- መኢአድ በመጪው ሰኞ አለም አቀፍ ጋዜጣዊ መግለጫ እሰጣለሁ አለ።
– የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተፈናቃዮችን እየተመላለሱ በሰብአዊነት በመርዳት እና በማጽናናት ላይ ናቸው።
– የአዲስ አበባ ሆስፒታሎች ተጎጂዎችን ለማጉላላት ያደረጉት ሙከራ በመኢአድ አባላት ጥረት ክሽፏል።
– የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ተፈናቃዮቹን እንዲጎበኙ መኢአድ ጥሪውን አቅርቧል።
– የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተፈናቃዮችን እየተመላለሱ በሰብአዊነት በመርዳት እና በማጽናናት ላይ ናቸው።
– የአዲስ አበባ ሆስፒታሎች ተጎጂዎችን ለማጉላላት ያደረጉት ሙከራ በመኢአድ አባላት ጥረት ክሽፏል።
– የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ተፈናቃዮቹን እንዲጎበኙ መኢአድ ጥሪውን አቅርቧል።
ባለፉት ሳምንታት በምእራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ ክልል በሚጤ ከተማ ከመሬት ቅርሚያ ጋር በተያያዘ በወያኔ ካድሬዎች ቀስቃሽነት ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ የተደረጉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ችግር ውስጥ በቴፒ የሚገኙ ሲሆን የተወሰኑት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በመኢአድ ቢሮ ውስጥ ተጠልለው የተጎዱት በመታከም ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።
ወደ አዲስ አበባ ከደረሱት ተፈናቃዮች እና ተጎጂዎች መካክል መኢአድ ቢሮ ሳይደርሱ ከመንገድ ላይ ታፍነው የተወሰዱ ስምንት ተፈናቃዮች በስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ጉዳዩን የሚከታተሉ የጉዳዩ ባለቤቶች በሰጡት መረጃ የታወቀ ሲሆን ሁኔታውን ለማረጋገጥ ተሞክሮ ፖሊስ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። እንዲሁም ሲፈናቀሉ ጉዳት የደረሰባቸው አዲስ አበባ የደረሱ ተጎጂዎች ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ከፍተኛ የሆነ ውጣ ውረድ በሆስፒታሎች የደረሰባቸው ሲሆን የቀበሌ መታወቂያ ወይንም የተፈናቀሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ከክልሉ አምጡ በማለት ለማጉላላት የተደረገው ጥረት በመኢአድ አባላት ብርቱ ጥረት መክሸፉ ሲታወቅ ተጎጂዎቹ ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓውል።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መኢአድ ባደረገው ጥሪ መሰረት አስፈላጊዎን ሰብአዊ እርዳታ እያደረጉ ሲሆን አሁንም የህዝቡን እርዳታ እና አጋርነት ለተጎጂዎቹ በተከታታይነት እንዲቀጥል እንዲሁም የሃገር ቢት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጎጂዎችን በመጎብኘት አጋርነታቸውን እንዲያረጋግጡ በድጋሚ መኢአድ ጥሪ አቅርቧል። በመጭው ሰኞ አለም አቀፍ ጋዜጣዊ መግለጫ በቢሮው እንደሚሰጥ ያስታወቀው መኢአድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እያደረጉ ያሉትን ሰብአዊ እርዳታ እና መጽናናት በማድነቅ በዚህ እንዲቀጥሉ የሰብአዊነት ጥሪውን አቅርቧል።
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen