ኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የወያኔ ቅጥረኞችን ኢላማ ያደረገ የውስጥ አርበኞች ዘመቻ በማካሄድ በ15 ቀን ውስጥ ብቻ የሳንጃ ወረዳ ዳኛ ግዛቸው ቸኮል ጌትነት፣ የገንዳ ውሃ ወረዳ ፖሊስ ኢንስፔክተር ዮሃንስ ይግዛውና ኮንስታብል ሻንበል አበበ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ መስከረም 24 ቀን 2007 ዓ/ም ከቀኑ ሰባት ሰዓት ገደማ የገንዳ ውሃ ወረዳ የፀረ-ሽምቅ ሃላፊ ሰጠኝ ፈንታ ላይ በተወሰደ የውስጥ አርበኞች እርምጃ በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል። ይህ የወያኔ ቅጥረኛ በበረሃ ለስራ የሚንቀሳቀሱ ስራ ፈላጊዎችንና ቤተሰቦቻቸውን ሽፍታ ናችሁ፤ ለሽፍቶች ስንቅና ውሃ ታቀብላላችሁ በማለት ዜጎችን ሲያስደበድብ፣ ሲያሳስርና ሲያንገለታ የነበር ሲሆን በግንባሩ በተሰጠው ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሊመለስ ባለመቻሉ እርምጃ ተወስዶበታል።
በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የውስጥ አርበኞች እየተወሰደ ያለው የወያኔ ቅጥረኞችን የማስወገድ ዘመቻ በሕብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍን በማግኘት ውጤታማ የሆኑ ተልዕኮዎች እየተፈጸሙ ሲሆን በቦታው ላይ ያሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉት ከሆነ "በአፈ-ሙዝ ሀይል አንገታችንን አስደፍተው የኖሩትን የወያኔ ቅጥረኞች መድሃኒታቸውን አውቀናል! ከአሁን በኋላ ያለው እጣ ፈንታችን በእጃችን ነው" በማለት ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር አድርባይ የወያኔ ቅጥረኞች ከአምባገነንና ከባንዳ ኃይል ጋር በመወገን እያከናወኑ ያለውን ፀረ-ሀገርና ፀረ-ሕዝብ እርምጃ እንዲገቱ እያስጠነቀቀ በዚህ ስራችን እንቀጥላለን ያሉት ላይ ግን የሚወሰደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በጥብቅ ያሳስባል።
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen