Netsanet: እምቢ በይ ባህር ዳር ! ( ሄኖክ የሺጥላ )

Freitag, 19. Dezember 2014

እምቢ በይ ባህር ዳር ! ( ሄኖክ የሺጥላ )


እንደምን አደርሽ ባህር ዳር 
ቀየሽ እንደምን ዋለ 
ልጅሽ ታቦቴን ብሎ ሰማሁ እምቢ እንዳለ ።
አንቺ የጣና ገዳም የ አባቶች ምስማክ መስበኪያ 
የመነኩሳቱ ማደሪያ የአበምኔቱ መጠጊያ።
የጻድቃን የሰማእታት 
የአበው የግዕዝ ልሳን 
መፍለቂያ የምህረት ጠበል ፣ መክተቢያ ትምህርተ ድርሳን !
አንቺ የገነት ደጃፍ የግዮን ምንጭ መፍለቂያ 
አንቺ የአጋንንት ጠር ፣ የዳቢሎስ ክንፍን መውጊያ !
ባህር ዳር የ ሙሴ ጽላት ፣ የ አምላክ ቃል ማደሪያ 
አንቺ ወለተ አርአያ ፣ ሃሌ የነብሴ መኖሪያ !
ባህርዳር የጠሎት ምድር ከመ ቀስተ ደመና 
ባህር ዳር ስላሴ ህዋድ ፣ መፍለቂያ ህብስተ መና !
አብይ ዜማሽ ሊሰበር 
ሊፈነገል ሲል ሰማሽ 
የእምናት ጉልቻሽ እንቧይ ጣይ 
ትኩስ ሬሳ አቃጣይ 
ሊሆን ሲል ልጅሽ አለ ዋይ ዋይ ዋይ !
መወድስሽ ሊፍረከረክ 
እስመ ኪያከ ይሴብሁ የሰርክ ጠሎት ሊሆን 
ውዳሴ ማርያምሽ ረክሶ 
የስብሐት ነግህ መርገፍ ዜማ ውርደቱ ረግፎ 
የታቦትሽ ማሳረፊያ ሬንጅ ሊሸከም ጀግኖ 
ጽላትሽ ጨርቁ ተገልጦ ፣ ድያቆንሽ ድምጹ በድኖ
እስከመቼ ዝም ብለሽ እስከ መቼ ሞት ተፈርቶ 
እስከመቼ ሕማማትሽ ፣ ጀግንነትሽ ማረግ ፈርቶ !
ዘበዳዊት ተነበየ ወበዩሐንስ ጥምቀት 
የታቦትሽን ማረፊያ ፣ ዝቃጭ ሬንጅ ፣ ጥቁር ጭቃ አይረፍበት !
እምቢ በይ አዋ አይሆንም 
እንኩዋን ድጉዋና ቅኔሽን 
እንኩዋን የታቦት ማደሪያ ፣ የ ማህሌት ማረፊያሽን 
እንኩዋን ኪዳን ድርሳንሽን የታቦር ዋልታ ቤትሽን 
የ ጦርሽን ሰገባ እንኩዋ ፣ ቅጫማም አይነካብሽም !
እምቢ በይ ባህር ዳር !

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen