December 4,2014
(ኢ.ኤም.ኤፍ) ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ “ሽብርተኛ” ተብላ በእስር ላይ የምትገኝ ሲሆን እንደማንኛውም እስረኛ ልታገኝ የሚገባውን አመክሮ ሳታገኝ ቀርታለች:: በመሰረቱ አመክሮ የሚሰጠው አንድ እስረኛ በ እስር ቤት ቆይታው ወቅት የሚያሳየው መልካም ባህሪ ተገምግሞ ለአንድ እስረኛ ከተፈረደበት አመት ተቀንሶ እንዲወጣ ይደረጋል:: ከቤተሰብ ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ከሆነ ለርዕዮት አለሙ ሊሰጣት የነበረው የአመክሮ ቅፅ “ከጥፋቴ ታርሜያለሁ” የሚል ነው::
ከዚህ በፊትም “አጥፍቻለሁ ይቅርታ ይደረግልኝ” ተብሎ በፕሬዘዳንቱ አማካኝነት የሚደረገውን ሂደት ሳትቀበለው ቀርታ የይቅርታ ደብዳቤ አለማገባቷ ይታወሳል:: አሁን በቅርቡ ማድረግ የሚቻለውን “አመክሮ” ተቀብላ ቢሆን ኖሮ አሁን ከ እስር የምትወጣበት ወቅት እንደነበር ከቤተሰብ አካባቢ ያገኘነው ምንጭ አረጋግጧል::ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን በዚህ ጉዳይ ያነጋገራት ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኤጀንሲ የመጣ ሰው ነበር:: በውይይታቸው ወቅት “ከጥፋቴ ታርሜያለሁ” የሚለውን አባባል ለመቀበል አልቻለችም:: ምክንያቱም ሃሳቧን በጽሁፍ ስለገለጸች ነው “አሸባሪ” ተብላ የታሰረችው:: ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኤጀንሲ የመጣውም ሰው “እንግዲያው አንቺ ከጥፋቴ ታርሜያለሁ” ብለሽ የማትፈርሚ ከሆነ እኛም አመክሮ አንሰጥሽም ብሏታል::
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen