April 22, 2014
ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር 9 ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ይዛ ቀርባለች፡፡ በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ በፒዲ ኤፍ (PDF) ለቀናታል፡፡
ፕ/ር አለማየሁ፣ ፕ/ር መሳይ፣ አቶ ታዲዮስ ታንቱ፣ ግርማ ሞገስ፣ ታምራት ታረቀኝና ሌሎችም ጥልቅ ትንታኔ ሰጥተውባታል፡፡ ጋዜጣዋ በርዕሰ አንቀጽዋ በፋሲካው ስለ ነጻነት፣ ፍትህ፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን አስበን እንድንውል ትመክራለች፡፡
በጎንደር የሚፈርሱት 30 ሺህ ቤቶች፣ ኢትዮጵያውያን ዛሬም ‹‹አገራችሁ አይደለም ውጡ!›› እየተባሉ መሆናቸውን፣ አርሶ አደሮች መሬታቸውን ያለ ካሳ መነጠቃቸውንና ሌሎች ትኩስ ወሬዎችን አካትታለች፡፡ ሰለሞን ተሰማ ጂ ለዚህ ትውልድ ‹‹ጥራኝ ጎዳናው፣ ጥራኝ መንገዱ›› እንደሚያስፈልገው ይተነትናል፡፡
በላይ ማናዬ በአገልግሎት እጥረትና በሎሎችም ችግሮች ውስጥ ያለውን ህዝብ ‹‹አይ አንተ ህዝብ ትግስትህ!›› በሚል የችግሩን ጥልቀትና የህዝቡን በዝምታ መገዛት ያስነብበናል፡፡ ጌታቸው ሺፈራው ‹‹የዘመኑ የፖለቲካ ሰማዕታቶች››ን ስለ ፖለቲካው ፋሲካ ቅርበትና ርቀት በአንደበታቸው የሚናገሩትን ጽፏል፡፡
የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ደረጀ መላኩ ስለ ኢትዮጵያ ስትራቴጃዊ ጠቀሜታና ከአሜሪካ ጋር ስላላት ግንኙነት ጥልቅ ትንታኔ ሰጥቶባታል፡፡ ሳሙኤል አበበ ‹‹ማጅራት መችው ፖሊስም የህዝብ ነውን?›› በሚል ‹‹ፖሊስ የህዝብ ነው!›› የሚሉትን ይሞግታል፡፡ ሌሎች ጉዳዮችም ተዳስሰውባታል! [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen