ዋ/ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ: ፓትርያርኩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከቅ/ሲኖዶሱ ያጡትን ይኹንታ በአቋራጭ ለማግኘት ‘በመልካም አስተዳደር’ ስም የጠሩትን ስብሰባ ተቃወሙ!
‹‹ባላወጣነውና ባላጸደቅነው ሕግ ማኅበራትን መፈረጅና ሕገ ወጥ ማለት አንችልም፡፡››
‹‹አቡነ ጳውሎስ በአማካሪዎች ክፋት ዕድሜያቸውን አሳጥረዋል፤ ቅዱስነትዎም ያስቡበት፡፡››
‹‹ከአለቆችና ጸሐፊዎች ጋራ የተደረገው ውይይት አባቶች የተዘለፉበትና ያዘኑበት ነው፡፡››
‹‹ለእገሌ ሚኒስትር እናገራለኹ፤ ለእገሌ ደኅንነት እደውላለኹ እያሉ አያስፈራሩን!!››
/ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ/
‹‹አቡነ ጳውሎስ በአማካሪዎች ክፋት ዕድሜያቸውን አሳጥረዋል፤ ቅዱስነትዎም ያስቡበት፡፡››
‹‹ከአለቆችና ጸሐፊዎች ጋራ የተደረገው ውይይት አባቶች የተዘለፉበትና ያዘኑበት ነው፡፡››
‹‹ለእገሌ ሚኒስትር እናገራለኹ፤ ለእገሌ ደኅንነት እደውላለኹ እያሉ አያስፈራሩን!!››
/ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ/
በአዲስ አበባ ታትሞ ዛሬ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ተጠርቶ መስከረም ፳፯ እና ፳፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የተካሔደው ስብሰባ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ወቅታዊ ኹኔታ የማይገልጽ፣ መዋቅሩን ያልጠበቀ እና ጽ/ቤታቸው የማያውቀው መኾኑን በመግለጽ ተቃወሙ፡፡
የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት አስተላልፎታል በተባለው የቃል ትእዛዝ መጠራቱ በተገለጸው በዚኹ ስብሰባ÷ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመምሪያዎች ዋናና ምክትል ሓላፊዎች፣ የየመምሪያው ዋና ክፍሎች ሓላፊዎች፣ የድርጅቶች ዋናና ምክትል ሥራ አስኪያጆች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአስተዳደር ሓላፊዎች፣ የዋና ክፍሎችና የክፍሎች ሓላፊዎች፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች ዋናና ምክትል ሥራ አስኪያጆች መሳተፋቸው ተገልጧል፡፡
በ፳፻፩ ዓ.ም. በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴ መቀጣጠሉን ተከትሎ የቀድሞው ፓትርያርክ መዋቅሩን ሳይከተሉና ከቅ/ሲኖዶሱ ጋራ ሳይመክሩ ወስደዋቸው ነበር ያሏቸውን ርምጃዎች በመቃወም በወቅቱ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ የነበሩት የአኹኑ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የሰጡት ቃለ ምልልስ በማስረጃነት ተይዞ እንደሚገኝ ያስታወሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹ቅዱስነትዎ በምትካቸው ሲቀመጡ መዋቅሩን ሊጠብቁ ይገባል፤ መዋቅሩን ሳይከተሉና ከሚመለከተው አካል ጋራ ሳይመክሩ የሚሠሩት ሥራ ቤተ ክርስቲያኒቱን አደጋ ላይ የሚጥል ነው፤›› እንዳሏቸው ተመልክቷል፡፡
በ፳፻፩ ዓ.ም. በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴ መቀጣጠሉን ተከትሎ የቀድሞው ፓትርያርክ መዋቅሩን ሳይከተሉና ከቅ/ሲኖዶሱ ጋራ ሳይመክሩ ወስደዋቸው ነበር ያሏቸውን ርምጃዎች በመቃወም በወቅቱ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ የነበሩት የአኹኑ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የሰጡት ቃለ ምልልስ በማስረጃነት ተይዞ እንደሚገኝ ያስታወሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹ቅዱስነትዎ በምትካቸው ሲቀመጡ መዋቅሩን ሊጠብቁ ይገባል፤ መዋቅሩን ሳይከተሉና ከሚመለከተው አካል ጋራ ሳይመክሩ የሚሠሩት ሥራ ቤተ ክርስቲያኒቱን አደጋ ላይ የሚጥል ነው፤›› እንዳሏቸው ተመልክቷል፡፡
ዋና ሥራ አስኪያጁ ‹‹ውድቀት እንዳይደረስብዎ አማካሪዎችዎ ሊያዝንልዎ ይገባል፤›› ማለታቸውን የገለጹት የስብሰባው ተሳታፊዎች አያይዘውም ‹‹ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በአማካሪዎቻቸው ክፋት ከዕድሜያቸው ዐሥር ዓመት አሳጥረዋል፤ እርስዎም በአማካሪዎችዎ የተነሣ ዕድሜዎ እንዳያጥር ያስቡበት፤›› ሲሉ መምከራቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ውይይቱን በሰብሳቢነት የመሩት ፓትርያርኩ፤ ‹‹በሥራ ባለመታገዛቸውና ብቻቸውን በመኾናቸው›› ስብሰባውን ወደ ታች ወርደው ለመጥራት እንደተገደዱ አስረድተዋል፡፡ ፓትርያርኩ ባቀረቡት በጽሑፍ የተደገፈ ገለጻ÷ በቤተ ክህነቱ የመልካም አስተዳደር ዕጦቶች እንዳሉ፣ በሙሰኝነት፣ በዘረኝነትና በአድሏዊነት የሚገለጹ የብልሹ አሠራር ሒደቶች እንደሚታዩ ዘርዝረዋል፡፡
በቤተ ክርስቲያን ስም የሚደራጁ ማኅበራትና ግለሰቦች ሕግና ደንብ እየጣሱ መዋቅሯን እየተፈታተኗት እንዳለና ከመዋቅራዊ ቁጥጥር ውጭ የሚንቀሳቀስ ሀብትና ንብረት እያካበቱ በመኾኑ አካሔዳቸው ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ጥንካሬና ህልውና ፍጹም አደጋ እንደኾነ አብራርተዋል፡፡ መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አንጻር ኹሉም የሥራ ሓላፊዎች ራሳቸውን በመፈተሽና በማጽዳት ችግሩን በዘላቂነት ለማስወገድ በሚደረግ ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፤ ያልተገባ ነው ያሉትን የማኅበራት አካሔድም ኹሉም ሊቃወመው ይገባል ብለዋል፡፡
ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ይወቁባቸው ስላሉት የአማካሪዎቻቸው ጉዳይም ‹‹አማካሪዎቼ ዓላማዬን የሚጋሩና የሚያስፈጽሙልኝ ሰዎች ናቸው፤›› ያሉት አቡነ ማቲያስ ‹‹አኹንም የምቀጥልበት መኾኑን አሳውቃለኹ፤›› ብለዋል፡፡
[በስብሰባው የተሳተፉት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአስተዳደር ዋና ክፍል ሓላፊ፣ ‹‹አንድ ጣታችንን ወደሌላው ስንጠቁም ሦስቱ ወደ እኛ እንደሚያመለክት አንዘንጋ፤›› በማለት ፓትርያርኩ ስለ ሙስናና ብልሹ አሠራር፣ ስለ ጎጠኝነትና ብኩንነት፣ ፍትሕን ስለማጉደልና ንጹሑን ሰው ስለመበደል፣ ስለ ትጋት ማነስና አባቶችን ስለ መከፋፈል፣ ለምእመናን መልካም አርኣያ ስላለመኾንና ለሀገር አለመቆርቆር ሌሎችን ሲገሥጹና ሲኰንኑ ስለራሳቸውና ስለከበቧቸው አማካሪዎቻቸውም እንዲያስቡበት አስታውሰዋቸዋል፡፡]
‹‹ብቻዬን ነኝ፤ በሥራም አልታገዝኹም›› ለሚለው የፓትርያርኩ ወቀሳ ‹‹ቅዱስነትዎ አዝዘው ምን ያልተፈጸመ ነገር አለ?›› በሚል ምላሽ የሰጡት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹ያልተፈጸመ ነገር ካለ ለጉባኤው በይፋ ይገለጽ›› ሲሉ ጠይቀዋቸዋል፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግርና የችግሩ መገለጫዎች በርግጥም እንዳሉ ያልሸሸጉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ መምሪያዎችና ድርጅቶች የበጀት ዓመቱን ዕቅድ በማውጣት፣ የክንውን ሪፖርት በአስተዳደር ጉባኤ በየወቅቱ እንዲያቀርቡ፣ ድክመቶች እንዲስተካከሉና ጠንካራ ጎኖች ታቅበው እንዲቀጥሉ መደረጉን በመግለጽ በፓትርያርኩ ጽሑፍ የቀረቡትን መረጃዎች ወቅታዊነት ሞግተዋል፡፡
በልማት ተግባራትና በሠራተኞች አያያዝ ባለፈው በጀት ዓመት የተፈጸሙ ተግባራትን የዘረዘሩት የጽ/ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አባ ኃይለ ማርያም መለሰ በበኩላቸው፤ በጥናት በተደገፉና ቀጣይነት ባላቸው የመልካም አስተዳደር ማሻሻያዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችና የተጉላሉ ባለጉዳዮች አለመኖራቸውን ገልጸዋል፡፡ ምክትል ሥራ አስኪያጁ አክለውም፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን የፋይናንስ ፖሊሲና የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት ዘመናዊ ለማድረግ ዝግጅቱ መጠናቀቁን ጠቁመው ፓትርያርኩ በገለጻቸው የተጠቀሙባቸውን የችግር መግለጫዎችን አግባብነት እንደጠየቁ ታውቋል፡፡
መንግሥት የሲቪል ማኅበራትን የሚከታተለው ሕግ አውጥቶና ተቋም መሥርቶ መኾኑን፣ በሕጉ እገዛለኹ ያለ አብሮ እንደሚጓዝ፣ በሕጉ አልተዳደርም ያለ እንደሚወጣ የተናገሩት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ቤተ ክርስቲያን ግን መንፈሳውያን ማኅበራት የሚቋቋሙበት ሕግ እንዳላወጣችና የምታቅፍበት መዋቅር እንዳልዘረጋች ገልጸዋል፡፡ በአገልግሎት ላይ ያሉትን መንፈሳውያን ማኅበራት በሕገ ወጥነትና በመዋቅር ባለመታዘዝ ለመጠየቅና ለመፈረጅ ሕጉን አውጥቶ በሥራ ላይ ማዋሉ መቅድም እንዳለበት በማስገንዘብ የፓትርያርኩን ግምገማና አፈራረጅ እንደተገዳደሩት ተጠቅሷል፡፡
በተያያዘም የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ሓላፊና ከቀንደኛ አማሳኞች ኃይሌ ኣብርሃና ዘካርያስ ሐዲስ ጋራ በመኾን ስብሰባዎቹን ያስተባበረው የመዝባሪዎች አለቃ ኤልያስ ኣብርሃ፣ ‹‹ማኅበሩ ለሕግ የማይገዛና የማይታዘዝ ነው፤›› እያለ ስሙን ለይቶ ሳይጠራ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሰነዘረው ውንጀላ የብዙኃኑን የስብሰባውን ተሳታፊዎች ተቀባይነት እንዳላገኘ ተመልክቷል፡፡
በኹኔታው የተበሳጨው የሚ/ር ሺፈራው ቤተኛ ኤልያስ ኣብርሃ፣ ‹‹እንዴት ሕገ ወጥ አይደለም ትላላችኹ? አክራሪነትና ጽንፈኝነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አለ የሚባለው ከማኅበሩ ጋራ በተያያዘ ነው፤›› የሚል በእብሪትና ተንኰል የተሞላ ክሡ የስብሰባው የጋራ የአቋም መግለጫ ኾኖ እንዲወጣ አካሉ እስኪንዘፈዘፍ እየተወራጨ ያደረገው መፍጨርጨር በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ የሰከነ ምከታና ማኅበሩ እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነቱ በጥናት የታገዘ ምላሽ እንዲሰጠው በሚያሳስቡ የሥራ ባልደረቦቻቸው ጥረት እንዳልተሳካ ታውቋል፡፡]
በሌላ በኩል ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹ለኢትዮጵያ በረሓ ወርደው፣ ብረት አንሥተው የታገሉትና ዋጋ የከፈሉት ኹሉም ሕዝቦች ናቸው፤›› ብለው እንደተናገሩ የስብሰባው ተሳታፊዎች የጠቀሱ ሲኾን፣ ‹‹ሕገ መንግሥት ለኹሉም እኩል ነው፤ ለእገሌ ሚኒስትር እናገራለኹ፤ ለእገሌ ደኅንነት እደውላለኹ እያሉ አያስፈራሩን፤›› በማለት ፓትርያርኩን እንዳሳሰቧቸውም ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡
አቡነ ማትያስ በዚኹ ሳምንት ማክሰኞ፣ ከቋሚ ሲኖዶሱ ጋራ ሳይመክሩ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአድባራትና ገዳማት አለቆችና ጸሐፊዎች ጋራ ባደረጉት ስብሰባ፣ ማኅበረ ቅዱሳንን ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጋራ ደርበው በሚወነጅሉ አንዳንድ አማሳኝ አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች ብፁዓን አባቶችን ማዘለፋቸውን የጠቀሱት አቡነ ማቴዎስ፣ በዚኽም ኹሉም አባቶች ቅሬታ እንደተሰማቸውና እንዳዘኑባቸው በግልጽ ነግረዋቸዋል፡፡
ፓትርያርኩ ዓመቱን በሙሉ በየደረጃው እቀጥልበታለኹ ባሉት ስብሰባ÷ አጀንዳዎች መዋቅር ሳይጠብቁ፣ ጥናት ሳይደረግባቸውና ሳይብላሉ ውይይቱ ለሚዲያዎች ዘገባ ክፍት መደረጉ ቤተ ክርስቲያኒቷን ለአላስፈላጊ የውጭ ተጽዕኖና ለአጉል ትችት እንደሚያጋልጣት በተሳታፊዎች አስተያየት ተተችቷል፡፡
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen