለ ሀብት መሰጠቱና ለሌላ አገልግሎት እንዲውል መወሰኑ ትክክል አይደለም ብሎ ቅሬታውን ሊያሰማ አደባባይ ወጣ። ይህ ለእምነቱ የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል ቀናዊ የሆነ በአገሬ ጉዳይና በኑሮዬ እሚንት የምታህል መብት አለኝ ብሉ የሚያስብ የየትም አገር ዜጋ ሊያደረገው የሚችል ነው። በእውን ይህን ማድረግ የሚከለከል ወይ ማድረጉስ ወንጀል የሚደረግበት ህዘብ በአለም ላይ አለ ወይ?። እኔ እይመስለኝም።
Bahir Dar protest
በባህርዳር የተቃውሞ ሰልፍ በወያኔ ታጣቂዎች ድብደባ ከተፈጸመባቸው ውስጥ አንዱ
በዋናነት ቅሬታቸውን ሰልፍ ወጥተው ማሰማታቸው የህግ አግባብ ያለው ነው። ህዝብ ይህን ማድረጉ ተፈጥራዊም ህገ መንግስታዊም እምነታዊም መብት መሆኑ ደምቆ ይሰመረብት። ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ቅሬታቸውን ማቅረባቸውንም እንዲሁ።
ይህም ሆና በባህር ዳር ላይ የሆነው እጅግ እጅግ በጣም ቀላል ነገር ነበር። መገድል መደብደብ ማዋከብ ውስጥ ሳይገባ ይህን የህዝብ ቅሬታ ማስተናገድ በቀላሉ የሚቻልባቸው መንገዶች ነበሩ።የሚያዳምጥ አካል በመላክ ቅሬታውን ማዳመጥን ብቻ ነበር እኮ የሚፈልገው። የህዝቡ ቅሬታ እውነታ ከሌለው እውነታውን ማስረዳት። የህዝቡ ቅሬታ እውነትነት ኖሮት ቦታው ለሌላ አገልግሎት ተሰጥቶ ከሆነ ውሳኔው የተላለፈበትን አግባብና በልዋጭ ህዝብ አምልኮውን የሚፈፅምበት ቦታ ተዘጋጅቶ ከሆነ ይህንን መንገርና በቀላሉ ሰላማዊ ፍፃሜ መስራት ይቻል ነበር። ሌላ ሶስተኛ አካል ከጀርባ ህዝብን አሳስቷል። ነጭ የገዳዬች ምክንያት ነው። ካልሆነ ከጨፈጨፍክ በሗላ ሳይሆን እዛው ሰልፉ ላይ አሳስተዋችሁ ነው። የምታቀርቡት ቅሬታ ምንም መሰረት የሌለው ነው። በማለት የተፈጠረውን አለመግባባት ማጥራት አይቻልም ነበር ወይ?። ቅሬታው አግባብ ኖሮት ውሳኔው የተላለፈበትን አግባብ እዛው መንገሩ ጥሩ አይሆንም ተብሎ ከታሰበም። ቅሬታውን አድምጠናል።
መልሳችንን በዚህ ቀን በዚህ መንገድ እንሰጣለን ማለትንስ ማንን ገደለ። አዎ ይህን በማድረግ በሰለጠነው መንገድ መጨረስ ስትችሉ ፈጇችሗቸው።
ሁላችንም ማወቅ ያለብን እንደሁሌው ይህ እጅግ ቀላል ነግር በዚህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታ የተፈፀመው አምጠንም ሰበብ ልንወልድልት በማይቻለን ስልጣን ላይ ያሉት የትግሬ ወያኔዎች በመሆናቸው ነው። አንድነት፤ ሰማያዊ፤ አዎ ኢሰፓም ብቻ የትኛውም አካል ስልጣን ላይ ቢሆን ኖሮ የሚያደርገው ካላይ ያልኩትን ነበር።
በእርግጠኛነት የምናገረው ለዚህ ቀላል ነግር የሰው ልጅ ለዛውም ዜጋ አይደለም ዝንብ አይሞትም ነበር። እናንተ ግን በምታውቁትና ሁሌም የዚህ አይነት የህዝብ ቅሬታን በምታስተናግዱበት መፍጀት በእድሜ የጠገቡ አሮጊቶችንና ለአካለ ስንኩላን እንኳ ሳትራሩ ዘግናኝ ወንጀል በድጋሚ ፈፀማችሁ። ግን ለምን?። ለምን ለሰው ለጅ ለዛውም ለወገናችሁ ሂወት የምትሰጡት ክብር እዚህ ደረጃ ወረደ?። ህዝብን ማሸበር እንዴት ነው እንደዚህ ደስታን እየሰጣችሁ ያለው?። ጎበዝ ግርም የሚል ነገር እኮ ነው የገጠመን።
ይህ በመፍጀት የሚነሱ የመብት ጥያቄዎችንና ቀላል ቅሬታዎችን ሁሉ መፍታት ለሀያ ሶስት አመት ሙሉ በተደጋጋሚ ሲፈፀሙ የነበረ መሆኑን ልብ እንበል። ሚሊዬኖችን ቀጥቅጠውበታል። በመቶ ሺዎች ገድለውበታል። በመቶ ሺ ዎች በየማጎርያው የመከራ ሂወት እንዲገፉበት አድርገዋል። ሚሊዬኖችን አሰድደዋል። ብዙዎችን ያለወላጅ አስቀርተዋል። ይህ ግፍ የተፈፀመባቸው ብዙዎቹ ይህን አይነቱን በሽታ ዝም ስለተባለ ማቆሚያ የሌለው መሆኑን በጠዋቱ አውቀው አቁሙ ስላሉ መሆኑን ደግሞ አንዘንጋ።
ዛሬም የሆነ አይነት “መንግስት” አድራጋችሗቸው ህግና ስርአትን ከማስከበር አኳያ፤ እንዲሁም በአደባባይ ስሜትን ለመግለፅ ከማሳወቅ በሉት ከማስፈቀድ የህግ አግባብ አኳያ እያያችሁ ትርጉም እንዲሰጣችሁ እየጣራችሁ ያላችሁ ትኖራላችሁ። እውነት እውነት እላችሗለው በጣሙን ተሳስታችሗል። እሩቅ ቦታ ሳልሄድ ሀዘን ደስታ ንዴት የስሜት ጉዳዬች ናቸው። ሁሌ በቀጠሮ የምናደርጋቸው አይደሉም። የሄን ደግሞ እኔ ስላልኩ አይደለም። ወያኔዎችም ያውቃሉ። ብሄራዊ ቡድናች ሌላ ጊዜ ደግሞ እሯጮቻችን አሸነፉ ብሎ ይህው ህዝብ በብዙ ቁጥር በደስታ ስሜት ብዙ ጊዜ ሳያስፈቅድ አደባባይ ወጥቷል። ገደሉት?። አልገደሉትም። ጦርነት አሸነፍን ባድሜ ለኛ ተወሰነ ብሎ ደስታውን ለመግለፅ ህዝብ አደባባይ በብዙ ቁጥር ወጥቶ ነበር። ፈጅት ፈፀሙበት?። አልፈፅሙም። መለስ ሞተ ብለው ሀዘኑን ሊገለፅ ነው ብለው ያለ ምንም ፍቃድ አሁንም አደባባይ ያወጡትን ህዝብ ፈጁት?። አልፈጁትም። እነሱ ደስታቸውን፤ ዝክራቸውንና ስኬታቸውን ሊነግሩን የበዛውን ጊዜ አደባባዩን የሚጠቀሙና ሲሰበሰቡ የሚውሉ ናቸው። እያስፈቀዱ ስለመሆኑ የምታውቁት ነገር አለ?። አስፈቀዱ ወይ ተከለከሉስ ሲባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?። ወይ እዚህ ቦታ መሰብሰብ ወይ መሰለፍ አትችሉም ተባሉስ ሲባልስ?። ሲቀሰቅሱ አባላት ታሰሩባቸውስ ሲባል ሰምታችሗል?። አውቃለው ጥያቄዬ የሞኝ እንደሚመስል። የማነሳው ግን ህጋዊነት ላይ ጠንካራ እምነት አለችሁና እነሱ ከህግ በላይ ናቸው እንደማትሉ ገምቼ ነው።
ወያኔንና ወንጀሎቹንና ጥፋቶቹን በሚመለከት ተሳስታችሗል ስላልኩ አይክፋችሁ። ይህን ለጉድ የገነነብንን ድርጅት በሚመለከት ማንም ሁሌ በሁሉ ነገር ትክክል ሆኖ አያውቅም። ሁሌ ትክክል መሆንም ለማንም ቀላል አልሆነም። በዙ ጊዜ የህዝብ ስህተተኛነት ከጨዋነትና አርቆ ከማሰብም እንደሚመጣም አሳምሬ አውቃለው። ደጋፊዎቹን እንተዋቸውና ወያኔዎችን በብዙ ድምር ምክንያቶች መሰረት አድርጎ በጭራሽ የማይፈይድና ጎጂ ቡድን ነው። ለመልካም በቶሎ መጥፋት አለበት ብለን ያሰመርን ብዙዎች አለን። በሌላ ወገን ደግሞ በእምነቱ ለመቆየት የሚያያቸውንና የሚሰማቸውን አስገራሚ፤ዘግናኝ ጥፋቶችና ወንጀሎችን በሙሉ በሚቻለው ሁሉ አመክንዮ ሊሰራባቸው፤ትርጉም እንዲሰጡት ሲጥር ሲጥር የሚኖር አለ። ምክንያታዊ ለመሆን ከእለት እለት እየከበደውና እጅጉኑ እየተቸገረ ያለ ቢሆንም ተስፋው ፈፅሞ ያለተሟጠጠ ወይ እንዳይሟጠጥ እየጣረ ነው። ይህ ክፍል ብዛቱ ቀላል የማይባል እንደሆነም ይታወቃል። ወያኔዎችን በሚመለከት ሁላችንም በሁሉ ነገር ሁሌ ትክክል ለመሆን ይከብደናል ስል ግን በሁሉም ወገን ያለነው ስህተት ስለምንሰራ ነው። የኔን በሰሞኑ የተገለፀልኝን ደደብ የነበረ ስህተት ልንገራችሁ።
በጠኔ ለሚሰቃይና ልጆቹን መመገብ ለቸገረው ብዙ ሚሊዬን ህዝብ እርቦናል ሲላቸው ጠግበሀል ብለው ሲከራከሩት እሰማለው። አንዷለም እስክንድርና፤ ዞን ዘጠኞችን አሸባሪ ስለሆኑ ነው ብለው ሲከራከሩ እሰማለው። ቦንብ አፈንድተው ገድለው እነንትና ናቸው ብለው ሲከራከሩን እሰማለው። ቤተሰቦቻችንን ሰብስበው ልጆቻችሁን አሁን እንገላለን ወይ ልንገላቸው አምሮናል ሲሉና ሲደነፉ እሰማለው። እነዚህ እንደው ለምሳሌ ነው ያቀረብኳቸው። ሁሌና ሁሉ ነገራቸው አስገራሚ ድርቅና ያለበት፤ አሳማኝና አግባብ ያለው እንዲመስል እንኳ ቅንጣት ታክል የማይጨነቁበት እንደሆነ አውቃለው። የበዛ ድፍረትም አይባልም ጥጋብ ያለበቻው መሆኑን አውቃለው። በዚህ ደረጃ ነው እየተረዳሗቸው ነው እንግዲህ። እንደዚህ የሚያደርጉት ለምንድን ነው?። ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ስሞክር የተሳሳትኩት።
የሚመስለኝ የነበረው ከጠቅላላ የመሀበረባችን ግንዛቤ፤ የድህነቱ ደረጃ፤ የበዛው ዜጋ ከነሱ ወገን የሚቀርበውን መረጃ ብቻ ስለሚያገኝ፤ ያልቆረጠለትና እንዲቆርጥለት የማይፈልገው ዜጋ ገና ብዙ ቁጥር ያለው ስለሆነ። ምንም ብንለው ሀሳቡን የገዛዋል ከሚል ነው አይነት ምክንያቶችን እደረድር ነበር። የሚመስለኝ የነበረው እነዚህንና የመሳሰሉ ነገሮች በጥልቅ አስበው፤ አይተውትና አስልተው፤ ሌሎች መንገዶች መኖራቸውን ቢያውቁም ላሁን መፍጀቱ መቀጥቀጡና ማሰሩ ይሻላል፤ ያዋጣልም፤ ሰርቷልም ብለው በማወቅ የሚያደርጉት ነበር የሚመስለኝ። ስህተቴን ያሳየኝ በሰሞኑ በስዊድን ዜጎች ላይ ያደረጉት የመግደል ሙከራና እንግሊዛዊ ዜግነት ያለውን ግለሰብ መግደላቸው ነው። ለምን የነዚህ አገር ዜጎች እንደተመረጡ ማወቁ አልከበደኝም። ለምን መግደሉን መረጡ ለሚለው ጥያቄ ግን ከዚህ በፊት የምደረደርው ምክንያቶች አንዳቸውም በጭራሽ እንደማይሆኑ ተረዳው። እስከዛሬም ስህተቴ አለማወቅ ብቻ ሳይሆን እውነቱን ለማመን አለመፈለግ [Denial] እንደነበረበትም አወኩ። ምን ላድርግ ስልጣን ላይ ያለን አካል በዚህ ደረጃ ለማወቅ የሚያስፈራ ነገር አለው።
ለማንኛውም ይህን በሽታ ዝም ብለን እንዲቀጥል አናድርገው። በጭራሽ አይቆምም። በአንክሮ ላጤነው በፈጠነ ሁኔታ እየጨመረ እየባሰበት እየሄደ ነው። ብዙ ልናደርጋቸው የምንችላቸው ነገሮች አሉ። ልናደርግ የምንችለውን የምር አድርገን ልናስብበት ግን እንጀምር። ላሁኑ የተቃውሞ ሰልፎች ታቅደዋል እንቀላቀል።
ሁላችንም ልናደረገው የምንችላቸው ቀላል የሆኑ ነገሮች ደግሞ ብዙ አሉ። እነዚህን አንዳኗም ሳናስቀር ሁላችንም ዛሬ ማድረግ እንጀምር። አሁን ለምሳሌ እድሜያችሁ ለመምረጥ የደረሳችሁ በሙሉ ማድረግ የምንችለው ስለሆነ እባካችሁ ሄደን የመምርጫ ካርዳችንን አሁኑኑ እንውሰድ። የተለያየ አመለካካት ምርጫው ላይ ሊኖረን ይችላል። ቅንጦት ቢኖርበትም ይህ ችግር አይደለም። ልዩነቱ ላይ መጨቃጨቁ ይቀጥል። ማወቅ ያለብን አገዛዙ ምርጫ አለ፡፤ ውጡና ምረጡ ብሎን ይህን ማድረጋችን ደግሞ የሚረብሸውና የሚያስጨንቀው መሆኑን ነው። ደግሞ ፍራቻው ምክንያታዊም ትክክልም ነው። ሁላችንም ከተመዘገብን ምርጫ የሚባለው ነገር እራሱ ቀርቷል ሊሉ ወይ ካርድ ሊያወጣ የተሰለፈ ህዘብ ላይ ደግሞ ልተወው። ብቻ ትግል ብለን ካደረግነው ትግል የማይሆን ምንም እስከጭራሹ ምንም ነገር የለም። እስቲ ነገ ፖሊሱንም፤ ወታደሩንም፤ ደህንነቱንና ካድሬዎችን በተለየ ሁኔታ ሞቅ አድረገን ፈገግታ መስጠትና ሰላም ማለት ሁላችንም እንጀምር። ድርጊታችንን ትግል ነው እንበለው። በእርግጠኛነት በነጋታው መሳቅ ከአሸባሪነት ጋር ተያይዞ በኢቲሺ ሲተነትኑበት ትሰማላችሁ። ቆያይቶ ደግሞ ማግጠጥ ይባልና ህገ መንግስትን በመናድ የሚል ህግ ተጠቅሶበት እስር ቤት የሚገባ ይኖራል። ብቻ ዝም አንበል። በሆነ መንገድ በግፍ ለገደሏቸው ወገኖቻችን መቆርቆራችንን እናሳይ። ላሁኑ እንጠራራ፤ እንሰባሰብ፤እንቀሳቀስ ሄደን ከርዳችንን በእጃችን እናስገባ። የተቃውሞ ሰልፎችን በገፍ ወጥተን እንቀላቀል።
የሞቱትን ነብስ ይማር። መፅናናቱንና ጥንካሬውን ለሁላችንም ይስጠን።

Samstag, 27. Dezember 2014

ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ የጀመርነው የጋራ ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል!! በ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› የሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሠጠ መግለጫ፤

ትብብራችን ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ያወጣውን የመጀመሪያ ዙር ፕሮግራም አጠናቆ ወደ ሁለተኛው ዙር ሲሸጋገር ከሁሉ በማስቀደም የአንደኛው ዙር ዕቅዳችን ተግባራት ክንዋኔ ከዓላማችን ጎን ቆማችሁ በተለያየ መንገድ ለደገፋችሁን በአገር ቤትና በውጪ አገር ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናችንን፣ በአንጻሩ ዕቅዳችን ከዳር እንዳይደርስ ህገመንግስታዊ መብታችንን በመጨፍለቅ ጉዞኣችንን ለማደናቀፍ የተቻላችሁን ህገወጥ የቢሮክራሲ መሰናክልና ለኢትዮጵያዊ ሠላማዊ ዜጋ ቀርቶ ለጠላት የማይገባ ኃይል በመጠቀም የመብት አፈና ለፈጸማችሁ የመንግሥት አካላት ሁሉ ወደ ኅሊናችሁ እንድትመለሱ ጥሪ በማቅረብ ነው፡፡ በተጨማሪ ለሁሉም ወገን የያዝነው ትግል የአገርና የህዝብ፣ተጠቃሚውም ሁላችንም/ሁሉም ዜጎች/ና የሁላችንም የጋራ አገራችን፣ለጉዞኣችን የመረጥነው መንገድ ሠላማዊና ህገመንግሥታዊ ብቻና ብቻ፣መጓጓዣችን ዲሞክራሲያዊ ምርጫ፣ መድረሻችን መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ እንዲሁም በጉዞኣችን ላይ የቱንም ያህል አረመኔያዊ የኃይል እርምጃ ይወሰድብን፣ ትግሉ የቱንም ዓይነት ዋጋና መስዋዕትነት ይጠይቅ ከጅምሩ ያለመስዋዕትነት ድል የለም ብለን ተነስተናልና ከያዝነው ዓላማ ኢንች የማናፈገፍግና ለቃላችን በጽናት የምንቆም መሆኑን ዳግም በማረጋገጥ ነው፡፡
ትብብራችን የመግባቢያ ሰነዳችንና የጥናት ሪፖርታችንን እንዲሁም ከመጀመሪያው ዙር ያገኘውን ተሞክሮ በሠረት በማድረግ ይህን የሁለተኛ ዙር የሁለት ወር ዕቅድ (ከታህሳስ 16 እስከ የካቲት 15 /2007) አውጥቶ በቀዳሚነት ለዋነኛ ባለቤቶቹና ፈጻሚዎቹ ኢትዮጵያዊያን ሲያቀርብ እንደመጀመሪያው ዙር ከጎኑ እንደሚቆሙ ሙሉ እምነት በማሳደር፣በእኛ በኩል ከፊት ቆመን ትግሉን ለመምራት ያለንን ዝግጁነትና ቁርጠኝነት ለዚህም የገባነውን ቃል በማደስ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ‹‹በየትም የዓለማችን ክፍል አምባገነንነት የህዝቦችን የተባበረ የዲሞክራሲ ጥያቄ በኃይል አፍኖ በጨቋኝነት የዘለቀበት ታሪክ አልተመዘገበም›› ማለታችንን በማስታወስ ነው፡፡
ይህ ዕቅድ የመጀመሪያው ዙር ቀጣይ እንደመሆኑ ዓላማችንም የምርጫ ሁኔታዎች ባልተሟሉበትና የመራጩ ህዝብ ነጻነት በሌለበት ስለምርጫ መናገር አስቸጋሪ ነው፣ እነዚህ በሌሉበት አማራጭ የምርጫ ኃሳቦች በህዝብ ውስጥ ሊንሸራሸሩም ሆነ አማራጭ ኃሳባችንን ከህዝብ ማድረስ አይቻልም፣ሚናችንም የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው አማራጭ ሆኖ መቅረብ ሣይሆን የህወኃት/ኢህአዴግ አጃቢነትና የሀገር ሃብት በአላስፈላጊ መንገድ የማባከን ሥራ ተባባሪነት የዘለለ አይሆንም ከሚል የመነጨ ነው፡፡ ደጋግመን እንደገለጽነው ነጻነት በሌለበት ያለንበት ተጨባጭ ሁኔታ ምርጫ ቧልት ነው፡፡
በመሆኑም የዚህ ዙር ዓላማችንም ‹‹ ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የጀመርነውን እንቅስቃሴ አጠናክሮና አስፍቶ በመቀጠል ለነጻ ፣ፍትሃዊ፣ተኣማኒ፣አሳታፊ….በአጠቃላይም ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ለህዝብ ተደራሽ በመሆን በህዝብ (የተለያዩ የህዝብ ክፍሎችን፣ አደረጃጀቶችንና ዜጎችን በማካተት) የነቃ ተሳትፎ ተጽዕኖ በማሳረፍ በምርጫ ሂደቱና አተገባበሩ ላይ ያነሳናቸው ጥያቄዎች እንዲመለሱ ማድረግና ከዚህ ጎን ለጎን በቀጣዩ ምርጫ (2007) ተቃውሞ ጎራው በአጠቃላይ የትብብሩ አባላት በተለይ ድምጽ እንዳይሻሙ /የመራጩ ህዝብ ድምጽ እንዳይከፋፈል/ የሚያስችል ስልት በመቀየስ ከመራጩ ህዝብ ማድረስ ነው፡፡
በዚህ ላይ በመመስረት ትብብሩ በዚህ ሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ዕቅዱ እንደባለፈው ተደጋጋፊ፣ ተመጋጋቢና ተከታታይ ሦስት ዋና ዋና ተግባራትና በሥራቸው አስራ አራት ዝርዝር ተግባራት አካቷል፡፡ እነዚህ በትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ጥልቅና ዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸው የጸደቁ ዋና ዋና ተግባራትም፡-
1. የአባላትና የትብብሩ አቅም ግንባታ፡- የትብብሩን አባላት አብሮነት ማጠናከርና የጋራ ዓላማውን የማስፈጸም አቅም ማጎልበት፤ 
2. የህዝብ ግንኙነት ተግባራት፡- የህዝብ ተደራሽነት ማስፋትና ዓላማ ማስተዋወቅ፣
3. የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች ማመቻቸት፡- በአዲስ አበባና የተመረጡ ከተሞች አራት የአዳራሽ/አደባባይ የህዝብ ውይይት ፤በአዲስ አበባና በተመረጡ አስራ አምስት የክልል ከተሞች በተመሳሳይ ቀንና ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ፤ የሚያጠቃልሉ ናቸው፡፡ 
4. 
አስተባባሪ ኮሚቴው ተግባራቱን በጊዜ ሠለዳ በማስቀመጥ ለነዚህ ተግባራት ማስፈጸሚያ የብር 1,215, 000.00 (አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ ) በጀት አጽድቋል፡፡
እዚህ ላይ ይህን ዕቅድ ስናወጣ መንግሥት/ጠቅላይ ሚ/ሩ/ ከቅርብ ቀን በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ‹‹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መንግሥትን መገዳደር አይችሉም›› የሚል ኃሳብ ያዘለ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ማድመጣችንን፤ይህ መልዕክት የማደናገሪያና ማደናበሪያ ፕሮፖጋንዳ ስልትም ይሁን የተቃዋሚዎችን ዓላማና የመኖር ትርጉም የመጨፍለቅ ግልጽ መልዕክት ቢሆን እኛ የተያያዝነው ህገመንግሥታዊ መብታችንና የዜግነት ክብራችንን የማስከበር ሠላማዊና ህጋዊ ትግል በመሆኑ ማስፈራሪያውም ሆነ ማስጠንቀቂያው ህገመንግሥታዊ አይደለምና ህገወጥ ነው አይመለከተንም፤በሚል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡
በመጨረሻም ለተያያዝነው ሠላማዊና ህገመንግሥታዊ የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትግል፡-
1ኛ/ የጉዳዩ ቀዳሚና ዋነኛ ባለቤት የሆናችሁ ኢትዮጵያዊያን ይህን አምባገነናዊ ሥርዓት በሠላማዊ ትግል አስገድደን ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ራሱን እንዲያዘጋጅ የነቃ ተሳትፎ በማድረግና ሁለንተናዊ ድጋፍ በማቅረብ ከጎናችን እንድትቆሙ፣ በተለይ በውጪ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ትብብሩ ለትግሉ ተገቢውን አቅም እንዲገነባ በጀቱን ለመሸፈን ወቅታዊ የፋይናንስ ድጋፍ እንድታደርጉ፤
2ኛ/ በአገራችን የሚደረጉ ምርጫዎች ዲሞክራሲያዊ እንዲሆኑና ከማንኛውም ፓርቲ ተጽዕኖ ነጻ ሆኖ ለማስፈጸም በህገ መንግሥቱ ሥልጣኑ የተሠጣችሁ፣ ኃላፊነቱ የተጣለባችሁ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አመራርና አስፈጻሚ ባለሥልጣናት ከገዢው ፓርቲ ወገኝተኝነት እንድትላቀቁና እንደ ተቋሙ መሪና ዜጋ ራሳችሁን ከትውልድ ባለዕዳነትና ከታሪክ ተጠያቂነትና ተወቃሽነት ነጻ እንድታወጡ፤
3ኛ/ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም የመግባቢ ሰነዱና የጥናቱ ሪፖርት ባለቤቶች የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የሚጠይቀውና የተያያዝነው ትግል ከፓርቲ መሪዎች የግል ፍላጎትና ከፓርቲ ጥቅም በእጅጉ የላቀ በመሆኑ ለአገርና ህዝብ ቅድሚያ በመስጠት ተቃዋሚ ጎራው ባለፉት ምርጫዎች ሁሉ በመከፋፈልና የህዝብን ድምጽ በመበታተን ሚናው ከምርጫ አጃቢነት ያላለፈ በመሆኑ ይህን ‹‹በቃ›› የማለት ወቅቱ ነገ ሳይሆን ዛሬ ስለሆነ ከ‹‹እናቴ መቀነት ጠለፈኝ›› ምክንያት ወጥታችሁ ለዚህ ዓላማ በጋራ ለመቆም ትብብሩን ያለቅድመ ሁኔታ እንዲቀላቀሉ፤ 
4ኛ/ገዢው ፓርቲ/መንግሥት ከተያያዘው በአፈና ‹‹ለብቻ በመሮጥ›› አሸናፊ ነኝ በሚል ሥላጣን የማስጠበቅ ኢህገመንግሥታዊ አካሄድ ታርሞ የአገርና ህዝብ ጉዳይ ከሥልጣን ማስጠበቅ በላይና የኃይል እርምጃና አፈና ሥልጣን የማራዘም እንጂ የህዝብን የለውጥ ፍላጎትም ሆነ ለውጥን የማስቀረት አቅምና ኃይል የሌለው መሆኑን ከዓለም ታሪክና ከቅርብ ጊዜ የጎረቤት አገሮች ተሞክሮ እንዲማርና ራሱን ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲያዘጋጅ፤ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ያለመስዋዕትነት ድል የለም፤ የጋራ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ታህሳስ 17/2007 ዓ.ም! አበባ!

Freitag, 26. Dezember 2014

የህወሃት ምርጫ የህዝብ መከራ!

ህወሃቶች እኛ ከሌለን ይህችን አገር እንበትናታለን፤ ይህችን አገር የምንሰብር እኛ የምንጠግን እኛ እያሉ እንደሚያሟርቱ ሰምተናል። እኛ የቀረፅነው ፖሊስ ከሚቀየር ሞታችንን እንመርጣለን እያሉ ማቅራራታቸውም ከህዝብ የተሰወረ ነገር አይደለም። የህወሃት ፖሊሲ የሚቀየረው በመቃብርችን ላይ ነው የሚል የማይናወፅ አቋማቸው መቼም ቢሆን በሠለጠነ መንገድ በውይይትና በድርድር እንደማይቀየር ደጋግመው አሳይተውናል። ህወሃቶችን በሠለጠነ መንገድ ተደራድሮ እና ሰጥቶ በመቀበል መርህ ለለውጥ አዘጋጃለሁ ማለት ከእባብ የእርግብ እንቁላል እንደመመኘት ያህል ነው። ከእባብ የእርግብን ዘር የሚጠብቅ ማን ነው?
እንግዲህ ህወሃቶች ይህን የመሰለ የከረረ አቋም ይዘው ምርጫ ለምን ያደርጋሉ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል። ይሄ ህወሃቶች ለኢትዮጵያና ለህዝቧ ራዕይ የሌላቸው ከመሆን የሚመነጭ ነው። ድርጅቱ ራዕይ አልባ የሆነው ደግሞ በህወሃት ውስጥ የተሰባሰቡ ግለሰቦች ራዕይ አልባ በመሆናቸው ነው። ህወሃቶች የሚኖሩለትም ሆነ የሚሞቱለት ቁም ነገር ከመብልና መጠጥ የዘለለ አይደለም። ህወሃቶች ራዕይ ቢኖራቸው ኑሮ በታሪክ የሚያስወቅሳቸውንና የህዝቡን ፍቅር የሚያሳጣቸውን እኩይ ተግባራት ባልፈፀሙ ነበር። ራዕይ የሌላቸው በመሆኑ ለሚፈፅሙት ወንጀል ሁሉ ገደብ እንዳይኖራቸው ሆኑ። ራዕይ ያለው ሰውም ሆነ ድርጅት እኔ ብቻ አይልም። ራዕይ የሰነቀ ድርጅትም ሆነ ሰው ከራሱ ክበብ አልፎ ሌላው እንደምን ሁኖ በሠላም እና በደስታ እንደሚኖር ያስባል እንጂ ዕለት ዕለት ደም በማፍሰስ አይኖርም።
ህወሃት በምርጫ ስልጣኑን እንደማይለቅ ለራሱ የማለ ድርጅት ነው። እዚህ መሃላ ላይ ያደረሰው ደግሞ እስከ ዛሬ የፈፀማቸው ወንጀሎቹ ናቸው።የጨበጠውን ስልጣን በምርጫ ቢለቅ ነገ የሚከተለውን ጠንቅቆ ያውቃል። ትላንት ያፈሰሱት የንፁሃን ደም ከኢትዮጵያ ምድር ላይ እየጮኸ ነው። ዘርፈው የገነቡት ህንፃ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ቆመው ሌብነታቸውን እየመሰከሩባቸው ነው። በልማት ሥም ከኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተዘርፎ የተደራጀው የንግድ ተቋም በኢትዮጵያ ህዝብ ወዝና ደም ታጥኖ እንዳማረበት አለ። ህወሃት የኢትዮጵያ የህዝብ ጠላት ሆኖ ራሱን ያቆመ ቡድን በመሆኑ በሰላማዊ እና በሰለጠን መንገድ የያዘውን ሥልጣን ለህዝብ አይለቅም።
እንግዲህ ምን ይሻላል ?
ህወሃቶች ኑና እንወዳደር ብለዋል። እነዚህ ቡድኖች ኑና እንወዳደር ሲሉ እነርሱ የብረት ቦክስ ጨብጠው፤ ሌሎቹ ደግሞ ሌጣቸውን ሁነው ያለ በቂ ታዛቢ እንዲፎካከሯቸው ወስነው ነው። እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ሁነንም ቢሆን የምንወዳደረው ለነፃነት መሆን ይኖርበታል። ከነፃነት በመለስ ያለው ማንኛውም ዓይነት የምርጫ ውጤት በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ዝሪፊያ፤ ዘረኝነት፤ እሥራት እና ግድያ ያስቆማል የሚል ዕምነት በማንም ዘንድ ያለ አይመስለንም። በምርጫ ውድድር የምናተርፈው የህግ የበላይነት፤ እኩልነት እና ነፃነት ካልሆነ ተጎጂው ሰፊው ህዝብ ይሆናል።
ህወሃት የብረት ቦክስ ጨብጦ እኛ ደግሞ ሌጣችንን ሁነን መወዳደር ፍትሃዊ አይደለም በማለት ድምፃቸውን እያሰሙ ያሉት ወገኖችም የህዝብን መሠረታዊ ፍላጎት ለሟሟላት አስፈላጊ የሆነው ነፃነት ዋነኛው ግባቸው መሆን ስለሚኖርበት ይመስለናል። ወደ ውድድር ከመግባታችን በፊት ህወሃት የብረት ቦክሱን ያውልቅ፤ የመወዳደሪያ መድረኩም እኩል ይሁን ማለታቸው የሚሰማ ቢኖር ፍትሃዊ ጥያቄ ነው።የህወሃትን የብረት ቦክስ ለማስወለቅ መሥዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውም ለነፃነት የሚከፈል ዋጋ ይሆናል። ከህወሃት ጭካኔና ድንቁርና ስንነሳ በዚህ መንገድ የሚሄዱት የሚከፍሉት መሥዋዕትነት ከባድ እንደሚሆን እንጠብቃለን። ግን ደግሞ ነፃነት ያለ መሥዋዕትነት እንደማይገኝ ሌላው ቀርቶ ነፃነትን የማያውቁት ህወሃቶች ያውቃሉ። በማንኛውም መልኩ ከህወሃቶች ጋር አገት ለአንገት ተናንቀው በአገር ቤት ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ድርጅቶች ልበ ሙሉነታቸውን እጅግ አድርገን እናደንቃለን። እምቢ ለነፃነቴ፤ እምቢ ለክብሬ፤ እምቢ ለህወሃቶች ቀይ መስመር ማለት ይሄ እንጂ ሌላ አይደለም። እንግዲህ ዘረኞቹና ዘራፊዎቹ ቡድኖች ሊያደርሱ የሚችሉትን ጉዳት መቀነስ የሚቻልበትን መንገድ ማሰብ ተገቢ ይሆናል። ህዝቡ በልዩ ልዩ ሰንሰለት የታሠረ በመሆኑም በሚፈለገው መጠን ወጥቶ የትግሉ አካል ካልሆነም ተስፋ መቁረጥ አይገባም።በተጀመረው ላይ ይበልጥ እያጠናከሩና እየጨመሩ እየተካሄደ ያለውን ትግል መቀጠል ምርጫ የሌለው ሥራ ነው።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አገር ቤት ሁነው ከጭካኔ በቀር ሌላ ዕውቀት ከሌላቸው ህወሃቶች ጋር በትግል ላይ ያሉ ድርጅቶችን ያደንቃል። ያመስግንማል። በርቱ ከማለት በቀር የምንለው ሌላ የለንም።
እኛ የጀመርነውን ሁለ ግብ ትግል እያጠናከርነው ነው። የአገራችንን ውርደት፤ የወገኖቻችንን ጉስቁልና እያየን ዝም ብንል እርግማን ይሁንብን ያሉ ወጣቶች የአያቶቻቸውን ጋሻና ጦር አንስተዋል። እናቶችም ልጆቻቸውን መርቀው ፋኖ ተሠማራ ብለዋል። ሌሎች ደግሞ የኋላ ደጀን ሁነው ሳያቅማሙ ቁመዋል። ብዙ ባለሙያዎች ለአገራቸው የሚከፈልውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጀተዋል።
እንግዲህ የጀመርነውን ትግል የሚያስቆመን ምድራዊ ኃይል የለም። የህወሃት የመረጃ መረብ ይበጣጠሳል። የጦር ኃይሉ ከጥቂት ዘረኞችና ሌቦች ይልቅ ወገኑን እንደሚመርጥ በየቀኑ የሚደርሱን መረጃዎች ያሳዩናል። የከተማው ህዝብ ህወሃቶችን አክ እንትፍ ካላቸው ብዙ ዘመን ሁኖታል። የገጠሩም ህዝብ የህወሃት ዋሻ የመሆኑ ነገር አብቅቷል። ይሄ ሁሉ የእኛ አቅማችን ነው። ይሄን አቅም አደራጅተንና ሥራ አሲይዘን አገራችንን ነፃ የምናወጣበት ግዜ ሩቅ አይደለም።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩን ይፋ አደረገ ∙በ15 ከተሞች በተመሳሳይ ሰዓት ሰልፎች ይደረጋሉ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ያወጣውን ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩን ዛሬ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓ.ም ይፋ አድርጓል፡፡ ትብብሩ የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብሩን በህዳር ወር በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ማከናወኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩ ደግሞ ለ2 ወራት የሚቆይ እንደሚሆን ተገልጹዋል፡፡
የትብብሩ አመራሮች በሰማያዊ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት በሁለተኛ ዙር የትብብሩ መርሃ ግብር መሰረት የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 የሀገሪቱ ትላልቅ ከተሞች ላይ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ይደረጋሉ፤ በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳ፣ በባህር ዳርና በአዳማ ደግሞ ህዝባዊ ስብሰባዎች እንደሚደረጉ የትብብሩና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነት (ኢ/ር) በመግለጫው ወቅት ተናግረዋል፡፡
‹‹የመግባቢያ ሰነዳችንና የጥናት ሪፖርታችንን እንዲሁም ከመጀመሪያው ዙር ያገኘውን ተሞክሮ በሠረት በማድረግ ይህን የሁለተኛ ዙር የሁለት ወር ዕቅድ (ከታህሳስ 16 እስከ የካቲት 15 /2007) አውጥቶ በቀዳሚነት ለዋነኛ ባለቤቶቹና ፈጻሚዎቹ ኢትዮጵያዊያን ሲያቀርብ እንደመጀመሪያው ዙር ከጎኑ እንደሚቆሙ ሙሉ እምነት በማሳደር ነው›› ያለው መግለጫው፣ በትብብሩ በኩል በአመራር ከፊት ቆመው ትግሉን ለመምራት ዝግጁነትና ቁርጠኝነት መኖሩን አስረድተዋል፡፡
‹‹የያዝነው የትግል መንገድ ሠላማዊና ህገ-መንግሥታዊ ብቻና ብቻ፣ መጓጓዣችን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ፣ መድረሻችን መድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ እንዲሁም በጉዞኣችን ላይ የቱንም ያህል አረመኔያዊ የኃይል እርምጃ ይወሰድብን፣ ትግሉ የቱንም ዓይነት ዋጋና መስዋዕትነት ይጠይቅ ከጅምሩ ያለመስዋዕትነት ድል የለም ብለን ተነስተናልና ከያዝነው ዓላማ ኢንች የማናፈገፍግና ለቃላችን በጽናት የምንቆም መሆኑን ዳግም እናረጋግጣለን›› ብሏል ትብብሩ በመግለጫው፡፡
እቅዱ የመጀመሪያው ዙር ቀጣይ መሆኑን ያተተው የትብብሩ መግለጫ፣ ‹‹ዓላማችን የምርጫ ሁኔታዎች ባልተሟሉበትና የመራጩ ህዝብ ነጻነት በሌለበት ስለምርጫ መናገር አስቸጋሪ ነው፣ እነዚህ በሌሉበት አማራጭ የምርጫ ኃሳቦች በህዝብ ውስጥ ሊንሸራሸሩም ሆነ አማራጭ ኃሳባችንን ከህዝብ ማድረስ አይቻልም፣ ሚናችንም የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው አማራጭ ሆኖ መቅረብ ሣይሆን የህወኃት/ኢህአዴግ አጃቢነትና የሀገር ሃብት በአላስፈላጊ መንገድ የማባከን ሥራ ተባባሪነት የዘለለ አይሆንም ከሚል የመነጨ ነው›› ሲል አቋሙን አሳውቋል፡፡ ነጻነት በሌለበት ተጨባጭ ሁኔታ ምርጫ ቧልት ነው ሲልም አክሏል መግለጫው፡፡
ሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ዕቅዱ እንደባለፈው ተደጋጋፊ፣ ተመጋጋቢና ተከታታይ ሦስት ዋና ዋና ተግባራትና በሥራቸው አስራ አራት ዝርዝር ተግባራት ማካተቱም ተመልክቷል፡፡ እነዚህ በትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ጥልቅና ዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸው የጸደቁ ዋና ዋና ተግባራትም፡-
1. የአባላትና የትብብሩ አቅም ግንባታ፡- የትብብሩን አባላት አብሮነት ማጠናከርና የጋራ ዓላማውን የማስፈጸም አቅም ማጎልበት፤ 
2. የህዝብ ግንኙነት ተግባራት፡- የህዝብ ተደራሽነት ማስፋትና ዓላማ ማስተዋወቅ፣
3. የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች ማመቻቸት፡- በአዲስ አበባና የተመረጡ ከተሞች አራት የአዳራሽ/አደባባይ የህዝብ ውይይት፤ በአዲስ አበባና በተመረጡ አስራ አምስት የክልል ከተሞች በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን፤ የሚያጠቃልሉ ናቸው፡፡
የትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ተግባራቱን በጊዜ ሠሌዳ በማስቀመጥ ለነዚህ ተግባራት ማስፈጸሚያ የብር 1,215, 000.00 (አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ ) በጀት ማጽደቁንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ትብብሩ ለያዘው ሠላማዊና ህገ-መንግሥታዊ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትግል በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ ሌሎች ትብብሩን ያልተቀላቀሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ትብብሩን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Donnerstag, 25. Dezember 2014

ኤርትራዊው አቶ በረከት በሕወሓት 40ኛ ዓመት ላይ “እኛ ብአዴኖች ወያኔዎች ነን” አሉ

ኤርትራዊው በረከት ስምዖን በሕወሓት የምስረታ በዓል ላይ እኛ ብአዴኖች (የአማራውን ድርጅት ማለታቸው ከሆነ) ወያኔዎች ነን አሉት:: ሙሉ ንግግራቸውን አስቀምጠናል ያንብቡትና ትዝብትዎን ይስጡ::
ኤርትራዊው በረከት ስምዖን በቅርቡ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ከተከለከው ፍልፍሉ ጋር:: ኢሳት ራድዮ ፍልፍሉን ቃለምልልስ አድርጎ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ እንዳተለከለ እንዲያስተባብል ዕድል ቢሰጠውም; ተስፋ የቆረጠው ፍልፍሉ ከበረከት ጋር በሕወሓት በዓል ላይ ፎቶውን እየተነሳ ስለዲያስፖራው መስማት የሚፈልጉትን እየነገራቸው ሲያስቃቸውም አምሽቷል:: ኢሳት የወያኔውን ተላላኪ ፍልፍሉ በዘ-ሐበሻ የቀረበበትን እውነተኛ መረጃ እንዲያስተባብል መድረኩን መፍቀዱ; ይህን ፕሮግራም ያቀረቡት ሰዎች ከበስተጀርባቸው ማን እንዳለ? እንዲመረምር አንባቢዎች እየጠየቁ ነው::
ኤርትራዊው በረከት ስምዖን በቅርቡ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ከተከለከው ፍልፍሉ ጋር:: ኢሳት ራድዮ ፍልፍሉን ቃለምልልስ አድርጎ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ እንዳተለከለ እንዲያስተባብል ዕድል ቢሰጠውም; ተስፋ የቆረጠው ፍልፍሉ ከበረከት ጋር በሕወሓት በዓል ላይ ፎቶውን እየተነሳ ስለዲያስፖራው መስማት የሚፈልጉትን እየነገራቸው ሲያስቃቸውም አምሽቷል::
ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ የለውጥ ፍላጎቶች ዘመናትን ያስቆጠሩ ናቸው። የብዙ ትውልዶች የትግል ውጤትም ናቸው – ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚደረግ የቅብብሎሽ ትግል ሆኖ ኢትዮጵያን ለማሻሻልና
ለመለወጥ ኢትዮጵያዊያን ዋጋ የከፈሉበት ሂደትም ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ የካቲት አስራ አንድ የተመሰረተው ህወሓት በዚህ ሂደት ውስት የሚጠቀስ አንዱ ድርጅት ነው። በዚያን ጊዜ ከተመሰረቱት ድርጅቶች ህልውናውን ጠብቆ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ተሳክቶለት በአሸናፊነት የወጣ ድርጅት ነው። ህወሓት የሰራቸው ስራዎች ምንድን ናቸው ብዬ ሳይ፣ የመጀመሪያው በ1967 ዓ.ም ሲደራጁ ከዚያ በፊት የነበረው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ አካባቢ የነበረው ሁኔታ ማስታወስ ጠቃሚ ይመስለኛል። ለውጥ ውስጣችን እንዲቀሰቀስ፣ እኛ ጋር የነበረው የለውጥ ስሜት በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ውስጥም እንዲኖር፣ ብዙ ትውልድ መስዋዕትም እንዲከፍል ያደረገው የዴሞክራሲ የልማት እና የመለወጥ ብሎም የህዝቦችን ፍላጎት የሚያረካ ብቃት ያለው ሥርዓት ስላልነበረ ነው። እንደዚህ አይነት ስርዓት በሌለበት፣ በተለይ ብዝሃነትን በአግባቡ ማስተናገድ የማይችል፣ የሃይማኖት፣ የብሔር መብት በአግባቡ ማክበር የማይችል የዜጎችን ዴሞክራሲያዊና የልማት ጥያቄዎችን በአግባቡ መመለስ የማይችል ስርዓት ባለበት እና በወቅቱ የነበረው ስርዓት የቆመው ከምንም ነገር በላይ በአፈና ስርዓት ተደግፎ በሆነበት፣ በጣም ግዙፍ ወታደራዊ ተቋም፣ በጣም ግዙፉ የስለላ ተቋም፣ በመላ ሀገሪቱ በተንሰራፋበት ሁኔታ እንዴት ነው ይህ የአፈና ስርዓት አሰወግዶ በኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ ማምጣት የሚቻለው? ግዙፉን የአፈና ተቋምስ በታሰበው መልማስወገድ ይቻላል ወይ? እንደሚታወቀው በኢትዮጵያስርዓት ውስጥ የመጨረሻ ትልቁን አፋኝ የደርግ አገዛዝ 500ሺ ጦር ሰራዊት የነበረው፣ በጥቁር አፍሪካ በትጥቁም በወታደራዊ ብዛቱም የሚስተካከለው አልነበረም። ይህን ሃይል አስወግደህ ብቻ ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ ሊመጣ የሚችል የነበረው። ይህ ሃይል ባለበት ቀይ ሽብር ነበር የነበረው። ይህ ሃይል ባለበት አፈና ነበር የነበረው። ስለዚህ ይህን ግዙፍ ሃይል እንዴት ነው የምናስወግድነው? የሚለው ጉዳይ በጣም ብዙ መሰረታዊ ጥያቄዎችን መመለስ ይጠይቅ ነበር። ከሁሉ በፊት የጠራ ዓላማ መያዝንም ይጠይቃል። የት ነው የምደርሰው? መዳረሻየስ የት ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ ማስፈን፣ ለልማት የተመቸ ከባቢያዊ ሁኔታዎች መፍጠር፣ ዴሞክራሲያዊ አዲስ የሆነ አንድነት መፍጠር እነዚህን የመሳሰሉት ግልፅ ዓላማዎችን መያዝም ይጠይቅ ነበር። ሁለተኛ፣ ብቃት ያላቸው የትግል ስልቶች፤ ትክክለኛ አቅጣጫዎች መተለምና እነሱንም ተግባራዊ ማድረግ ይጠይቅም ነበር። ስለዚህም ህወሓት ይሄን (ከላይ የሰፈሩትን) ይዞ ነበር የተነሳው። ህወሓትን ከሌሎች ድርጅቶች የሚለይበት ወሳኙ ነገርም ይህ ነው። ጥርት ያሉ ነገሮችን፣ ሊያታግሉ የሚችሉ፣ ለውጥ ማምጣት የሚችሉ፣ ሃሳቦችን ይዞ መምጣት።
ላለፉት ሰላሳ አራት ዓመታት ከህወሓት ጋር አብረን ታግለናል። ድርጅቱን በቅርቡ እናውቀዋለን፣ ህወሓት ለሃሳብ ልዕልና ትልቅ ቦታ ያለው ድርጅት ነው። ጥርት ነገር ያለ መያዝ። ነገ ከነገወዲያ በምናያቸው ቦታዎች ሃሳብን እንዴት እንደማጥራት የሚችል ድርጅት ነው። ለትግሉ መነሻና መድረሻውን ጥርት አድርጎ በደንብ ማስቀመጥ በመቻል ላይ ትልቅ አቅም አለው። ስለዚህም ግልፅ የትግል ዓላማ ይዞ የተንቀሳቀሰ ድርጅት ነበር። ይህንን ዓላማ ይዞ በመጀመሪያዎቹ የደርግ ዓመታት የመሃል ሀገር እንቅስቃሴ በተዳከመበት ጊዜ ሸክሙ እዚህ ሰሜን ኢትዮጵያ ላይ ነበር። በጣም ከባድ ሸክም ነበር የተቋቋምነው። የትግራይን ሕዝብ ይዞ ከትግራይ ሕዝብ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ በጣም ብዙ ዘመቻዎችን አልፏል። እኛ በለሳ እስከምንመጣ፣ በስድስተኛ ዘመቻ ላይ ነበር ትግራይ የደረስነው። እነዚህ ማዕበሎች ነበሩ። የደርግ ሰራዊት ይመጣል፣ ድርጅቱን ለማጥፋት ይሞክራል። ድርጅቱ ጥቃቱን ይቋቋማል፣ ወደአዲስ ምዕራፎችም ይሻገራል። በዚህ መንገድ የደርግ ማዕበሎችን እየተቋቋመ የዘለቀ ድርጅት ነው ፤ህወሃት። የሰው ሃይል እየተጠናከረ ሲመጣ በጋራ እየተፋለምን ኢሕአዴግን መስርተን ግዙፉን የደርግ ሰራዊት ለመደምሰስ ችለናል።
ስለዚህም የህወሓት አንዱ ትልቁ ሚና ተብሎ መጠቀስ ያለበት ምንድነው ከተባለ በኢትዮጵያ የአፈና ስርዓትን ማስወገድ ነው። ያንን የአፈና ስርዓት ማስወገድ ባይቻል ኖሮ፣ ከዚህ ግዙፉ የአፈና ተቋም ጋር ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት አትበቃም ነበር። ይህ በታሪክ የተለየ ተደርጎ መታየት ያለበት ነው። ሊከበርም፣ ሊገለጽም፣ ሊፃፍበትም የሚገባ ነው። የጦርነቱ ሂደት፣ የተከፈለው መስዋዕትነት፣ ትግሉ መሃል ሃገር ሲዳከም እዚህ ጫፍ ላይ እንደምንም ሕዝባዊ ትግሉን ጠብቀህ የመቀጠል ነገር ትልቅ ትልቅ መስዋዕትነትን፣ አስተዋይነትን፣ በዚህ ደረጃ ሕዝባዊ ልቦናን የሚጠይቅ ነበር። ለዚህም ነው የህወሓት ትልቅ ሚና፣ የነበረውን የአፈና ስርዓት በኢትዮጵያ ውስጥ ላይመለስ አድርጎ መታገሉ ተጠቃሽ የሚሆነው።
ይህም ብቻ አይደለም። ደርግ በወደቀ ማግስት ምንድን ነው የተደረገው ብለን ከመጀመሪያው እንይ። የካቲት 11 ድርጅቱ እዚህ ቦታ ትጥቅ ትግል ሲጀምር ይዞት የነበረውን ዓላማ በፍጥነት ወደ ተግባርመተርጎም የደመረበት ወቅት ነው። የአፈናው ስርዓት ተቋም ከተገረሰሰ በኋላ አዲስ መሰረተ ሰፊ ዴሞክረሲ ነው በኢትዮጵያ ውስጥ የተዘረጋው። ስለዚህም ይህ መስዋዕትነት ባይኖር ኖሮ ያንን ማድረግ ይቻል ነበር ወይ? በብሔር ጥያቄ ዙሪያ በወቅቱ ብዙ አማራጮች ነበሩ። በኦሮሚያ ውስጥ ከዳር እስከ ዳር የነበረው ኦነግ ነው። በደቡብ ኢትዮጵያም ብዙ ተመሳሳይ ድርጅቶች ነበሩ። በሶማሌም በአፋርም ተመሳሳይ ድርጅቶች ነበሩ። በመሐል ሀገር ኢሕፓ ሞካክሮ የተወው ትግል አለ። ተስፋ መቁረጥ በተዛባ አካሄድ የመሄድ እድሎች ሰፍተው የነበረበት ሁኔታ ነበር የነበረው። ይህን ተቋቁሞ በትክክለኛ መስመር ተመርቶ ጥሩ አጋሮች ካገኘ በኋላ የአጋርነት እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ላለፉት አርባ አመታት የታገለ ድርጅት ነው።
በሌላ መድረክ ከዴሞክራሲው ባሻገር በልማት ሥራዎች ላይ ያለውን አስተዋፅዖ እንመሰክራለን። ሆኖም ግን የህወሓት አስተዋፅዖና ሚና በኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል ውስጥ ትውልድ በቅብብሎሽ ትግሉን ዳር ያደርሳል ብሎ የተነሳበት ሁኔታ በልዩ ሁኔታ መታየት ያለበት ይመስለኛል። ይህን ትግል ከመነሻው የመሩት እዚህ ያሉት ጓዶች ናቸው። ከእነሱ ጋር በመሆን አብረው ሲመሩት የነበሩት ምንአልባትም በአስተሳሰብ ልቀት ሁላችንም የምናከብራቸው አቶ መለስ ለዚሁ ትግል ያበረከቱት ትልቅ አስተዋጽኦም አለ።
ህወሓት የአስተሳሰብ ጥራት የነበረው፣ አስተሳሰቡንም በተጨባጭ ተግባር ላይ ማዋል የሚችል ድርጅት ነው። ይህም በመሆኑ ነው ብዙ ንቅናቄዎች ተጀምረው በከሸፉበት ሁኔታ ሃሳብን ተግባራዊ በማድረግና በተለይ ህዝብን ይዞ በብቃት በመታገል ረገድ ይኸው ድርጅት ውጤታማ የሆነውና እዚህ ደረጃም የደረሰው።

ብአዴኖችም ሁሌም ቢሆን ራሳችንን ከህወሓት ነጥለን ያየንበት ጊዜ የለም። ሁላችንም “ወየንቲ ኢና” (ወያኔዎች ነን) ነው የምንለው በዚህ ሁሉ ሂደት ጠንካራ ሠራዊት ገንብቷል። እኛ ደጀን ነው የምንለው፣ ከሕዝቡ ጋር የፀና እና ጥብቅ ግንኙነት ነበረው። ለሕዝብ ታዛዥ ሕዝብን የሚያከብር ድርጅት ነበር። በዚህ መንገድ እየታገለ ቆየ። እኛ በ1972 ዓ.ም. ከኢሕአፓ ተለይተን ህወሓት ወንድም ድርጅት ይፈልግ በነበረበት ጊዜ፣ ከበለሳ የመሐል ሃገሩ አልመች ሲለን ወደ ትግራይ እንሂድ ብለን መጣን። ከህወሓት ጋርም ተገናኘን፣ ከተገናኘን በኋላ በብዙ ነገሮችም አብረን ሠርተኛል፤ታግለናል። በወቅቱ እኛ ቁጥራችን ትንሽ ነበር። እነሱ ደግሞ በአንፃሩ ግዙፍ መሆን ጀምረዋል። እኛ መስዋዕትነት እንዳንከፍል ከእኛ በፊት እነሱ ለመሰዋት ብዙ ብዙ ነገሮች እያደረጉ እያገዙን፣ የእኛ ሃይል እንዳይመታ እንዳይመናመን ከፍተኛ እገዛ አድርገውልናል። በኋላ የእኛ  እኛ ብአዴኖችም ሁሌም ቢሆን ራሳችንን ከህወሓት ነጥለን ያየንበት ጊዜ የለም። ሁላችንም “ወየንቲ ኢና” (ወያኔዎች ነን) ነው የምንለው። ስለዚህ ይህንን ምስክርነት የምሰጠው እንደ ብአዴን ሆኜ አይደለም፤ እንደ አንድ ወያናይ ሆኜ ነው። እንኳን ለዚህ በቃችሁ፤ እንኳን ለዚህ በቃን እላለሁ።

ከታህሳስ 10 ቀን 2007 የአዲስ አበባና ባህርዳር አመጾች ምን እንማራለን?

ዓርብ ታህሳስ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. አዲስ አበባ እና ባህርዳር በዓይነታቸው ልዩ የሆኑ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን አስተናግደዋል። በአዲስ አበባ ሙስሊም ወገኖቻችን ከህወሓት ሰላዮች እይታ ውጭ በተደራጀ መንገድ በኑር መስኪድ ያደረጉት ተቃውሞ ቢያንስ ሶስት ቁም ነገሮችን አስገንዝቧል። እነዚህ ሶስት ነገሮች፣ (1ኛ) ምላሽ እስካላገኘ ድረስ የመብት ማስከበር ትግል በአፈና ተዳፍኖ እንደማይጠፋ፣ (2ኛ) ጽናት ካለ የወያኔ አፈናን የሚቋቋም ድርጅትና ተግባቦት መፍጠር እንደሚቻል፣ እና (3ኛ) ሙስሊሙን በተመለከተ የህወሓት አንድ-ለአምስት አደረጃጀት መፍረሱ ናቸው። ይህ ድል የሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ሙስሊም ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያንም የሚጋሩት የጋራ ድል ነው። በተለይም የወያኔ አንድ-ለአምስት አደረጃጀት የሚናድ መሆኑ በተግባር ማሳየታቸው እና የህወሓት ሰላዮች ሳይሰሙ ተቃውሞዓቸውን አደራጅተው ተግባራዊ ማድረጋቸው የሚደነቅ ነው።
በዚሁ ዕለት በባህርዳር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ከሕዝብ ጋር ሳይመክር በልማት ስም ያሻውን የሚያደርገውን እብሪተኛን ለመቃወም በአጭር ጊዜና በፍጥነት ተሰባስበው ቁጣቸው ማሰማት ችለዋል። በባህር ዳር ሕዝብ ልብ ውስጥ ለዓመታት ሲብሰለሰል የቆየውን የበደል ስሜት በዚህ አጋጣሚ ገንፍሎ ወጥቷል። በተለይም የወያኔ “ምርጥ ባርያ” መሆኑ የሚስፈነጥዘው ብአዴን በአማራ ሕዝብ ምን ያህል የተጠላና የተናቀ መሆኑ እንዲያውቅ ተደርጓል። ሆኖም ግን፣ ማናቸውንም ዓይነት ተቃውሞ የማያስተናዱት ህወሓትና ባርያው ብአዴን በባዶ እጁ ለተቃውሞ በወጣው ሕዝብ ላይ የጥይት ናዳ እንዲያወርድ ሠራዊታቸውን በማዘዛቸው እና ይህን ዘግኛኝ ትዕዛዝ የሚያስፈጽም ሠራዊት ያለ በመሆኑ ብዙ አዛውንት፣ ጎልማሶችና ወጣቶችን ለሞትና ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል። የህወሓትና የብአዴን ሠራዊት ከዱላና ከገዳይ ጥይት ሌላ አንዳችም የአድማ መበተን እውቀት የሌለው መሆኑን የሚያሳዝን ነው፤ በሰላማዊ ሕዝብ ላይ እንዲተኩስ ሲታዘዝ የሚተኩስ መሆኑም የሚያሳፍር ነው። በባህርዳር ከተፈፀመውም የኢትዮጵያ ሕዝብ (1ኛ) ሕዝባዊ አብዮት እንዲህ በደንብ ሳይታሰብበትም ሊቀሰቀስ የሚችል መሆኑ፣ (2ኛ)ህወሓት ሕዝብ አምርሮ ሲነሳበበት የሚደነግጥና የሚርበተበት ፈሪ መሆኑ፣ እና (3ኛ) በፈሪነቱ ምክንያትም በባዶ እጃቸው በወጡ አዛውንትና ህፃናት ጭምር የተኩስ እሩምታ ከመክፈት የማይመለስ መሆኑን አስተውሏል ብለን እናምናለን።
ህወሓትንና አገልጋዮቹን ከስልጣን ለማባረር በአዲስ አበባ እና ባህርዳር የተደረጉትን ማቀናጀት ግዴታ ነው። በሌላ አነጋገር የባህር ዳሩ ሕዝባዊ አመጽ አዲስ አበባ ኑር መስጊድ በታየው ዓይነት ብልሃት፣ ድርጅት እና ዲሲፕሊን ተመርቶ ቢሆን ኖሮ በባህር ዳር የተጫረው የነፃነት እሳት በመላው አገሪቷ ተቀጣጥሎ ዛሬ የምንገኝበት ሁኔታ ከታህሳስ 10 ከነበረው ፈጽሞ የተለየ በሆነ ነበር። ለወደፊቱም ማድረግ የሚኖርብን ይህ ነው። ሙስሊምና ክርስቲያኑ ተደጋግፎ አንዱ ዘንድ የጎደለው በሌላው አካክሶ የሁላችንም ጠላት የሆነውን ህወሓትን ከነ አገልጋዮቹ ከሥልጣን ማስወገድ የሁላችንም የጋራ ግዴታ ነው። ጠመንጃው የፍርሃቱ መሸሸጊያ ያደረገው ህወሓትም ጠመንጃውን የሚያስጥል መላ እና ዱላ መዘጋጀት ይኖርበታል። ህወሓትንና አጫፋሪዎቹን ከሥልጣን ለማባረር በጠንካራ ድርጅት፣ ዲሲፕሊንና ብልሃት የሚመራ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽ ቅንጅት ሊኖር እንደሚገባ የታህሳስ 10 ቀን 2007 ትልቁ ትምህርት ነው። በዚህ ዕለት የህወሓትን ወደ ጠመንጃ የመሮጥ ወራዳ ባህርይን የሚያስቆም ኃይል የማደራጀት አስፈላጊነትም ጉልህ ሆኖ ወጥቷል። ዓርብ ታህሳስ 10 ቀን 2007 ዓም አዲስ አበባና ባህርዳር የተፈፀሙትን አገናኝቶ ያነበበ ማንኛውም ሰው የሁለገብ ትግል ስልት ምንነትና አዋጭነት በገሃድ ይረዳል፤ ወደዚያ እያመራን መሆኑንም ይገነዛባል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዓርብ ታህሳስ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. በባህርዳር ከተማ በርካታ ወገኖቻችን ሕይወታቸውን ያጡ በመሆናቸው የተሰማውን ጥልቅ ሀዘንና ቁጭትእየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል። እንደዚሁም በዚሁ ዕለት በህወሓትና ብአዴን ሠራዊቶች ጥይት ለቆሰላችሁና ለተደበደባችሁ ወገኖቻችን ሁሉ ህመማችሁ ህመማችን፤ በእናንንተ ላይ የደረሰው በደል በሁላችንም ላይ የደረሰ መሆኑን እንድትረዱልን እንፈልጋለን። እንዲህ ዓይነቱ በደል እንዲያበቃ ደግሞ ህወሓት፣ ብአዴን እና በየክልሉ ያሉት አጋፋሪዎቹ ከሥልጣን መወገድ እንዳለባቸው ያለጥርጥር እናምናለን። ህወሓት እና አጫፋሪዎቹን ከሥልጣን ለማባረር ደግሞ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ከሕዝባዊ አመጽ ጋር ማዳቀል ስለሚኖርብን በሁሉም ረገድ ዝግጅቶቻችን አጠናቀን ለወሳኙ ፍልምያ እንነሳ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የወደፊቱ የተሻለ የህይወት ተስፋ ያለው ወያኔ መቃብር ላይ ነው!!

ወያኔ በሀገራችን የዘረጋው ማህበራዊ ፖለቲካዊና የኢኮኖሚ ስርአት ለጠቅላላ ህዝባችን፣ በተለይ ለወደፊቱ ሀገር ተረካቢ ወጣት ሲኦል መሆኑ ቅጥሏል። በሀገሬ ውስጥ፣ ሰርቸ የተሻለ ህይወት እኖራለሁ ብሎ ማለም ቅዠት ሆኗል። ከዚህ ይልቅ ያብዛኛውን ወጣት ተስፋ ሀገር ጥሎ በገፍ መሰደድ ከሆነ ውሎ አድሯል።
በእጅጉ በሚዘገንን ሁኔታ በግፍ ተሰቃይተው ከሳውዲ አረቢያ ወደሀገራቸው ከተመለሱት ከ160 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ግማሽ ያህሉ ተመልሰው መሰደዳቸውን በቅርቡ የወጣ ጥናት አረጋግጦል። በዚህ ሁኔታ ከተሰደዱ ወገኖቻችን ውስጥ ቁጥራቸው ከ70 በላይ የሚሆኑት ቀይ ባህር ላይ የነበሩበት ጀልባ ሰምጦ አልቀዋል። እነዚህ ወገኖቻችን ጉዞቸው በሞትና ህይወት መሃል መሆኑን አስቀድመው ያውቃሉ። ይህንን ያስመረጣቸው ግን የወያኔ ስርአት ነው። የወያኔ ስርአት የተመቻቸው ለስርአቱ ሹመኞችና ለዘመድ አዝማድ ከዚያ ከተረፈ ለጎሳ ተወላጆቻቸው ብቻ ነው። ሀገሪቱ ውስጥ ተገኘ የሚባል የኢኮኖሚ እድገት ካለም ከዚሁ ከጠባብ ቡድን ጥቅም አልፎ መከረኛውን ህዝብ የሚጠግን አልሆነም።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ከተስፋ ቆራጪነትና ሞትና ህይወትን ከሚያስመርጥ አስከፊ ህይወት ያለፈ ምርጫ አለ። ዋናው ምርጫቸውም ይህ ሊሆን ይገባል፤ ምርጫው ለዚህ መከራና ሀዘን ውርደት የዳረገንን ጨካኝ የወያኔ ስርአት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ነው።
ወያኔ የህዝቡ ጉስቁልናና ስቃይ ጉዳዩ አለመሆኑን ባለፉት ሳምንታት ከ70 በላይ ወገኖቻችን ቀይ ባህር ውስጥ ሰምጠው: አለም በሀዘን በሚመለከተንና መንግስት አለ ብሎ የሀዘን መግለጫ በሚልክበት ሰአት የብሄረሰብ ቀን በሚባል የቦልት በአል የወያኔ ሹሞች ብዙ ሚሊዮን ብር አውጥተው በውስኪ እየተራጩ ይጨፍሩ ነበር።
ይህ አልበቃ ብሎ አሻንጉሊቱ ሃይለማርያም ደሳለኝ በስደተኛው ላይ ለሰሚ የሚቀፍ የወረደ አሉባልታና ስድብ ሲያወርድ ሰምተናል፣ ራሱን ያወረደ ተረት ተረትም ተናገረ። በሥልጣን የመባለግ ዝንባሌያቸው ሳይውል ሳያድር በሚጠቀሙት የባለገ አዋራጅ ቃላት የመጠቀም ርሃባቸው አሳየን።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፦ በምድረ ኢትዮጵያ የተስፋ መቁረጥና ለወያኔ ሎሌዎቹ መሳለቂያ እንድንሆን ያበቃን ይህ የነቀዘ ዘራፊ የወያኔ ስርአት ብቻ ነው። ይህ ሁሉ ስቃይና ውርደት የሚቆመው ወያኔ ሲወገድ ብቻ መሆኑን ሁላችንም ጠንቅቀን ልንረዳ ይገባል። በቅርቡ ዱላውንና ግፉን ሁሉ ለመቀበል ቆርጠው ወያኔን ከተጋፈጡት የሰማያዊ ፓርቲ አባልና ደጋፊ ወጣቶች ብዙ ልንማር ይገባል። እንደእባብ በጭካኔ መቀጥቀጣቸው አጠነከራቸው እንጂ አላዳከማቸውም።
ወያኔ ዛሬ ከመቸውም በበለጠ ነቅዞል። የጭካኔውና የፍርሀቱ ምንጪ ጣር ሞቱ እንጂ ሌላ አይደለም።
ሞትና ህይወትን ከሚያማርጥ ስደት የደረሰው ወጣቱ አርበኝነትን መምረጥ አለበት። ከቀን ጅቦች ራስን በማዳን ውርደትን፣ ስደትን ማስወገድ ይቻላል። ይህ የነገ ሳይሆን የዛሬ ውሳኔ መሆን ይኖርበታል።
በመሆኑም ግንቦት 7 ወጣቱ በያለህበት በራስህ አነሳሽነት እንድትደራጅ ያበረታታል። አመች ሁኔታ ያለህ ወጣት ደግሞ ተቀላቀለን። ሰራዊቱ ውስጥ ያለህ ወጣትና ሎሌነት የሰለቸህ ሁሉ የነጻነት ሀይሎችን ትቀላቀል ዘንድ ጥሪያችን ይድረስህ።
የሀገራችን የህዝባችንና የያንዳንዳችን የተሻለ ህይወትና ዘመን ተስፋ የተቀመጠው ወያኔ መቃብር ላይ መሆኑን መዘንጋት የለብንም።
ድል ኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ተስፋየ ተስፋ ሲቆርጥ


(ሰናይ ገ/መድህን)
ክፍል 4
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቴሌቪዥን ቀርበዉ (የቀጥታም ሆነ
የተቀረፀ)  ቃለምልልስ ከማካሄዳቸዉ በፊት ቀደም ብሎ
በቴሌቭዥንና ራዲዮ ተደጋጋሚ ማስታዎቂያ መልቀቅ የተዘወተረ
ነዉ፡፡ በተለይም ቃለምልልሱ የሚደረገዉ ከዉጭ ከሚመጡ
ጋዜጠኞች ጋር ከሆነ ማስተዋወቁ ሞቅ ደመቅ ይላል፡፡ ጋዜጠኞቹ
በቀጠናዉና ዓለምአቀፉ የወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት ጉዳይ ትንታኔ
ፍለጋ ሰዉየዉ ጋ እንደሚመጡ ተደርጎ ይራገባል፡፡ያሳብቅማልም፡፡
ያዉ 15ዓመት እንዳራገብኩላቸዉና እንደታዘብናቸዉም ሰዉየዉ ለመተንተን ወደሁዋላ አይሉም፡፡
ይደፍራሉ፡፡ ካፈርኩ አይመልሰኝ ወይንም የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም እንዲሉ ነገር ፡፡ የአንድ ሰሞኑ
የቅድመ ቃ/መ ማስታወቂያ ታዲያ ይበልጥ ትኩረትን የሳበ ሆነ፡፡ ታዋቂ ከሆኑት ኢትዮጵያዊያን
ድረገፆች መሀል ከኢትዮጵያን ሪቪዉ ጋር ቃለምልልስ  የማካሄዳቸዉ ጉዳይ ፡፡ በኤርትራ ቆይታየ ሰዉየዉ ኢትዮጵያዉያን ተቃዋሚ
ግለሰቦችን በተናጥል ከማነጋገር በቀር ከኢትዮጵያዉን ሚድያዎች ጋር ፊትለፊት ቁጭ ብለዉ አያዉቁም፡፡ ያን ጊዜ ግን በራቸዉን
ለሚዲዎች ክፍት ያደረጉ መሰሉ፡፡ ዳሩ ግን በኢትዮጵያን ሪቪዉ  ለመቅረብ በፈለጉበት ጊዜ  አንድ ነገር ግልፅ ነበር ፡፡ መገምገም ለቻለ፡፡
ይሄዉም ኤርትራ ከመሸጉት ኢትዮጰያዉያን ተቃዋሚ ሀይሎች መሃል የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ዴምህት) እየጎለበተ
መሄዱና የሌሎቹ የመፍተልተል ጉዳይ አደባባይ መዉጣቱ፤ በተለይም  በኤርትራ ከዴምህት አራት አመት በፊት ቀድሞ ግንባር ሆኖ
የተመሰረተዉ  የኢትዮጵያ ህዝቦች አርበኞች ግንባር እንደግመል ሽንት የሁዋሊዮሽ መዝረክረኩና (ስለመረጥኩት ቃል ይቅርታና በግንባሩ
ለተሰዉ ለታገሉ ለሚታገሉና ለሞከሩ ሁሉ አክብሮቴን እየገለጥኩ የሁዋሊዮሽ መፍተልተሉ ማለቴ የግንባሩን ጉዞ ይሆናል) መወነጃጀሉ
ይፋ እየሆነ መሄዱን ይጠቅሱዋል፡፡ የኤርትራ መንግስትም ከሚወነጀሉት ዋነኛዉ በመሆኑ፡፡ በኢትዮጵያዉያን ሚድያ ቀርበዉ ካንገት
ይሁን ካንጀታቸዉ ቢያስተባብሉ ምንም እንደማይከስሩ በመካሪዎች ተመከሩ እንበል፡፡ እንዲያዉም ጥቂት የዋሆችን ለወያኔ
ማሰፈራሪያነት ልንማርክ እንችላለን ይባሉም ይሆናል፡፡ ባናቱ ላይ ስለኢትዮጵያና ህዝቡዋ የሚሰጡት ገመድ ትንታኔ አለ፡፡ እናም
ቃለምልልሱ ተካሄደ ፡፡ግንባሮቹም ቀጠሉ፡፡ላሁኑ ይሄዉ ይበቃናል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ቃለምልልሱን ያካሄዱት እንደሚታወሰዉ ከሁለት ጋዜጠኞች ጋር ነበር ፡፡ ከኤልያስ ክፍሌና ከሎንዶኑ ስለሺ ጥላሁን ጋር፡፡
በድረገፅ በስም ብቻ ከማዉቀዉ ከኢትዮጵያን ሪቪዉ ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ጋር የተዋወቅሁትም በዚሁ ጊዜ ነበር፡፡ ከስለሺ ጋር ቀደም
ባለ ጉብኝቱ ተዋዉቀናል፡፡
ከጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ጋር በተለያዩ ጥቂት አጋጣሚዎች በኤርትራ በኩል ስለሚደረጉ የትጥቅ ትግል አያያዞች ጉዳይ የሀሳብ ልዉዉጥ
ያደረግን ሲሆን የኔ ድምዳሜ “ከንቱ ልፋትና መስዋዕትነት መክፈል ነዉ” የሚል ነበር፡፡ አሁንም ፡፡ ዝርዝር እማኝነቴ አሁን አያሻንም፡፡
ኤልያስ በህግደፍ ተስፋ ሰንቆ ነበር የመጣዉ፡፡ እንደተረዳሁት፡፡ ከፕሬዚዳንት ኢሳያሳ ጋር ቃለምልልስ ካካሄደ በሁዋላም በቀጠሮ ኒያላ
ሆቴል ተገናኝተን በሙያዊ የስራ ዕቅዱ ዙሪያ ያሰቡትን ሲገልጥልኝ ከዚሁ ተስፋ የመነጨ መሆኑን ተገንዝቢያለሁ፡፡ እናም ፀረ ወያኔ
የትጥቅ ትግሉን በቅርብ ለመደገፍና መረጃዎችን በቅርብ ለማስተላለፍ የኢትዮጵያን ሪቪዉ ቢሮ በአስመራ ለመክፈት እንቅስቃሴ
መጀመሩንና በዚህ ቢሮም ተስፋየ ገብረአብና እኔን እንድንሰራ እንደሚፈልግ በመግለጥ ግብዣዉን አቀረበልኝ፡፡ ስለ ህግደፍና አርበኞች
ግንባር ብዙ አሉታዊ ነገሮች ይፋ በወጡበት ጊዜ ኤልያስ ይህን እቅድ ማሰቡ ትንሽ ግራ አጋባኝ፡፡ ምን ተማምኖ ነዉ በሚል።፡”እርግጠኛ
ነህ ይሄ ነገር ይሳካል?” የግል ሚዲያ የማይዋጥላቸዉ ኢሳያስ ጉያቸዉ ዉስጥ ያዉም የአማርኛ ድረገፅ እንዲከፈት ቀና ሊሆኑ? ነባር
የህግደፍ ታጋዮችና የኢሳያስ ህቡዕ ፓርቲ አባላት (ኤማሰ)  የሚቆጣጠሩት የአማርኛዉ ኦሮሚኛ ትግራይና ሶማሌኛ  ቴሌቭዥንና ራዲዮ
ፕሮግራሞች እንዴት በሸምቀቆ እንደምንሰራ እያወቅኩ እነኤልያስን በነፃ ሚዲያነት እንዲሰሩ እንዴት ይፈቅዳሉ ብዬ ልገምት?…. ፡፡
ኤልያስ ጥርጣሬየን ተገንዝቦ “እነ ኮ/ሎኔል ፍፁም በኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚዎች አያያዝ ላይ ብዙ ነገሮችን እንዲያስተካክሉ ተነጋግረናል፤
በአጠቃላይ ፕሬዚዳንቱም አይዙዋችሁ ብለዉናል” ሲል ያገኙትን ተስፋ ባጭሩ አመላከተኝ፡፡
ቢሳካም ባይሳካም ለእሺታየ አላቅማማሁም፡፡ ምክንያቱም የሁዋላ የሁዋላ እጅ እጅ እያለኝ ከመጣዉና የማላምንበትን እየሰራሁ በመሆኔ
ህሊናየ እኔነቴን ሲጠየፈዉ እየታወቀኝ ከሄደዉ የኤርትራ ማስተወቂያ ሚ/ር ጭፍን ፕሮፓጋንዳ አካባቢ መገላገያ አገኘሁ በማለት፡፡ አንድ
ከባድ ችግር ግን ነበረ፡፡ በግል ፍላጎት ለመልቀቅ አይፈቀድልኝም፡፡ ስለዚህ ኤልያስ በዋነኛነት እንዲያነጋግር ተስማማን፡፡ ለሱ ሲሉ
http://www.ethiomedia.com/11notes/tesfaye_tesfa_seeqort.pdf

ከአንድነት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ተካሄዷል ብለን አናምንም!


ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ምርጫ ቦርድ ነፃና ገለልተኛ እንዳልሆነ የሚገነዘብ ቢሆንም ባለፈው ታህሳስ 12/04/2007 ዓ.ም የተካሄደው የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ በሀገራችን የምርጫ ቦርድ አለ ወይ?! እንዲል አድርጎታል።
የታህሳሱ 12/04/2007 ዓ.ም የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ነፃና ገልልተኛ አልነበረም ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የምርጫ ህጉን ተከተሎ ያልተካሄደ ሌላው ይቅርና የራሱ የምርጫ ቦርድ መመሪያን እንኳን ያልተከተለ ከመሆኑ አንፃር ተካሄዷል ብለን አናምንም። እንዲህ ዓይነቱ ድምዳሜ እንድንደርስ ያደረጉን ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም በዋናነት የሚከተሉት ነጥቦች ከግምት ውስጥ አስገብተናል።
ካገኘናቸው በርካታ ችግሮች ቀዳሚው ህዝቡ በምርጫ ቦርድ በእኩል በይፋ የስብሰባ ጥሪ ያልተደረገለት መሆኑ ነው። ፓርቲው ባሰማረባቸው የምርጫ ጣቢያ ቦታዎች ከሞላ ጎደል በአንድ ለአምስት ስርዓቱ ካደራጃቸው የራሱ አባላትና ደጋፊዎች በስተቀር ሌላው ህዝብ ሳያውቅ ነው የተካሄደው ማለት ይቻላል። ይሄ ደግሞ ከአስር ሺዎች በላይ ነዋሪ ያለባቸው አከባቢዎች ሀምሳ እና መቶ ሰው የተገኘባቸው አዳራሾች ነበሩ። የምርጫ ቦርድ መመሪያ ቁጥር 3/2001 አንቀጽ 9/3/ሀ ህዝቡ በይፋ በምርጫ ቦርድ በእኩል መጠራት አለበት ይላል፤ ይሄ ህግ በዘንድሮው የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ላይ ተፈፃሚ አልሆነም። 
ሌላው በመመሪያው አንቀፅ 7/3 የህዝብ ታዛቢዎች ሲመረጡ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በምርጫ ቦርድ በይፋ መጋበዝ አለባቸው ቢልም ፅድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ እንደሚባለው በመላ ሀገሪቱ ምርጫው ሂደት ለመታዘብ የተሰማሩ አባላቶቻችን በፀጥታ ኃይሎች ለእስርና እንግልት ተፈፅሞባቸዋል፤ በዚህ ምክንያት በዕለቱ በተለያዩ አከባቢዎች ከአንድነት ፓርቲ ብቻ ከአስራ ስድት አባላት በላይ በፖሊስ ለሰዓታት ታግተዋል። ከዚህ የምንረዳው ተወዳዳሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በህዝብ ታዛቢ ምርጫ ላይ እንዳይገኙ ተፈልጓል ማለት ነው፤ ይህ ደግሞ በዕለቱ የተፈፀሙትን እጅግ በጣም አሳፋሪና ህገወጥ ተግባራት በቦታው ተገኝተው እንዳይታዘቡ ለማድረግ ነው ካልሆነ ሌላ ምክንያት ሊኖረው አይችልም።
ከሁሉም ነገር በላይ የህዝብ ታዛቢ ምርጫው አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ በበርካታ አከባቢዎች ምንም ዓይነት ምርጫ ያልተካሄደ መሆኑ ነው፤ በ2002 ምርጫ ታዛቢ የነበሩ ሰዎች እንዳሉ ለዘንድሮው የ2007 ምርጫም ታዛቢ እንዲሆኑ በጅምላ እንዲፀድቅላቸው የማደረጉ ጉዳይ ነው፤ በዚህ ምክንያትም በአሁኑ ሰዓት በአከባቢው የሌሉና የሞቱ ሰዎችም ጭምር የህዝብ ታዛቢ ሆነው የተመረጡበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ለምሳሌ በአዲስ አበባ በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 6 ምርጫ ሳይደረግ የቀድሞ የምርጫ ታዛቢዎች ነው በንባብ ስም ዝርዝራቸው የተገለፀው። ምርጫ እንዳዲስ በተካሄደባቸው ቦታዎችም ቢሆኑ በመመሪያው መሰረት አስር አስር እጩዎች ለእያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ መቅረብ ሲገባው አምስት ሰው ዝም ብሎ በቀጥታ እየተጠቆሙ እንዲያልፉ መደረጉ ይሄም የቦርዱን መመሪያ አንቀጽ 9/4መ የሚጥስ ሆኖ አግኝተነዋል። በእነዚህ የምርጫ አዳራሾች የነበረው ምርጫ ሁኔታ ጠቋሚውም፤ ተጠቋሚውም አንድ ለአምስት በቀበሌና በጎጥ ከተደራጁት ውስጥ መሆኑ ሂደቱ እጅግ አሳፋሪና ተስፋ አስቆራጭ እንዲሆን አድርጎታል።
በአንዳንድ አከባቢዎች የምርጫ ቦርዱ ሰዎች በሌሉበት በቀበሌ አመራሮች የህዝብ ታዛቢ ምርጫው የተካሄደበትም ሁኔታ አጋጥሞናል፤ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆነን በአዳማ ቀበሌ 01 የተካሄደው ነው። የታዛቢዎች ምርጫ ያስፈፀሙት አቶ በዳዳ የተባሉ የቀበሌው ሊቀመንበር ናቸው። እንደዚሁም በደብረ ሲና ከተማ ምርጫውን ያስፈፀሙት የከተማው አፈ-ጉባዔ አቶ ፍቃዱ ሙላት ናቸው።
በሌሎች አከባቢዎች ደግሞ ጭራሽ ምርጫው ያልተካሄደባቸው ቦታዎችም እንደነበሩ የደረሱን ሪፖርቶች ያመለክታሉ። ለምሳሌ በደቡብ ክልል በአማሮ ወረዳ ምንም ዓይነት የህዝብ ታዛቢ ምርጫ አልተካሄደም። እንደዚሁም በዕለቱ እሁድ ወደ ቀበሌ የሄዱ ሰዎች ምርጫው ትናንት ታህሳስ አስር ነው የተካሄደው ተብለው የተመለሱ ነዋሪዎችችም አጋጥሞናል። ለምሳሌ በአዳማ ቀበሌ 06 የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ተካሂዷል የተባለው በታህሳስ 11/04/2007 ዓ.ም. ነው። እንደዚያም ሆኖ ምርጫው ተካሄዷል በተባለው በዕለት ይካሄድ አይካሄድ ማረጋገጥ አልተቻለም።
በዘንድሮ የተካሄደው የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ጠቅለል አድርገን ስናየው፤ የህዝብ ታዛቢ ምርጫ ተካሄዷል ማለት የሚቻል አይደለም። ይሄ ሁኔታ በዘንድሮ የሚካሄደው የ2007 ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ገለልተኛና ተኣማኒ እንደማይሆን ከወዲሁ የሚያረጋግጥ ነው። አንድነት ቀድሞም ቢሆን ምርጫ ቦርድን ተማምኖ አይደለም ወደ ምርጫው ለምግባት የወሰነው፤ በመሆኑም ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ እያጋለጠ በህዝባዊ ንቅናቄ ህዝቡን አደራጅቶ ትግሉን በቆራጥነት ለመምራት ያለው ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ ይወዳል። አሁንም ቢሆን አንድነት ነፃና ፍትሀዊ ምርጫ እንዲደረግ ህዝቡ ተገቢውን ተፅዕኖ ያደርግ ዘንድ ከፓርቲው ጎን እንዲቆምና ተደራጅቶ ለለውጥ እንዲታገል ጥሪያችንን እናቀርባለን።
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ታህሣሥ 16 ቀን 2ዐዐ7 ዓም
አዲስ አበባ

የፀጋዬ በርሔ ቪላ ተሸጠ – ከኢየሩሳሌም አረአያ

woyane
የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትና በኋላ የፌዴራል ደህንነት ዋና ባለስልጣን የሆኑት የሕወሐት ፖሊት ቢሮ ባል አቶ ፀጋዬ በርሄ በመቀሌ ልዩ ስሙ “አፕርታይድ መንደር” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ያስገነቡት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ ቪላ መሸጣቸውን ታማኝ ምንጮች አረጋገጠዋል። 10 ሚሊዮን ብር ገደማ እንደፈጀ የሚነገርለት የአቶ ፀጋዬ ቪላ ለአንድ ባለሃብት 25ሚሊዮን ብር እንደተሸጠ ቢነገረም በትክክል የተሸጠበትን ዋጋ ማወቅ እንዳልተቻለ ምንጮቹ አስታውቀዋል። ፀጋዬ በርሄ የቅዱሳን ነጋ ባለቤት ሲሆኑ ቅዱሳን የስብሃት ነጋ ታናሽ እህት ናቸው።የመቀሌ ነዋሪ “አፓርታይድ መንደር” የሚል ስያሜ በሰጠው በዚህ ቦታ ከአቶ ፀጋዬ በርሄ በተጨማሪ አቦይ ስብሃት ነጋ በራሳቸውና በመጀመሪያ ልጃቸው ስም ሁለት ቪላዎችን ሲያስገነቡ ቴዎድሮስ ሃጐስ፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጎበዛይ ወ/አረጋይ፣ ተክለወይኒ አሰፋ ዘመናዊ ቪላዎችን ካስገነቡ የሕወሐት ባለስልጣናት ሲጠቀሱ ኪሮስ ቢተው በሰባት ሚሊዮን ብር ወጪ በዚሁ ስፍራ ያስገነቡትን ቪላ ከ9 ወራት በፊት መሸጣቸውን ምንጮቹ አስረድተዋል። በሌላም በኩል የቀድሞ አየር ሃይል አዛዥ የነበሩት የሕወሐት አባል ጄ/ል አበበ ተ/ሃይማኖት (በቅፅል ስማቸው ጆቤ) በቦሌ ያስገነቡትን ቪላ በ24 ሚሊዮን ብር መሸጣቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል። - See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/3168#sthash.11SeBtRt.dpuf

Mittwoch, 24. Dezember 2014

በነ ሀብታሙ አያሌው የክስ ጉዳይ የተሰየመው ችሎት ‹አስገራሚ› ውሎ ∙ተከሳሾቹ ‹‹ዘረፋ›› ተፈጽሞብናል ብለዋል


∙‹‹ለማን አቤት ይባላል?›› ሀብታሙ አያሌው
በላይ ማናዬ
ዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር፡፡ የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች ተሟልተው ፍርድ ቤት ተገኝተዋል፡፡
ችሎቱ የተሰየመው ታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ወቅት ተከሳሾች በቀረበባቸው የሽብር ክስ ላይ የሰጡትን መልስ በተመለከተ 7ኛ ተከሳሽ መልስ በዕለቱ ባለማቅረባቸው አሟልተው እንዲቀርቡ ነበር፡፡ በተጨማሪም ተከሳሾች በእስር ላይ ባሉበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሊጎበኟቸው የሚሄዱ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ወደ እስር ቤቱ ሲገቡ በተለየ መዝገብ እንዲመዘገቡ እየተደረጉ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበው ስለነበር ይህን በተመለከተ ማረሚያ ቤቱ ማብራሪያ እንዲሰጥ በታዘዘው መሰረት ማብራሪያውን ለመስማት ነበር፡፡
የተከሳሾች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች በጥየቃ ወቅት በተለየ መዝገብ ይመዘገባሉ የተባለውን አቤቱታ በተመለከተ፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በደብዳቤ መልስ መስጠቱ የተገለጸ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ‹‹ማረሚያ ቤቱ በሰጠው መልስ እስረኞች ከሌሎች በተለየ የደረሰባቸው ችግር የለም›› ማለቱን ገልጾ ይህንኑ መልስ ሙሉ ለሙሉ መቀበሉን አስታውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በዛሬው የችሎቱ ውሎ ላይ ተከሳሾች ለየት ያለ አቤቱታ በጠበቆቻቸው በኩል አቅርበዋል፡፡ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ለችሎቱ እንዳስረዱት ደንበኞቻቸው ከሌሎች በተለየ መልኩ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመባቸው ነው፡፡ አቶ ተማም አባቡልጉ በታህሳስ 12 ለ13 ቀን 2007 ዓ.ም አጥቢያ ሌሊት ስምንት ሰዓት ጀምሮ ደንበኞቻቸው ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጎ የግል ማስታወሻዎቻቸው፣ ገንዘብ እና በተከሰሱበት ጉዳይ ላይ እያዘጋጁት የነበረው መቃወሚያና መከራከሪያ ተወስዶባቸዋል ብለዋል፡፡
‹‹ደንበኞቼ ላይ እየተደረገ ያለው ጉዳይ ለህይወታቸውም የሚያሰጋቸው ነው፡፡ በማረሚያ ቤቱ በሌሊት ፍተሻ ያደረጉባቸው ሰዎች ቀደም ሲል በምርመራ ወቅት ‹ህገ-ወጥ› ተግባራት ሲፈጽሙባቸው የነበሩ የፌደራል ፖሊስና የደህንነት አባላት ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ሰዎች ደንበኞቼ ያውቋቸዋል፡፡ ስለሆነም ፍተሻው የተከናወነው በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች አልነበረም ማለት ነው፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው የተለየ የስም ዝርዝር ተይዞ ከሌሎች በተለየ መልኩ ነው፡፡ ለአብነት ደንበኞቼ አቶ አብርሃ ደስታና በሌላ የክስ መዝገብ የተከሰሰው አብዱራዛቅ አክመድ ላይ የሆነው ከሌሎቹ በተለየ መልኩ ነው፡፡ ፍተሻው ስለት ነገር አልያም ሌላ ህገ-ወጥ ቁሳቁስ ለመያዝ የተደረገ አለመሆኑን ከተወሰዱት ንብረቶች ማየት ይቻላል›› ሲሉ አቶ ተማም ለፍርድ ቤቱ በደንበኞቻቸው ላይ የተፈጸመውን ድርጊት አስረድተዋል፡፡
ይህን በተመለከተ አስተያየት የሰጡት የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው፣ ‹‹ማረሚያ ቤቱ መንግስት ዜጎች ታንጸው እንዲወጡ ያሰራው ነው፡፡ ይህን አሰራር ለመጠበቅም የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር የተለያዩ ስራዎችን ሊሰራ ይችላል፡፡ እየቀረበ ያለው አቤቱታም ከዚህ አኳያ መታየት ያለበት ነው›› ብለዋል፡፡
ጠበቃ ተማም የደንበኞቻቸውን አቤቱታ ከህግ አንጻር ያስረዱ ሲሆን፣ ‹‹በመሰረቱ ፍተሻ ሊካሄድ መቻሉ ላይ አይደለም አቤቱታው፡፡ የተካሄደው ፍተሻ ግን ህገ-ወጥ ነው፤ ምክንያቱም ፍተሻው የተከናወነበት ሰዓት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ባለው ጊዜ ሳይሆን ሌሊት 8 ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ይህ ህገ-ወጥ ነው፡፡ በሌላ በኩልም ፍተሻው በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች አይደለም የተከናወነው፡፡ በደህንነቶችና የፌደራል ፖሊሶች ነው ፍተሻው የተደረገው፡፡ ይህም ማረሚያ ቤቱ ደንበኞቼን ለመጠበቅ ፍላጎቱም ሆነ ብቃቱ እንደሌለው ያሳያል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ይህን መሰል ድርጊት የፈጸሙት አካላትና በማን ትዕዛዝ እንደተፈጸመ ምርመራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ እንዲሰጥልን እንጠይቃለን›› ብለዋል፡፡
ጠበቃ ተማም በተጨማሪ ከደንበኞቻቸው ላይ በፍተሻው ወቅት የተወሰዱባቸው ንብረቶችና ማስታወሻዎች እንዲመለሱላቸው ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው አመልክተዋል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ‹‹የተለየ ከፍተኛ በደል ደርሶብኛል›› በሚል ለፍርድ ቤቱ እንዲያስረዱ ዕድል እንዲሰጣቸው ጠይቀው የነበሩት 3ኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ሺበሺ የጠየቁት የመናገር እድል ሳይፈቀድላቸው ቀርቷል፡፡
በጠበቆቹ አማካኝነት የቀረበው አቤቱታን በተመለከተ ችሎቱ አስተያየት የሰጠ ሲሆን በተለይ ጠበቃ ተማም አቤቱታውን ባቀረቡበት ወቅት ‹‹ማረሚያ ቤቱ ደንበኞቼን ለመጠበቅ ፍላጎትም ብቃትም የለውም›› ያሉት አገላለጽ ተገቢ ስላልሆነ እንዲታረሙ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በቃል የገለጹት የመሐል ዳኛው፣ ‹‹እንዲህ አይነት አገላለጽ ማረሚያ ቤቱ የበቀል እርምጃ እንዲወስድ የሚገፋፋ እንዳይሆን…›› በማለት ሌላ አስገራሚ መነጋገሪያ ከፍተዋል፡፡
ይህን የዳኛውን ንግግር ተከትሎ 2ኛ ተከሳሽ አቶ ሀብታሙ አያሌው የመናገር እድል ከተደጋጋሚ ጥያቄ በኋላ ለአጭር ጊዜ ተፈቅዶለታል፡፡ እናም፣ ‹‹እርስዎ እያሉት ያለው ነገር ተገቢ አይደለም፡፡ በህይወቴ ላይ የደህንነት ስጋት አለብኝ ነው እያልኩ ያለሁት፡፡ ይህንን ስጋቴን ለችሎት እያስረዳሁ ነው፡፡ ግን እርስዎ ‹የበቀል እርምጃ› እንዲወሰድብን ማሳሰቢያ እየሰጡ ነው፡፡ ይህ ተገቢ አይደለም፡፡ በእርግጥ አሁንም የበቀል እርምጃ እንደማይወሰድብን ማረጋገጫ የለንም፡፡ እሺ ለማን አቤት ይባላል? የደረሰብንን በደል ለፍርድ ቤት ከማስረዳት ውጭ ለማን አቤት እንላለን….አሁን እኮ ፍርድ ቤቱ ከማረሚያ ቤቱ ጋር መወገኑን ነው እያየን ያለነው፡፡ ፍርድ ቤቱ የእኛን አቤቱታ እየሰማ አይደለም፡፡ ከፍርድ ቤት ውጭ ለማን አቤት እንበል?›› ሲል አቤቱታውን በስሜት ውስጥ ሆኖ አስረድቷል፡፡
የሀብታሙን ንግግር አዳምጠው አንደኛ ዳኛ ‹‹እኛ ሳንሆን ህጉ ነው ይህን እንድንል የሚያደርገን›› በማለት አጭር መልስ ሰጥተዋል፡፡
በዚህ መልኩ ቀጥሎ የዋለው ችሎት በተከሳሾች በኩል የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ ፍርድ ቤቱ ይህን ጉዳይ የማየት ስልጣን አለው ወይስ የለውም በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት፣ እና መደበኛ ክሱን ለማየት ለታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተጥቷል፡፡