Netsanet: በጋምቤላ ክልል የተፈናቀሉ እና ከዘር ማጥፋቱ የተረፉ አማሮች ወደ መኢአድ ቢሮ መጡ!

Freitag, 3. Oktober 2014

በጋምቤላ ክልል የተፈናቀሉ እና ከዘር ማጥፋቱ የተረፉ አማሮች ወደ መኢአድ ቢሮ መጡ!

ተስፋሁን አለምነህ
በፋሽሽቱ ወያኔ ከጋምቤላ ክልል በግፍ የተፈናቀሉ እና ከዘር ማጥፋት ወንጀል የተረፉት አማሮች ወደ መኢአድ ጽ/ቤት መጥተዋል፡፡
10557166_289176601284451_3918092730700238932_nበጋምቤላ ክልል ሜጢ ከተማ ጎሽኔ ቀበሌ አቶ በለጠ ጌታቸው ጎጃም ቢቸና አካባቢ የመጡ የግራ እጃቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 
በዚሁ ቀበሌ ከወሎ መካነሰላም ቦረና አካባቢ የመጡ አቶ ገበየሁ ኮስትር በጀርባቸው በኩል በከፍተኛ ሁኔታ በጥይት ከተመቱ በኋላ ጥይቱ በሰውነታቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ በአካባቢው በተደረገላቸው ህክምና ጥይቱን ማውጣት ስላልተቻለ በከፋ ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ቤተሰቦቻቸው ይሙቱ ይዳኑ ምንም አይነት መረጃ ባለማግኘታቸው በጭንቀት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ ጀምበሬ ኮስትር፣ ወ/ሮ ሳዓዳ ተፈራ፣ ወ/ሮ ኮከቤ ኮስትር ከእነ ህፃን ልጆቻቸው በባሰ ችግር ውስጥ ሆነው ወደ መኢአድ ጽ/ቤት በመምጣት በሰቀቀን ችግራቸውን ተናግረዋል፡፡
ተፈናቃዮችና ከዘር ማጥፋት የተረፉት፤ እኛስ ከእነ ችግሩም ቢሆን የተወሰነ ድጋፍ አግኝተናል፡፡ ከዚያው የቀሩት ወንድሞቻችን ጉዳይ በእጅጉ ያሳስበናል ካሉ በኋላ ለእኛም ሆነ ለወንድሞቻችን የኢትዮጵያ ህዝብ በአሰቸኳይ እንዲደርስልን ሲሉ ተማጽነዋል፡፡


10639572_289176534617791_2977291456973500637_n
10660079_289176564617788_3322022603869885720_n10622808_289176551284456_5565999195673726435_n10635892_289176581284453_5367515463374168246_n

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen