Netsanet: ተስፋየ ተስፋ ሲቆርጥ

Donnerstag, 25. Dezember 2014

ተስፋየ ተስፋ ሲቆርጥ


(ሰናይ ገ/መድህን)
ክፍል 4
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቴሌቪዥን ቀርበዉ (የቀጥታም ሆነ
የተቀረፀ)  ቃለምልልስ ከማካሄዳቸዉ በፊት ቀደም ብሎ
በቴሌቭዥንና ራዲዮ ተደጋጋሚ ማስታዎቂያ መልቀቅ የተዘወተረ
ነዉ፡፡ በተለይም ቃለምልልሱ የሚደረገዉ ከዉጭ ከሚመጡ
ጋዜጠኞች ጋር ከሆነ ማስተዋወቁ ሞቅ ደመቅ ይላል፡፡ ጋዜጠኞቹ
በቀጠናዉና ዓለምአቀፉ የወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት ጉዳይ ትንታኔ
ፍለጋ ሰዉየዉ ጋ እንደሚመጡ ተደርጎ ይራገባል፡፡ያሳብቅማልም፡፡
ያዉ 15ዓመት እንዳራገብኩላቸዉና እንደታዘብናቸዉም ሰዉየዉ ለመተንተን ወደሁዋላ አይሉም፡፡
ይደፍራሉ፡፡ ካፈርኩ አይመልሰኝ ወይንም የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም እንዲሉ ነገር ፡፡ የአንድ ሰሞኑ
የቅድመ ቃ/መ ማስታወቂያ ታዲያ ይበልጥ ትኩረትን የሳበ ሆነ፡፡ ታዋቂ ከሆኑት ኢትዮጵያዊያን
ድረገፆች መሀል ከኢትዮጵያን ሪቪዉ ጋር ቃለምልልስ  የማካሄዳቸዉ ጉዳይ ፡፡ በኤርትራ ቆይታየ ሰዉየዉ ኢትዮጵያዉያን ተቃዋሚ
ግለሰቦችን በተናጥል ከማነጋገር በቀር ከኢትዮጵያዉን ሚድያዎች ጋር ፊትለፊት ቁጭ ብለዉ አያዉቁም፡፡ ያን ጊዜ ግን በራቸዉን
ለሚዲዎች ክፍት ያደረጉ መሰሉ፡፡ ዳሩ ግን በኢትዮጵያን ሪቪዉ  ለመቅረብ በፈለጉበት ጊዜ  አንድ ነገር ግልፅ ነበር ፡፡ መገምገም ለቻለ፡፡
ይሄዉም ኤርትራ ከመሸጉት ኢትዮጰያዉያን ተቃዋሚ ሀይሎች መሃል የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ዴምህት) እየጎለበተ
መሄዱና የሌሎቹ የመፍተልተል ጉዳይ አደባባይ መዉጣቱ፤ በተለይም  በኤርትራ ከዴምህት አራት አመት በፊት ቀድሞ ግንባር ሆኖ
የተመሰረተዉ  የኢትዮጵያ ህዝቦች አርበኞች ግንባር እንደግመል ሽንት የሁዋሊዮሽ መዝረክረኩና (ስለመረጥኩት ቃል ይቅርታና በግንባሩ
ለተሰዉ ለታገሉ ለሚታገሉና ለሞከሩ ሁሉ አክብሮቴን እየገለጥኩ የሁዋሊዮሽ መፍተልተሉ ማለቴ የግንባሩን ጉዞ ይሆናል) መወነጃጀሉ
ይፋ እየሆነ መሄዱን ይጠቅሱዋል፡፡ የኤርትራ መንግስትም ከሚወነጀሉት ዋነኛዉ በመሆኑ፡፡ በኢትዮጵያዉያን ሚድያ ቀርበዉ ካንገት
ይሁን ካንጀታቸዉ ቢያስተባብሉ ምንም እንደማይከስሩ በመካሪዎች ተመከሩ እንበል፡፡ እንዲያዉም ጥቂት የዋሆችን ለወያኔ
ማሰፈራሪያነት ልንማርክ እንችላለን ይባሉም ይሆናል፡፡ ባናቱ ላይ ስለኢትዮጵያና ህዝቡዋ የሚሰጡት ገመድ ትንታኔ አለ፡፡ እናም
ቃለምልልሱ ተካሄደ ፡፡ግንባሮቹም ቀጠሉ፡፡ላሁኑ ይሄዉ ይበቃናል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ቃለምልልሱን ያካሄዱት እንደሚታወሰዉ ከሁለት ጋዜጠኞች ጋር ነበር ፡፡ ከኤልያስ ክፍሌና ከሎንዶኑ ስለሺ ጥላሁን ጋር፡፡
በድረገፅ በስም ብቻ ከማዉቀዉ ከኢትዮጵያን ሪቪዉ ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ጋር የተዋወቅሁትም በዚሁ ጊዜ ነበር፡፡ ከስለሺ ጋር ቀደም
ባለ ጉብኝቱ ተዋዉቀናል፡፡
ከጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ጋር በተለያዩ ጥቂት አጋጣሚዎች በኤርትራ በኩል ስለሚደረጉ የትጥቅ ትግል አያያዞች ጉዳይ የሀሳብ ልዉዉጥ
ያደረግን ሲሆን የኔ ድምዳሜ “ከንቱ ልፋትና መስዋዕትነት መክፈል ነዉ” የሚል ነበር፡፡ አሁንም ፡፡ ዝርዝር እማኝነቴ አሁን አያሻንም፡፡
ኤልያስ በህግደፍ ተስፋ ሰንቆ ነበር የመጣዉ፡፡ እንደተረዳሁት፡፡ ከፕሬዚዳንት ኢሳያሳ ጋር ቃለምልልስ ካካሄደ በሁዋላም በቀጠሮ ኒያላ
ሆቴል ተገናኝተን በሙያዊ የስራ ዕቅዱ ዙሪያ ያሰቡትን ሲገልጥልኝ ከዚሁ ተስፋ የመነጨ መሆኑን ተገንዝቢያለሁ፡፡ እናም ፀረ ወያኔ
የትጥቅ ትግሉን በቅርብ ለመደገፍና መረጃዎችን በቅርብ ለማስተላለፍ የኢትዮጵያን ሪቪዉ ቢሮ በአስመራ ለመክፈት እንቅስቃሴ
መጀመሩንና በዚህ ቢሮም ተስፋየ ገብረአብና እኔን እንድንሰራ እንደሚፈልግ በመግለጥ ግብዣዉን አቀረበልኝ፡፡ ስለ ህግደፍና አርበኞች
ግንባር ብዙ አሉታዊ ነገሮች ይፋ በወጡበት ጊዜ ኤልያስ ይህን እቅድ ማሰቡ ትንሽ ግራ አጋባኝ፡፡ ምን ተማምኖ ነዉ በሚል።፡”እርግጠኛ
ነህ ይሄ ነገር ይሳካል?” የግል ሚዲያ የማይዋጥላቸዉ ኢሳያስ ጉያቸዉ ዉስጥ ያዉም የአማርኛ ድረገፅ እንዲከፈት ቀና ሊሆኑ? ነባር
የህግደፍ ታጋዮችና የኢሳያስ ህቡዕ ፓርቲ አባላት (ኤማሰ)  የሚቆጣጠሩት የአማርኛዉ ኦሮሚኛ ትግራይና ሶማሌኛ  ቴሌቭዥንና ራዲዮ
ፕሮግራሞች እንዴት በሸምቀቆ እንደምንሰራ እያወቅኩ እነኤልያስን በነፃ ሚዲያነት እንዲሰሩ እንዴት ይፈቅዳሉ ብዬ ልገምት?…. ፡፡
ኤልያስ ጥርጣሬየን ተገንዝቦ “እነ ኮ/ሎኔል ፍፁም በኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚዎች አያያዝ ላይ ብዙ ነገሮችን እንዲያስተካክሉ ተነጋግረናል፤
በአጠቃላይ ፕሬዚዳንቱም አይዙዋችሁ ብለዉናል” ሲል ያገኙትን ተስፋ ባጭሩ አመላከተኝ፡፡
ቢሳካም ባይሳካም ለእሺታየ አላቅማማሁም፡፡ ምክንያቱም የሁዋላ የሁዋላ እጅ እጅ እያለኝ ከመጣዉና የማላምንበትን እየሰራሁ በመሆኔ
ህሊናየ እኔነቴን ሲጠየፈዉ እየታወቀኝ ከሄደዉ የኤርትራ ማስተወቂያ ሚ/ር ጭፍን ፕሮፓጋንዳ አካባቢ መገላገያ አገኘሁ በማለት፡፡ አንድ
ከባድ ችግር ግን ነበረ፡፡ በግል ፍላጎት ለመልቀቅ አይፈቀድልኝም፡፡ ስለዚህ ኤልያስ በዋነኛነት እንዲያነጋግር ተስማማን፡፡ ለሱ ሲሉ
http://www.ethiomedia.com/11notes/tesfaye_tesfa_seeqort.pdf

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen