Netsanet: ዓለም፤ የትንሣኤ በዓል በመላው ዓለም ተከበረ

Sonntag, 20. April 2014

ዓለም፤ የትንሣኤ በዓል በመላው ዓለም ተከበረ

April 20/2014
የትንሣኤ በዓል ዛሬ በመላው አለም በሚገኙ ክርስቲያኖች ዘንድ ተከብሮ ዋለ ። በሺህዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች የበዓሉን አከባበር ለማየት በእየሩሳሌም ተገኝተዋል። ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ የትንሣኤን የቅዳሴ ስነ ስርዓት ለመካፈል 4000 የሚደርሱ አማኞች  መሰብሰባቸውን ፖሊስ አስታውቋል። የቅዳሴው ስነ ስርዓት በዚህ አካባቢ በሰላም ቢካሄድም በእስራኤል ፖሊስ እና በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ግን ግጭት ተስተውሏል።  ግጭቱ የተቀሰቀሰው የእስራኤል ፖሊስ፤ እድሜያቸው ከ50 ዓመት በታች የሆኑ ሙስሊሞች ወደ አልአቅሳ መስጊድ እንዳይገቡ በመከልከሉ ነው። በእዚህም የተነሳ ሁለት ፖሊሶች ሲቆስሉ  ድንጋይ የወረወሩ 16 ፍልስጤማውያን ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።  ምንም እንኳን የቀን አቆጣጠራቸው የተለያየ ቢሆንም የምስራቅ እና የምዕራብ የክርስትና እምነት ተከታዮች የዛሬውን የትንሣኤ በዓለ በአንድ ቀን ነው ያከበሩት። የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲስ በሮማው በቅዱስ ጵጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰበ ህዝብ ባሰሙት የፀሎት ንግግር ወደ 150 000 ሰው መገኘቱ ተገልጿል።


http://www.dw.de/%E1%8B%AD%E1%8B%98%E1%89%B5/s-11646

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen