DW
የኢትዮጵያ ፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞች የተከሰሱበትን ክስ አሻሽሎ ማቅረቡ ተነገረ። በ10 ገፆች የተካተተዉና ተሻሽሎ ቀረበ የተባለዉ ክስ፤ ፍርድ ቤቱ እንዲሻሻል በጠየቀዉ መሰረት እንዳልተሻሻለ የታሳሪዎቹ ጦማርያንና ጋዜጠኞች ጠበቃ አስታዉቀዋል።
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት፤ ኅዳር አምስት የፌዴራል አቃቤ ሕጉ በእያንዳንዱ ተከሳሽ ላይ ያቀረበዉን ክስ እንዲያሻሽልና በዝርዝር እንዲያቀርብ ጠይቆ እንደ ነበር ይታወቃል።
«በሕገ መንግሥቱ እና በስርዓቱ ላይ ያነጣጠረ የአመፅ ጥሪ ለመፈፀም በሕቡዕ ተደራጅተዉ ተንቀሳቅሰዋል» በሚል ወንጀል እስር ላይ የሚገኙት ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት ወንጀል ዉስጥ የነበራቸዉ ሚና በዝርዝር እንዲቀርብ እና ክሱ እንዲሻሻል ፍርድ ቤቱ ባሳለፈዉ ዉሳኔ፤ ዓቃቤ ሕግ አሻሻልኩ ያለዉን የክስ ዝርዝር ባለፈዉ ረቡዕ ማቅረቡ ተገልጾዋል። ይህ ክስ ግን በትዕዛዙ መሰረት እንዳልተሻሻለ የጦማርያኑ ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንን አስታውቀዋል።

ጠበቃ አምሃ መኮንን እንዳስረዱት ግን፣ ዓቃቤ ሕግ ዝርዝር በሚል ያቀረበው የክስ ማስረጃ ሰነድ ስለ ክሱ በቂ መረጃ አልያዘም። ኤዶም ካሳዬ እና ማህሌት ፋንታሁን የተባሉት ሁለቱ ሴት ታሳሪዎች ጥቂት የቤተሰብ አባላት በቀን ለአስር ደቂቃ ብቻ እንዲጎበኙዋቸው መፈቀዱን በመቃወም ለፍርድ ቤቱ ላቀረቡት አቤቱታ መፍትሄ እንደሚገኝ እንደተነገራቸው ጠበቃ አምሃ መኮንን አስታዉቀዋል።
ከታሰሩ ስምንተኛ ወራቸዉን ያገባደዱት ስድስት የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና የሶስት ጋዜጠኛ ጠበቆች ተሻሽሎ ቀረበ ለተባለዉ ክስ ታህሳስ ሰባት መልስ እንደሚሰጡም ገልጸዋል።
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen