ኢትዮጵያን ኦባንግ በብቸኝነት ወክለዋል
October 13, 2014 09:10 am By
የዓለም ባንክ ስለሚሰጠው ብድርና ዕርዳታ በተመለከተ ሊያካሂድ ያሰበው የፖሊሲ ለውጥ ሰነድ አፈትልኮ ከወጣ ጀምሮ በርካታ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚሟገቱ ዓለምአቀፍ የሲቪል ማኅበረሰቦችን ያስቆጣ ሆኗል፡፡ የፖሊሲ ለውጡ ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለው መልኩ ለታዳጊ አገራት ብድር ከመስጠት ባለፈ በተለይ አምባገነናዊ አገዛዝ በሰፈነባቸውና አገዛዞቹንም ለሚደግፉ ድርጅቶች ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ገንዘብ መስጠትን የሚፈቅድ ነው፡፡
በዚህ አሠራር መሠረት ማንኛውም ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ለማድረግ የሚፈልግ ድርጅት ወደ አንድ ታዳጊ አገር ለመሥራት በሚፈልግበት ጊዜ ባንኩ ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ሳይጠይቅ ብድር ይፈቅድለታል፡፡ ሆኖም ድርጅቱ በዚያ ታዳጊ አገር ላይ የሰብዓዊ መብቶችን በመርገጥ፣ ከአምባገነናዊ ሥርዓቶች ጋር በመመሳጠር የፈለገውን ሕገወጥ ድርጊት ቢያከናውን የሚጠይቀው አይኖርም፤ ይህም እንደ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦ ብድሩን አያስከለክለውም፡፡
ለምሳሌ፤ መሬት ያለአግባብ ቢነጥቅ፣ ነዋሪዎችን ከቦታቸው ቢያፈናቅል፣ ለስደት ቢዳርግ፣ ህጻናትን በሥራ በማሰማራት “ባርነት” ቢያካሂድ፣ … ማንኛውንም ሰብዓዊ መብቶችን የሚረግጥ ሥራ ቢሰራ ለኢንቨስትመንት እስከተንቀሳቀሰ ድረስ ባንኩ ተጠያቂ አያደርገውም፤ ብድርም አይከለክለውም፡፡ ይህ አሁን ባንኩ ካለውና በበርካቶች ከሚተቸው አሠራሩ እጅግ መረን የለቀቀ ነው፡፡
የብሪክሶችን (BRICS – Brazil, Russia, India, China and South Africa) አሠራርና አካሄድ ለማክሸፍ የተነጣጠረ ነው የተባለለት ይህ የዓለም ባንክ ፖሊሲ ለውጥ ከ750 በላይ ዓለምአቀፍ የሲቪል ማኅበረሰቦች ተቃውመውታል፤ አሠራሩ እንዲቀየርም የማሻሻያ ፖሊሲዎችን ነድፈው አቅርበዋል፤ ለሳምንት ያህል በተካሄደው ስብሰባ ላይ ለባንኩ አመራሮች ገለጻ አድርገዋል፡፡
ገና ከጅማሬው በስብሰባው ላይ በመገኘት የኢትዮጵያውያንን ድምጽ በብቸኝነት ሲያሰሙ የነበሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል የድረገጽጋዜጣ በስልክ በሰጡት አስተያየት ሳምንት የፈጀውን ስብሰባ አስረድተዋል፤ እርሳቸውም ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ ህወሃት/ኢህአዴግ እንደ ካሩቱሪ እና የሼኽ አላሙዲ ሳውዲ ስታር መሰል የንግድ ድርጅቶች ጋር በመመሳጠር በኢትዮጵያ እያደረሱ ያሉትን ግፍ ከበርካታ ማስረጃዎች ጋር የሲቪል ማኅበረሰቡ አባላት በተሰበሰቡበት ለባንኩ ከፍተኛ ኃላፊዎች በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
“የኢትዮጵያ ተወካይ የለም” እየተባለ በሚገመትበት ቦታ ሁሉበብቸኝነት አገራቸውን በመወከልና የአገራቸውን ጉዳይ ለዓለምአቀፍ መድረክ በማቅረብ በቀዳሚነት ስማቸው የሚጠራው “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ በኢትዮጵያ የሚካሄደው “የመሬት ነጠቃ” ሳይሆን “የህይወት ነጠቃ” ነው በማለት ተሰብሳቢውን የሲቪል ማኅበረሰብ ኃላፊዎች ያስደመመ፤ የባንኩ ባለሥልጣናትን አፍ ያስዘጋ መግለጫና ማብራሪያ በሳምንቱ የስብሰባ ቀናት ማቅረባቸውን ጎልጉል ያነጋገራቸው አንድ የሕንድ ሲቪል ማኅበረሰብና መቀመጫውን ሰሜን አሜሪካ ያደረገ የአካባቢ ጥበቃ ተንከባካቢ ድርጅት ተወካዮች ተናግረዋል፡፡
የስብሰባው መጠናቀቂያ ቀን በነበረው ቅዳሜ ዕለት የሲቪል ማኅበረሰቦቹ ባንኩ በተግባር ላይ ሊያውል ያሰበውን ፖሊሲ ባቀረቡት የማሻሻያ ነጥቦች መሠረት የማይቀይር ከሆነ ስብሰባውን ረግጠው እንደሚወጡ በኢሜይል በላኩት መልዕክት ገልጸው ነበር፡፡ በዚህም መሠረት ከ750 በላይ የሲቪል ማኅበረሰቦች ኃላፊዎች እንዲሁም የባንኩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት የመጨረሻ ቀን ስብሰባ ተቃሟቸውን እንዲያሰሙ ከተመረጡት መካከል ኦባንግ አንዱ ነበሩ፡፡ እርሳቸውም ከተናገሩት ውስጥ ባንኩ ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለው መልኩ፤ ስለ ሕዝብ የሚከራከሩ የሲቪል ማኅበረሰቦች እንዳይኖሩ በሕግ በተከለከለበት እንደ ኢትዮጵያ ዓይነት በህወሃት/ኢህአዴግ የተፈጠሩ የሃሰት “ሲቪል ማኅበረሰቦች” ባሉበትና እነርሱ በሚሰጡት የአንድ ወገንና አገዛዙን የሚደግፍ መረጃ ላይ በመመርኮዝ ባንኩ የሰብዓዊ መብቶችን እንዲረገጡ በመፍቀድ ፖሊሲዉን ለመቀየር የሚያደርገው አካሄድ የሚወገዝ መሆኑን በአጽዕኖት መናገራቸውን ለጎልጉል ገልጸዋል፡፡
የሲቪል ማኅበረሰቡ በገባው ስምምነት መሠረት የመጨረሻ ተናጋሪ ህንዳዊው የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካይ ሶምያ ዱታ ነበሩ፡፡ እርሳቸውም የሲቪል ማኅበረሰቡን ድምጽ የሚወክል የተቃውሞ ጽሁፍ በንባብ አሰምተዋል፡፡ በንግግራቸውም ባንኩ የበርካታ ሕዝቦችን መብት የሚገፍፉ “የልማት” ተግባራትን ሲካሂድ እንደቆየ በመጥቀስ እንዲህ ያለውን አሠራር የሲቪል ማኅበረሰቦቹ ቢቃወሙም እስካሁን የተለወጠ ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡ ሲቀጥሉም ከዚህ አልፎ አሁን ደግሞ የአሰራር ለውጥ በማድረግ እጅግ በርካታ የዓለማችን ሕዝቦች የበለጠ ስቃይና መከራ እንዲደርስባቸው ባንኩ የፖሊሲውን ለውጥ እንዳያደርግ ሲወተውቱ መሰንበታቸውን አስረድተዋል፡፡ ሆኖም ለዚህ ሁሉ ውትወታ ባንኩ ጆሮ ዳባ ማለቱ እነዚህ ሁሉ በተሰበሰቡት ከ750 በላይ የሲቪል ማኅበረሰቦችና በሺዎች እነርሱ በሚወክሏቸው ስም የባንኩን ረቂቅ የማይቀበሉ መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ በመጨረሻም የሕዝባቸውን መብቶች ለማስከበር ከዓለም ጋር እንጂ ከባንኩ ጋር እንደማይቆሙ በመናገር በውጭ ያሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞች ለመቀላቀል ስብሰባውን ረግጠው እንደሚወጡ ይፋ አደረጉ፡፡
ቀጥሎም ጥቁር የተቃውሞ ሸሚዞቻቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩት የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች በማሳየት ስብሰባውን አንድ በአንድ ረግጠው በመውጣት “መፈንቅለ ዓለም ባንክ” የተባለለትን ትዕይንት አሳዩ፡፡ ስብሰባውን የሚመሩት የዓለም ባንክ ከፍተኛ ባለሥልጣናትም በተከሰተው ትዕይንት ስብሰባውን መቀጠል ባለመቻላቸውና ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ በመሆናቸው ወሳኝ የነበረውን የዕለቱን ስብሰባ በይፋ ለመሰረዝ ተገድደዋል፡፡
ህንዳዊው በንባብ ያሰሙት ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል፡-
It is nearly 3 years that you started this current review of your safeguards on Bank investments. Affected communities and their support groups and many other CSOs from all over the world seriously & sincerely engaged with this and provided enormous amount of inputs about how the safeguard policies must be strengthened to ensure real protections for people and the planet.
Over these years, large sections of the people in poorer and developing countries faced the many threats from increasingly aggressive industrialization and extraction of ‘natural resources’, ever-more forceful evictions and land-grabs, dilution of labor rights & informalization, rapidly rising privatization of commons, discrimination against various marginalized communities. Many of these were funded partly by the World Bank Group, where affected people looked for some basic minimum levels of protection, through the instrument of safeguards and expected improvements. We have watched with rising concern that your new ‘safeguard’ proposals betrays these expectations and represent the opposite.
Instead of ensuring protection of vulnerable communities and the project affected people, your draft proposes dismantling of even existing protections that have been built over decades of hard work, hard won protections that people have fought and died for.
We cannot remain mute spectators of this regressive journey and must convey to you the rising frustration and anger amongst the many communities that are facing these impacts from Bank supported projects, and also within many people’s movements and supporting civil society groups, collectives and networks from around the world.
Even during the past few days of deliberations, we have watched with increasing dismay – the increasingly insensitive responses to the passionate appeals by cornered and distressed communities affected by bank supported projects.
We have watched the urgent pleas from our brothers and sisters from Guatemala and Cambodia – for minimum protection from rampant human rights abuses, being met with hawkish response like “not possible’. We were frustrated by the cold shouldering of the sufferings of thousands of affected families of religious minorities from the western fringe of India, even after the confirmation by your own audit mechanism, of violations of performance standards and massive impacts. And these are just a few examples.
We are also alarmed by the rising talk of the Bank venturing into riskier investments, coming from as high positions as the President! Hundreds of organizations of indigenous peoples and forest dwellers are terribly concerned with the proposed ‘opt out’ clause, and the dilution of protection hitherto given to biodiversity rich and protected areas. You also propose to venture into uncharted territory of biodiversity offsets! These are gambles more suited to a venture capital fund, not fit for a “Development Bank”, and the people of the world cannot allow this to happen.
We, the hundreds of people’s movements and organizations present here from around the world, and the many thousands we represent back in our countries, are rejecting this current draft of safeguards. The protections you now seek to dismantle, the safeguards that we fought for over decades – do not belong to you, they are not yours to throw away, they belong to the world and its vulnerable people.
In our engagements here, we have also heard a handful of saner voices from within the bank, and urge them to fight inside the system, for protecting the very rights they themselves enjoy – also for the people and communities around the world facing potential threats from this proposed dilution of protections. We strongly believe this protest action that we were compelled to take, will strengthen those voices and create a better environment for creating a really progressive safeguards policy. This will be in the interest of the bank itself, as well as for the entire world.
That is why we are forced to take this action now and join our partners in the protest outside. Today we are going out of this consultation, to defend the safeguards and to stand with the World and against the Bank that is trying to destroy it! We sincerely hope that this will help a better tomorrow, within & outside.
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen