ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ንብረትና ቤት አልባ አድርጎ በአንጻሩ ደግሞ በውጭ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ በአገሩ ውስጥ ያለውን አፋኝና አምባገነን አገዛዝ እንዳይታገል ለማድረግ በርካታ የማታለያና የማደናገሪያ ዘዴዎችን ይጠቀማል። ከነዚህም ዘዴዎች አንዱ በውጭ የሚኖረውን (ዲያስፖራውን) አገር ውስጥ ካለው ወገኑ በሚነጠቀው ቦታ ላይ ቤት እንዲሰራና በዚህም ምክንያት የወያኔ ደጋፊና ተላላኪ እንዲሆን ማድረግ ነው። የዚህ የወያኔ መሠሪነት አብዛኛው በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የተገነዘበ ቢሆንም ጥቂቶችን ግን ከወያኔ ወጥመድ ውስጥ ከመግባት አላመለጡም። ከነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ በጭፍን ዘረኝነት ተለክፈው ለአገዛዙ ድጋፍ የሚሰጡ የአንድ አካባቢ ተወላጆች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ “ያባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ስግብግብነት ተነሳስተው ጥቅም አስክሯቸው የተሰለፉ ነው።
የወያኔ አላማ በዲያስፖራ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አገር ውስጥ ቤት ንብረት ካፈሩና ማንነታቸው ታውቆ ከተመዘገቡ ከተቃዋሚነት እራሳቸውን ያገላሉ፤ ከተቻለም ለወያኔ ወሬ ለቃቃሚ ይሆናሉ የሚል ነው። በእርግጥ ይህንን የሚያመላክቱ አንዳንዳ ተጨባጭ መረጃዎች አሉ። በውጭው ዓለም ተቃዋሚ የነበሩና ብዙ አስተዋጽኦ ሲያበረከቱ የነበሩ ወገኖች በወያኔ ማታለያ ተጠልፈው አገር ቤት ገብተው አንዲት ዛኒጋባ ሲቀይሱ፣ በአንድ ጀንበር ተቃዋሚነታቸው ቀርቶ “ከለማበት የተጋባበት” እንደሚባለው ለወያኔ ጆሮ ጠቢነትና አለቅላቂነት አለእፍረትና አለይሉኝታ ሲያካሂዱ ይታያሉ። ወያኔ በከፍተኛ ደረጃ በጀትና የሰው ኃይል መድቦ “በከተሞች መልካም አስተዳደር አቅም ግንባታ ቢሮየሕዝብ ተሳርፎና ያልተማከለ አስተዳደር ማጠናከር መምሪያ የዲያስፖራ ተሳትፎ ኬዝ ቲም“ በሚል በዲያስፖራ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ያዘጋጀው የግለሰቦች የግል መረጃ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ የወያኔ አገልጋዮች ስም ዝርዝር http://www.ethiopianreview.com/amharic/wp-content/uploads/%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%88%88%E1%8B%AB%E1%8B%A9-%E1%8A%A0%E1%8C%88%E1%88%AE%E1%89%BD-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%8A%96%E1%88%A9-%E1%8B%A8%E1%8B%88%E1%8B%AB%E1%8A%94-%E1%8A%A0%E1%8C%88%E1%88%8D%E1%8C%8B%E1%8B%AE%E1%89%BD-%E1%88%B5%E1%88%9D-%E1%8B%9D%E1%88%AD%E1%8B%9D%E1%88%AD.pdf