April 25, 2014
ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው (ከፍርድ ቤት)
ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት….
….ወዲያው ከ-ጸሃይ መሞቅ አንደገባሁ 22 ቁጥር ቢሮ ለምርመራ ተጠራሁ።በካቴና ታስሬ ነበር የመጣሁት። ”ኣለማየሁ መርማሪ ይለወጥልኝ ትላለህ ኣለ?..”….” ምን ዓይነት መርማሪ ነው የምትፈልገው” ኣለኝ። ዝም ኣልኩት።
”ሱሪህን ኣውልቅ…’ ኣለኝ።
”አኔ ወንድ ነኝ ። ወንድ ፊት ሱርዬን ኣላወልቅም። ከፈለክ ኣውልቀው ስለው ደህንነቱ ተናዶ ምራቁን ተፍቶብኝ ሆዴን በቦክስ ኣለው። የስነ- ልቦና ጫና ስላደረስኩበት ሱሪዬን ሳያወልቀው ቀረ። አኢንስፔክተር ኣለማየሁ ተቀብሎ ጺሜን ሲነጭ፣ ኣስጮኽኝ። ”ዝም በል” ብሎ ጉሮሮዬን ሲያንቀኝ፣ ትንፋሽ ኣጥሮኝ ዝም- ኣልኩ። ፊት- ለፊት የታሰርኩበትን ካቴና ፈትቶ ወደ ሁዋላ ኣሰረኝ። ደህንነቱ ቀድሞ ጺሜን አየነጨ በ አስኪሪብቶ ጫፍ ጠቀጠቀኝ።
”ይህ …ሆ ያለው ህዝብ ነገ ዞር ብሎ ኣያይህም። ኣንተንም ህዝብህንም አናስተነፍሳችሁዋለን። ኣሁን አራስህን ብታወጣ ይሻልሃል።”
…አጄ ወደ ሁዋላ በመታሰሩ፣ ፊቴ ላይ ተገትሮ አስኪሪብቶውን የዓይኔ ብረት ጋር አያደረሰ፣ ኣሳቀቀኝ። ኣፍንጫዬ ውስጥ ከትቶ ስቃዬን ኣብዝቶታል።
አሱ ስልክ ተደውሎለት ሲወጣ፣ ኢንስፔክተር ኣለማየሁ ተቀበለኝ።መሬት ጣለኝ። ተንበርክከህ ሂድ፣ ኣለኝ። በቅጣት ጫና የበፊት ጉዳቴ አየተሰማኝ ነው።ዛሬን ኣሳርፈኝ ኣልኩት፤ ኣልተባበረኝም። ኣላዘነልኝም። መሬት ኣንከባሎ ረግጦኝ መጽሔት ያነብ ጀመር።
በመሃል ”ተነስ ቁጭ በል” ኣለኝ። ሁለት እጅ ወደ ሁዋላ ታስሮ ራስን ችሎ መነሳት ከባድ ነው። በተለይ ለደከመ ጾመኛ። ግድግዳ ተደግፌ ተነሳሁ። ወንበር ላይ ተቀመጥ ኣለኝ። ተቀመጥኩ። የሚያነበውን የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሔት፣ ጠረጴዛ ላይ ኣመቻችቶ ኣስቀምጦ ”ኣንብብ” ኣለኝ።
በሃገሪቱ የስራ ቋንቋ ነው የተጻፈው ለምን ኣንተ ኣታነበውም ኣልኩት።በጥፊ መታኝ። በራሱ ምልክት አየሰጠኝ፣ ኣንብብ ብሎ።” ነጻ ሓሳብ” በሚል ኣምድ ስር የተጻፈ ነው። ጸሓፊው አራሴው ነበርኩ። ”ሰላም ሲበዛ አራስ ያማል አንዴ?..” በሚል ርዐስ ስር የተጻፈ ነው። ፎቶ ግራፉም የ ኢሜል ኣድራሻዬም በግልጽ ተቀምጦኣል።
ለረጅም ደቂቃ ሳነበው ቆይቼ ”ድምጽህን ከፍ ኣድርግ !” ኣለና ድንገት ከሁዋላ ጆሮ ግንዴን ኣላጋው። ነፍሴንም ኣሳተው። እስከኣሁን ድረስ የግራ ጆሮዬ ለበሽታ ተዳርጓል።አዚያው ማአከላዋ ባደረኩት ምርመራም ”ጆሮህ ቁስለት ኣለው” ተብሎኣል። (ምንጭ The heartbreaking plight of journalist Yusuf Getachew in the Ethiopian hellish gulag aka ‘Maekelawi’ … በሚል ዘላለም ክብረት በትዊተር ገጹ ከለቀቀው)
ዛሬ ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው የፍርድ ውሎ
“…በመጨረሻም ኢንስፔክተር አለማየሁ በፈለገው መንገድ በገጣጠመው ቃሌ ፈርም ተባልኩ። “እኔ ከዚህ በፊት ያመንኩበትን ቃሌ አንብቤ ፈርሜያለሁ” አልኩ። አትጨቃጨቅ! ትፈርማለህ ፈርም!” ሲል ሌላ የስቃይ ምዕራፍ ለመክፈት ሲዝትብኝ “እሺ ላንብበው፤ ወይም አንብብሉኝ” አልኩ፡፡ ብድግ ብሎ “ፈርም ብያለሁ ፈርም!” አለኝ። ፈረምኩለት።
ትናንት ለፍርድ ቤት መደብደቤን በመናገሬ የከፋ ቅጣት ገጥሞኛል። ዛሬም ቃሌን ሳላምንበት፣ አስተያየቴን ሳልጠየቅበት፣ ሳላነበው፣ ሳይነበብልኝ በሐይል ተፅእኖ ውስጥ ሆኜ ፈርሜያለሁ።
ክቡር ፍርድ ቤት! በሀይል የተገኘ ቃል ፍትህ እንዳያዛባ ውድቅ እንዲደረግልኝ እጠይቃለሁ!
ክቡር ፍርድ ቤት! በሀይል የተገኘ ቃል ፍትህ እንዳያዛባ ውድቅ እንዲደረግልኝ እጠይቃለሁ!
19ኛ ተከሳሽ ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው
ለናሙና ነጻው ፕሬስ ከ 18 ዓመት በፊት
…ፍርድ ክልል ስገባ መረጡና የሳንባ በሽቶኞች ክፍል ኣስገቡኝ። አኔ ጤነኛ ነኝ። አዛ ከህዳር 21 አስከ ጥር 16/1988 ኣስቀመጡኝ። ጠቅላላ የሳንባ በሽተኛ ነው። የማይተላለፍ ቢሆን አንኩዋን የምትጠየፈው ክፍል ነው። አዛ ኣቆዩኝ። በተጨማሪ የክታብ ጋዜጣ ዋና ኣዘጋጅ የነበረውና የሮሃ ጋዜጣ ዋና ኣዘጋጅ የነበረ አዚህ ክፍል ለቅጣት ተብሎ ገብተው ነበር። ሁላችንም ጤነኞች ነን። ምድነው በሽታው መሰለህ ”ፕሬስ” ነው። ”ፕሬስ” ከሆንክ አንደ ሳንባ በሽተኛ ኣድርገው ያስገቡሃል። (ጥናታዊ ጽሁፍ-ዲማጽ )
በኣንጻሩ የኢትዮጵያ ‘ህገ-መንግስት’ ኣንቀጽ 18፣ ንዐስ ኣንቀጽ 1፣ ”ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት፣ ኢ-ሰብ ኣዊ ከሆነ፣ ወይም ክብሩን ከሚያዋርድ፣ ኣያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት ኣለው” ይላል።
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen