Netsanet: ለ24 ሰዓታት የዱንያ ግንኙነታችንን የማቋረጥና በዱዓ የመጠመድ ጥሪ!!!

Freitag, 25. Juli 2014

ለ24 ሰዓታት የዱንያ ግንኙነታችንን የማቋረጥና በዱዓ የመጠመድ ጥሪ!!!


#Ethiopia #EthioMuslims #BlackTerror#SwitchOffYourPhone #ምንሊክሳልሳዊ

ሞባይሎቻችንን ከዛሬ ሐሙስ መግሪብ እስከ ጁሙዓ መግሪብ (ለ24 ሰዓታት) እንዝጋ!

እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አላህን የምንለምንባቸው ብዙ ጉዳዮች አሉን፡፡ ከምንም በላይ እምነታችን ላይ በመንግስት ጥቃት መሰንዘር ከጀመረ አመታት ተቆጠረዋል፡፡ ጀግኖቻችን በእስር ቤት ታጉረዋል፡፡ ተደብድበናል፤ ተዘርፈናል፤ ታስረናል፤ ተሰደናል፤ ተገድለናል፤ ሌላም ሌላም ብዙ በደል ተፈጽሞብናል፡፡ ባለፈው ጁሙዓ መንግስት ሰላማዊ ትግሉን አስቆማለሁ በሚል ቀቢጸ ተስፋ የ‹‹ጥቁር ሽብር›› እርምጃ በሺዎች በሚቆጠሩ ሙስሊሞች ላይ ወስዷል፡፡ የእምነት ቤታችን ተደፍሯል፤ የእምነት አልባሳቶቻችን ተቃጥለዋል፤ አካላችን ተጎድቷል፤ በዚህ ሁሉ በደል መካከል በ27ኛዋ ሌሊት አላህን መማጸን እና ችግራችንን ለእርሱ ማቅረብ መተኪያ የማይገኝለት ታላቅ እድል ነው፡፡

በመሆኑም ይህንን የ27ኛ የረመዳን ሌሊት እና የቀኑን ጾም ታላቅ የዱዓ ጊዜ ለማድረግና አላህን በሙሉ ልባችን ለመለመን ከዱንያ ጋር ሙሉ ለሙሉ የምንቆራረጥበት የ24 ሰዓት ጊዜ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከዱንያ ሙሉ ለሙሉ የምንቆራረጠው ከነገ ሐሙስ መግሪብ ሰላት ጀምሮ እስከ ጁሙዓ መግሪብ ሰላት ባለው የ27ኛ ረመዳን የሌሊትና የቀን ጊዜ (24 ሰዓታት) ስልካችንን ሙሉ ለሙሉ ስዊች ኦፍ አድርገን በማጥፋት ሲሆን አንገብጋቢ ለሆነ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀርም ስልካችንን በሌሊቱም ሆነ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የማንከፍት ይሆናል፡፡ በዚህች የዱንያ ግንኙነታችንን ለመግታት ስልካችንን በምናጠፋባት የ24 ሰዓት ጊዜ አላህ ዱዓችንን እንዲቀበለን እና ያለንበትንም ፈተና እንዲያነሳልን እንመኛለን! 
ድምፃችን ይሰማ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen