Netsanet: ጄነራል ኃይሉ ጎንፋ ያሉበት የኦነግ ከፍተኛ አመራር ጄነራል ከማል ገልቹን ከስልጣን ማንሳቱን አስታወቀ -

Freitag, 24. Oktober 2014

ጄነራል ኃይሉ ጎንፋ ያሉበት የኦነግ ከፍተኛ አመራር ጄነራል ከማል ገልቹን ከስልጣን ማንሳቱን አስታወቀ -

kemal_gelchi በአስመራ የሚገኘውና በጀነራል ከማል ገልቹ ይመራ የነበረው ኦነግ መሪውን ከስልጣን ማንሳቱን ዘ-ሐበሻን ጨምሮ በተለያዩ ሚዲያዎች በበተነው መግለጫ አስታወቀ።
በዶ/ር ኑሮ ደደፎ፣ በምክትላቸው ብርጋዴር ጄነራል ሃይሉ ጎንፋና በአቶ ዳባ ጉተማ በኩል የበለጠ መረጃ ታገኛላችሁ በሚል የኦነግ ከፍተኛ አመራር ባወጣው መግለጫ ብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ ከስልጣን እንዲነሱ የተደረገበትን ምክንያት አብራርቷል። ዘ-ሐበሻ መግለጫውን ኦነግ የሕግ ጉዳዮችና የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ ከዶ/ር ኑሮ ደደፎ ለማረጋገጥም ችላለች።
በሌላ በኩል ከስልጣን ተነሱ የተባሉት ጀነራል ከማል ገልቹም እንዲሁ በበኩላቸው መግለጫ ሊሰጡ ይችላሉ እየተባለ ሲሆን ዘ-ሐበሻ እርሳቸውን ለማግኘት ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35658#sthash.8mJOdJ4V.LXZa258n.dpuf

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen