- በእገዳው ቤተ ክርስቲያን ሕግን እንደጣሰች ቅ/ሲኖዶሱም አላዋቂ እንደኾነ ተደርጎ ተዘልፏል
- አማሳኞቹ ሐቅ ተናጋሪዎች ቅ/ሲኖዶሱ ደግሞ ጊዜ ያለፈበትን አፈና አንጋሽ ተደርጎ ተገልጧል
- የአማሳኞቹ ውንጀላ ከባድ ጥፋት ሳይኾን እንደ ‹‹ዳኅፀ ልሳንና የአፍ ወለምታ›› ተቆጥሯል
- የአማሳኞቹ ጉባኤ ሕግን የጣሰ ሳይኾን በቤተ ክርስቲያን ጠሪነት እንደተሰበሰበ ተጠቅሷል
- የውሳኔውን አፈጻጸም የሚያግደው ደብዳቤ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ግልባጭ ተደርጓል
- ብፁዕ ዋ/ጸሐፊውና ብፁዕ ጠቅ/ሥራ አስኪያጁ ከቋሚ ሲኖዶሱ አባላት ጋራ እየመከሩበት ነው
* * *
- የፓትርያርኩ የእገዳ ማስታወቂያ÷ አባ ማትያስ የቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛው ሥልጣን ባለቤት የኾነውን የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልናና አመራር አምነውና ተቀብለው ውሳኔውንና መመሪያውን ከማስፈጸም ይልቅ በግለሰብ የበላይነትና ዐምባገነናዊ አመራር ሰጭነት ለመርገጥ ያለባቸው እልክ ማሳያና ቤተ ክርስቲያናችን አማሳኞቹን መሣርያ ላደረጉ ባዕዳን ኃይሎች ተጽዕኖ ክፉኛ መጋለጧን አረጋግጧል፡፡
- የእገዳው አግባብነት÷ በራስዋ ሕግና ሥርዐት የምትመራው ሉዓላዊት ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አስተዳደርዋን በሚመለከት የበላይ ሕጓ በኾነውና ማንኛውም የቤተ ክርስቲያን ባለሥልጣን፣ አገልጋይ ሠራተኛና ምእመን ሊገዛበት፣ ሊያከብረውና ሊያስከብረው በሚገባው ሕገ ቤተ ክርስቲያን የተደገፈ አለመኾኑ የአማሳኞቹ ቡድን ፍላጎትና የባዕዳን ኃይሎቹ ስውር ሚና መገለጫ ኾኗል፡፡
- በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ድንጋጌ መሠረት ከፍተኛው መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ሕግ አውጭና ወሳኝ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ÷ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮችን በተመለከተ ለጥፋተኞችና ለበደለኞች እንደ ጥፋታቸው መጠን በቀኖና የመቅጣት፣ ምሕረትን የመስጠት፣ ይቅርታንም የማድረግ የዳኝነት ሥልጣንና ተግባር አለው፡፡
የዜናውን ተጨማሪ መረጃዎች ይከታተሉ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen