Netsanet: ለፍርድ መነሳት!

Samstag, 5. Juli 2014

ለፍርድ መነሳት!

አርአያ ተስፋማሪያም
የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ በተመለከተ ከታዘብኩት አንዱ በውጭ አገር ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተቃውሞ መግለጫ ማውጣታቸው ነበር። በቅድሚያ መታወቅ ያለበት “ለምን መግለጫ አወጡ?” ለማለት አይደለም። ነገር ግን ተቃዋሚዎች “አንድ” ሊያደርጋቸው የሚችለው ..የሰው መታሰርና መገደል መሆን የለበትም!! …ዛሬ ከገዛ አገራችን እንድንሰደድ ያደረጉን የሕወሐት/ኢህአዴግ መሪዎች..ጭራሽ ባህር ማዶ እየተሻገሩ ያሻቸውን እንዲፈፅሙ ያደረጋቸው የተቃዋሚው ተቻችሎ በሰለጠነ መንገድ ያለመጓዝ ነው። ማስረጃ ልጥቀስ፤ እዚህ አሜሪካ የሕወሐት ወንጀለኞች አሉ። የአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ ታዋቂ አባላትን በጅምላ አሰቃይቶ የገደለ የሕወሐት ወንጀለኛ ስሙን በመጥቀስ፣ ወንጀሉን በማጋለጥና ምስክሮች እንዳሉ በመግለጽ በይፋ “ተፋረዱት” በማለት መረጃ ይፋ ሆነ። በግል ከፓርቲው ሰዎች ጋር ለመነጋገር ተሞከረ። ..ምንም ምላሽ ግን አልሰጡም። የሟቾቹን ፎቶ በመለጠፍ ብቻ እንደተለመደው.. ዝምታን መረጡ። ...ይህን ማንሳት ያስፈለገው - የገዢው ፓርቲ ወንጀለኞችን በህግ ፊት ለማቆም በቂ መረጃና ማስረጃ እያለ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መጠቀም ያለመቻላቸውን ለማስገንዘብ ነው!! አዎ፤ መግለጫ ብቻ በቂ አይደለም! ሰው ያልገደለው አቶ አንዳርጋቸው..በወንጀለኞች ሲያዝ በአንፃሩ እዚህ አፍንጫችን ስር የሚንፈላሰሱ የሕወሐት ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ አልተቻለም። ተቃዋሚው ወገን ሰምቶ - እንዳልሰማ ሆነ።.. መነጋገርና መደማመጥ ያሻል። አዎ፤ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ለማቅረብ እንነሳ!! እዚህ አሜሪካ የሚኖሩ የገዢው ባለስልጣናት ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ የተጀመረ ነገር አለ። ተቃዋሚ ፓርቲዎችስ?? .. ቆም ብሎ መነጋገርና ማሰብ ያስፈልጋል። ከነአሜሪካ መንግስታት ለውጥ አይጠበቅም። የዋህነትም ነው!!..ነገር ግን ፍትህ በፍ/ቤቶች እንደሚገኝ ጥርጥር የለውም። ሕወሐት/ኢህአዴግ በቀይ ሽብር ወንጀለኞች ላይ የሚመሰርተውን ክስና ፍርድ መመልከቱ በቂ ማሳያ ይሆናል። ስለዚህም በገዢው ወንጀለኞች ላይ ለፍርድ እንነሳ!!

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen