Netsanet: የወያኔን የዘርኝነት አገዛዝ በመቃወም ወደ አርበኞች ግንባር የትግል ጎራ የሚቀላቀሉት የአየር ሃይል አባላት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

Mittwoch, 10. Dezember 2014

የወያኔን የዘርኝነት አገዛዝ በመቃወም ወደ አርበኞች ግንባር የትግል ጎራ የሚቀላቀሉት የአየር ሃይል አባላት ተጠናክሮ ቀጥሏል።


በአገዛዙ የአየር ሃይል ውስጥ በሰፈነው አይን ያወጣ ዘረኝነትና ብልሹ አስተዳደር ምክንያት በርካታ የአየር ሃይል አባላት አገዛዙን እየከዱ ከፊሉ ሀገር ጥለው እየኮበለሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም አራት የአየር ሃይል አባላት ማለትም፦
1ኛ, ፓይለት ዳንኤል የሽዋስ
2ኛ, ፓይለት ዳንኤል አበራ መኮነን
3ኛ, ፓይለት ጠይብ ቃዲ እና
4ኛ, ፠ ገ/ከርስቶስ ታደሰ የተባሉት የአየር ሃይል አባላት ፀረ- ወያኔ የትጥቅ ትግሉን የተቀላቀሉ መሆናቸውን በአርበኞች ድምፅ ሬዲዮ እና በሌሎችም የዜና አውታሮች መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፦ ህዳር 30/2007 ዓ.ም የFF 260 የጦር አውሮፕላን አብራሪ የነበረው ወጣት ፓይለት አዲሱ አገኘሁ ደርበው የወያኔን ብልሹ አስተዳደር በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ለመቀላቀል ችሏል።
ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ፀረ-ወያኔ የትግል ጎራ የተቀላቀለው ፓይለት አዲሱ አገኘሁ ደርበው አገዛዙን ለመክዳት የተገደደበትን ምክንያት ሲያስረዳ በመከላከያ ኢንጅነሪንግ የ3ኛ አመት ተማሪ እንደነበረ ገልፆ፦ በኢንጅነሪግ ተቋም ውስጥ እየተፈፀመ ያለው ሙስና እንዲሁም የአንድ ወገን የበላይነት የሰፈነበት የዘር መድሎ ልዩነትን መሸከም ስለመረረኝ አገዛዙን ለማስወገድ የነፃነት አርበኞችን ለመቀላቀል ወስኛለሁ በማለት ፓይለት አዲሱ አገኘሁ ገልጿል።
ወጣት ፓይለት አዲሱ አገኘሁ በአየር ሃይል ስልጠና ኮድ s.s 260 በተባለው የጦር አውሮፕላን ለ 33 ሰዓታት ያህል በአየር ላይ በመብረር የስልጠና ግዳጁን በብቃት መወጣቱን የፓይለት አገኘሁ ሰነዶች ይመሰክራሉ። ፓይለት አዲሱ አገኘሁ ደርበው የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የፓዊ ወረዳ ተወላጅ ነው።
በተመሳሳይ ዜና፦ ብዛት ያላቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን መቀላቀላቸው ታወቀ።
ሰሞኑን ግንባሩን ከተቀላቀሉት የጎንደር ዩኒቨርስቲ የB.A ተመራቂ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ቻላቸው ተክሉ ወ/ማሪያም፤ተማሪ ተስፋሁን ፈንታ እና ሌሎች የጎንደር የቴክኒክና የሙያ ማሰልጠኛና የ2ኛ አመት ተማሪዎች ፀረ-ወያኔ የነፃነት ትግሉን ተቀላቅለዋል።
እነሆ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እንደገለፁት ከድሃ ቤተሰብ ድጋፍ ተምረን በከፍተኛ ውጤት ብንመረቅም የአገዛዙ ክልላዊ መዋቅሩ እና አገዛዙ የሚከተለው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ፍልስፍናው ለስራ አጥነት ዳርጎን ቆይቷል በማለት ሰሞኑነ ግንባሩን የተቀላቀሉት ተማሪዎች በአገዛዙ ላይ ያላቸውን የጥላቻ ስሜት በቁጭት ተናግረዋል።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen