Netsanet: የእንግሊዝ ጠበቆች የውጪ ጉዳይ ቢሮውን ውጥረት ውስጥ ከተውታል።

Dienstag, 8. Juli 2014

የእንግሊዝ ጠበቆች የውጪ ጉዳይ ቢሮውን ውጥረት ውስጥ ከተውታል።

የእንግሊዝ ጠበቆች የውጪ ጉዳይ ቢሮውን ውጥረት ውስጥ ከተውታል።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UK‬ ‪#‎Yemen‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎GInbot7‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የየመን ፕረዚዳንት እና የደህንነት ሃላፊው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፈው ለመስጠት ከደብረጺሆን እጅ አንድ ሚሊዮን ዶላር እንደተቀበሉ አውቃለሁ ያለ አንድ ግለሰብ ለካምብሪጅ የጠበቆች ቡድን ጥቆማ ከሰጠ በኋላ ጠበቆቹ የእንግሊዝ ውጪ ጉዳይ ቢሮን አጣብቂኝ ውስጥ መክተታቸው ታወቀ።
ጉዳዩን በማስርጃ አስደግፎ የያዘው የ እንግሊዝ ጠበቆች ቡድን የየመን ፕረዚዳንት በሃገሪት ከሚካሄዱ የስለላ እና የደህንነት ጉዳዮች ጋር ቀጥተኛ የሆን ግንኙነት ያላቸው ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸውን ጉድዳ ለመጨረስ የየመን ፕሬዚዳንት እና የደህንነት ሹሙ ከሌሎች ባለስልጣናቶች እውቅና ውጪ እንዲሁም ከየመን ውጪ ጉዳይ እውቅና ውጪ ይአንድ ሚሊዮን ዶላር የጉቦ ስምምነት በማድረግ አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፈው ለመስትታቸው ማስረጃዎች በበቂ ሁኔታ ተይዘዋል።
እንዲሁም በየመን መንግስት ስም የትምባሆ ፋብሪካውን ደብረጺሆን በፊርማው አጽድቆ የሰጠ ሲሆን ይህ ከትንባሆ ፋብሪካ የሚገኘው ጥቅም ለፕሬዚዳንቱ እና ለደህንነት ሹሙ በየመን መንግስት ስም እንደሚሰጣቸው ተጠቁሟል፡፤

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen