April 21/2014
ለተከበራችሁ የኢትዮጵያ መምህራን በሙሉ!!! ለአንድ አገር ብልጽግና ትምህርት ቁልፍ ስለመሆኑ ለማንም አጠያያቂ አይደለም፡፡ ለዚህም ሲባል መንግስታት ለትምህርት የሚሰጡት ትኩረት በቀዳሚነት ቦታ ላይ ይገኛል፡፡ በአገራችን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ግን ከዚህ ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው፡፡ የትምህርት ፖሊሲ ከመቸውም ጊዜ በባሰ ሁኔታ ለእናንተ ለመምህራኖች የማያሰራ፣ ብቁ የተማረ ዜጋ የማይፈራበትና ለአገርም የማይጠቅም ሆኗል፡፡ ሁሉንም ነገር ለስልጣናቸው በሚያመች መልኩ የሚዘውሩት የወቅቱ ገዥዎች ትምህርት ከንጉሱና በደርግም ጊዜ ከነበረው በባሰ ደረጃ እንዲገኝ አድርገውታል፡፡
ውድ የአገራችን መምህራኖች፤ በአሁኑ ወቅት መምህር በደርግና በኃይለስላሴ ዘመን ከነበረው ክብር ስለመውረዱ ከእናንተ ውጭ እማኝ መጥራት አያስፈልግም፡፡ መምህራኖች በማስተማር ብቃታቸውና ትምህርት ደረጃቸው፣ በስራ ዘመናቸው፣ በአጠቃላይ ለቀጣዩ ትውልድና ለአገራቸው በሚያበረክቱት ሳይሆን ለስርዓቱ ባላቸው ቅርበትና ርቀት እንደሚመዘኑም እናንተው ራሳችሁ የምታሳልፉት የዕለት ተዕለት ጭቆና በመሆኑ ሀቁ ከእናንተ የተደበቀ አይደለም፡፡
በስራችሁ ላይ የሚደረግባችሁ ጣልቃ ገብነት ተባብሶ መቀጠሉም የአደባባይ ሚስጥር ሆኗል፡፡ የገዥው ፓርቲ ያልተማረ ካድሬ ከእናንተ የተሻለ ተጠቃሚ በሆነበት አገር መጭውን ትውልድ የምትቀርጹት እናንተ መምህራን ግን ኑሮን ለመግፋት ተቸግራችኋል፡፡ በደሞዝ ጭማሬ ስም የ70 ብር ያልበለጠ ጭማሪ ልክ እንደ ቀሪው ጭቁን የኢትዮጵያ ህዝብ በእናንተም ላይ ስርዓቱ እየቀለደ ቀጥሏል፡፡ በነጻነት ለማስተማር አለመቻላችሁና እንዲሁም የሚገባችሁን ክብርና ክፍያ ባለማግኘታችሁ ተሸማቅቃችሁ እንደምትኖሩ የታወቀ ሀቅ ነው፡፡
መምህር ለራሱ ብቻ ሳይሆን አገሩንና ቀጣዩን ትውልድም የሚቀርጽ ፈጣሪ የማህበረሰባችን ክፍል ነው፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያ መምህራን ስለ ራሳችሁ መብት እንኳ ጮኽ ብላችሁ ስትከራከሩ፣ ስታስተምሩ አይታይም፡፡ ከስርዓቱ አፋኝነት አንጻር ለእናንተ የሚከራከሩ ማህበራትም የሉም፡፡ በጣም የሚያሳዝነው በ1960ዎቹ እነዚህ ማህበራት ለአባላቶቻቸው ከመቆም አልፈው ለአገራቸው ህዝብ ድምጽ እንደነበሩ ስናስብ ነው፡፡ በዛ ዘመን ከየትኛውም ተቀጣሪ በላይ ሲከበርና ሲከፈለው የነበረው መምህር ‹‹እኔ ተጠቃሚ ነኝ!›› ብሎ የህዝቡን ችግር ጀሮ ዳባ ልበስ ብሎ አላለፈም፡፡
በአሁኑ ወቅት እናንተም ችግር ውስጥ ወድቃችሁ፣ አገራችንም በሚያሳዝን ምስቅልቅል ላይ ሆና ድምጻችሁ አይሰማም፡፡ መብታችሁ ሲነጠቅ፣ ህዝብ መብቱን ሲቀማ፣ ከቀዬው ሲፈናቀል፣ አገራችን ስትዋረድ....በርካታ በደልና ግፍ ሲደርስ ማስተማር፣ መተቸት፣ ጮህ ብሎ መናገር የነበረበት መምህር የጋን መብራት ሆኗል ማለት ይቀላል፡፡
ፓርቲያችን ሰማያዊ መምህራንን ጨምሮ የአገሪቱ ህዝብ በአሳዛኝ ጭቆና ላይ በመሆኑ የተነጠቁትን መብቶች ለማስመለስ ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ በዚህ ሰልፍ የተነጠቃችሁትን የማስተማር ነጻነት፣ ክብር፣ እንዲሁም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያጣችኋቸውን መብቶች ጮህ ብላችሁ እንድትናገሩ፣ ህዝብ መብቱን በነጻነት መጠየቅ እንደሚችል እንድታስተምሩ ጥሪ አቅርቦላችኋል፡፡ መምህር የጋን መብራት በሆነባት አገር ትውልድ ወደባሰ ጨለማና ጭቆና ማምራቱ የማይቀር በመሆኑ መምህራን የሙያም ሆነ አገራዊ ግዴታችሁን በመወጣት የእናንተንም ሆነ የቀሪውን ኢትዮጵያዊ ወገናችሁን መብት ለማስመለስ በምናደርገው የትግል ጉዞ ግንባር ቀደሙን ስፍራ ይዛችሁ ህዝብ እንድታታግሉ በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen