ድርጅታችን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ሁለተኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በድል አጠናቀቀ!!
ስልጣን የያዘው የወያኔ መንግስት የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በመከተልና ኢኮኖሚውን በመቆጣጠር ለዘመናት የቆየ የህዝባችን ታሪካዊ ትስስሩንና አንድነቱን አደጋ ውስጥ ከቶታል::
በዚህ አስከፊ ሁኔታ በጠላትነት የተፈረጀው የአማራ ህዝብ ውስጥ ዋናው ተጋላጭ በመሆኑሃገራችንንና ህዝባችን ለማዳንና እኩይ ተግባሩን ለማስቆም የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን በ 2002 ዓም መመስረታችን የሚታወቅ ነው::
አዴሃን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በብዙ ውጣውረዶች እና ፈተናወች ውስጥ በማለፍ እራሱን እያጠናከረ የወያኔን መንግስት ሲዋጋ ቆይቷል:: እየተዋጋ ይገኛል::
የተጀመረውን ትግል አጠናክሮ በመቀጠል ዘመኑ የሚጠይቀውን አዲስ አደረጃጀትና የትግል ስልት በመቀየስና የነበሩ የድርጅቱ ሰነዶችን በማስተካከል ለሚመጣው ግዜ የሚመሩትን የድርጅት ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ሌሎች የስራ አስፈጻሚ አባላትን ና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ በመሰየም ጉባኤው ን በ 24_01_2007 ዓም በድል አጠናቋል::ይህም ድርጅታችን ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን የሚያሳይ ነው::
የኢትዮጲያ ህዝብ ሆይ
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ዘረኛው እና አምባገነኑን የወያኔ ስርዓት ለማስወገድ የሚያደርገውን ትግል ይሁን ከሚመስሉት ድርጅቶች በመዋሃድ የሚያደርገው ትግል የመኖር እና ያለመኖር ትግል መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ኢትዮ ጲያዊ ከጎ ናችን እንዲሰለፍ ጥሪያችን እናስተላልፋለን::
ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!!
የአዴሃን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
መስከረም 30 _2007 ዓም
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen