Netsanet: ኢትዮጵያ የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ የማዘጋጀት አቅሙ የለኝም በሚል ከውድድሩ ራሷን አገለለች

Mittwoch, 1. Oktober 2014

ኢትዮጵያ የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ የማዘጋጀት አቅሙ የለኝም በሚል ከውድድሩ ራሷን አገለለች

(ዘ-ሐበሻ) ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ሊቢያን በመተካት በ2017 እ.ኤ.አ ላይ 31ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ እንደሚፈልግ 3 ሳምንታት በፊት ሲሆን በኦፊሴላዊ ደረጃ ለካፍ ማመልከቻ ሳያስገባ ቆይቷል። ዛሬ ከፌዴሬሽኑ አካባቢ ያሉ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳረጋገጡት የ2017ን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ፍላጎት የማሳወቂያ ቀን ዛሬ ያበቃ ሲሆን ኢትዮጵያ በሁለት ዓመት ውስጥ ይህን ትልቅ ውድድር ለማዘጋጀት አቅም የለኝም በማለት ራሷን ከአዘጋጅነት ፍላጎት ማግለሏ ታውቋል።
addis ababa stadium
31ኛውን አፍሪካ ዋንጫ (AFCON 2017) በ2017 እኤአ ላይ እንድታዘጋጅ ተመርጣ የነበረችው ሊቢያ መስተንግዶውን የተወችው በአገሪቱ በቂ ሰላምና መረጋጋት አለመስፈኑ በፈጠረባት እክል እንደሆነ ማስታወቋን ተከትሎ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ሊቢያ ለውድድሩ የሚያስፈልጉ ስታድዬሞችን በመገንባት እንደማይሳካላት እና በአስተማማኝ ፀጥታ ውድድሩን ለማካሄድ እንደማትችል አረጋግጫለሁ በማለት ለአባል ፌደሬሽኖቹ ምትክ አዘጋጅን ለማግኘት ጥሪ አቅርቧል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ መስራች እንደነበረች በማስታወስና ባለፉት 3 ዓመታት ለ31 ዓመታት ከውድድሩ የራቀችበትን ሁኔታ በቀየረ የእግር ኳስ ለውጥ ላይ እንደምትገኝ በመግለፅ አዘጋጅነቱን ብታገኝ ይገባታል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች የነበሩ ሲሆን ከሁለት ሳምንት በፊት በአፍሪካ የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ መናሀርያነት የምትጠቀሰው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ገልፆ ቢቢሲ ሳይቀር ዘግቦ ነበር፡፡ በወቅቱ በአዲስ አበባና በባህርዳር ሁለት ዝግጁ ስታድዬሞች መኖራቸውን ለቢቢሲ የተናገሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ ሲሆኑ ፤ በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ደረጃቸውን የጠበቁ ስታድዬሞች ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑን በመጥቀስ ውድድሩን ለማስተናገድ ዝግጁ ነን ብለው ነበር፡ ኢትዮጵያ የፊፋ እና የኦሎምፒክ ስታንዳርድን የሚያሟላ እና 60ሺ ተመልካች የሚያስተናግድ ብሄራዊ ስታድዬም በአዲስ አበባ ለመስራት እቅድ እንዳላት የገለፀው የሱፕር ስፖርት ዘገባ ሶስት አፍሪካ ዋንጫዎችን ያስተናገደው የአዲስ አበባው ብሄራዊ ስታድዬምም ከፍተኛ እድሳት ተደርጎለት ለመስተንግዶ ሊደርስ እንደሚችል ጠቅሶም ነበር። ሆኖም ግን ፌዴሬሽኑ ኢትዮጵያ በሁለት ዓመታት ውስጥ እንዲህ ያለውን ነገር ለማድረግ አቅም ስለማይኖራት ውድድሩን ለማዘጋጀት የነበራትን ፍላጎት መሠረዙ ታውቋል።
ይህን ተከተሎ በወጡ አንዳንድ መረጃዎች ላይ ዘ-ሐበሻ ለመረዳት እንደቻለቸው የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ አልጄሪያ የማዘጋጀቱን ዕድል ልታገኝ ትችላለች።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen