Danawit Asemamawu
በባህርዳር ከተማ ሲካሂድ የነበረዉ የመላዉ ኢትዮጲያ ስፖርት ጨዋታወች ዉድድር ከመክፈቻዉ እሰከ መደመድሚያዉ የታየዉ የህዝቡ ንቃት ህሊና በገዥዉ ፓርቲ ኢሃዲግ ላይ ጥላዉን ያጠላና በርካታ የተሳሳቱ የስራዓቱ ሲስተም ፍሬ ምን ይመስል እንደነበር በተግባር ያሳየና ያዋረደ ትዕይንት ሁኖ አልፋል::
መጭዉ 2007 የኢሃዲግ የቅጥፈት ምርጫም ፈታኝ እንደሚሆን በህዝቡ የተስተዋሉ በርካታ ድርጊቶች የጠቆሙ ሲሆን በግልፅ ጎልተዉ የተስታዋሉትን ድርጊቶች ልዘርዝር-
በመክፈቻዉ ስነስራዓት ዉስጥ ኢትዮጲያ ከሃይለስላሲ ዘመን አሰከ ዘመነ ኢሃዲግ ምን እንደምትመስል ይተርክ የነበረዉ እንቅስቃሲ አዘል ዶክምንታሪ መታየት ሲጀመር ህዝቡ በፀጥታ ይከታተል ነበር የሃለስላሴዉ ግዜ አልፉ ወደ መንግስቱ ሃይለማሪያም ግዜ የነበርዉ ትዕይነት ሲታይ ህዝብ ግልብጥ ብሎ በመነሳትና በመጮህም ጭምር ነበር ድጋፉን ሲሰጥ የተስተዋለዉ ይህ ድርጊት በዚህ ስራዓት ላይ ያላቸዉን ጥላቻ ለመግለፅ እነደሆነ ግልፅ ነዉ፡፡
ለሁለት ሳምንት የቀጠለዉ ጨዋታ ብሄርን ማዕከል በማድረግ የተደረገዉ ፉክክር ከስፖርታዊዉ ባህል ያፈነገጠ የብሄር ጦርነትን መልክ ያዘለ ምናልባትም የሁሉም ብሄር ደጋፊወች በባህርዳር ከተማ ቢኖሩ መልኩን ቀይሮ ችግር ዉስጥ ይጥለን እንደነበር መገመት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያዉ ብሄርን ማዕከል በማደረግ የተጀመረዉ ጠብ ጋምቤላ ከአማራ ክልል ጋር ያደረጉት ጨዋታ ነበር - በአማራ ክልል ቅርጫት ካስ ቡድን ዉስጥ ከደብረብራሃን ዩንቨርስቲ የተገኘ ለአማራ ክልል ጋምቤላዊ ተሰላፊ አቻ ላቻ ሁኖ እየቀጠለ የነበረ ጨዋታቸዉን የመጨረሻ ማሸነፊያ የሆነችዉን ጎል ጋምቤላዊ የአማራ ክልል ተስላፊ በጋምቤላ ክልል ላይ ጎል በማስቆጠሩና አማራን አሸናፊ በማድረጉ የተበሳጩ የጋምቤላ ተጨዋቾች በወረወሩት ዲንጋ ልጁን በመፈንከታቸዉ የተፈጠረዉ ግጭት; በቀጣይ ደግሞ ኦሮሚያ ከአማራ ክልል ጋር ያደረጉት እግር ካስ ጨዋታ ላይ ገና ጨዋታዉ ሳይጀመር ነበር ህዝቡ ብሄር ተኮር ስድቦችን ሲወረዉር የተስተዋለዉ የዚህንም አፀፋ የኦሮሚያ ተጨዋቾች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ኦሮሚያወችም ለሰጡት ምላሽ እሚመስል መፈክር ከስቲዲየም በወረቀት የተፃፈ መፈከሮች ተመልክቻለሁ ለኔ የተመቸኝ ገለፃ ነበር !! አወ እኔ ነፍጠኛ ነኝ!! የሚል፡፡ እዚህም እዜያም ለመጭዉ ትዉልድ አስደንጋጭ የሆኑ የብሄር ዉርጂብኝን ስታስተናገድ የነበረችዉ ባህርዳር ከተማ መደምደሚያዋን ታላላቅ እንግዶቻን ጋብዛ የመዝጊያ ፕሮግራሞችን ለማሞቅ ከፍ ዝቅ ስትል የፕሪዝዳንት ሙላቱ ተሾመን ንግግር ግን ልታስተጋባ ወይም ልታሰማ አልቻለችም እጂግ አስደንጋጭ በሆነ የጩሆት ድምፅ ንግግሩን ለማቆምና ለመቀጠል አስኪቸገር ድረስ ነበር ህዝቡ በጩሆት የተቃወመዉ ይሄንንም የአማራ ክልል ቴሌቪዥን ላይ በድጋሚ ተመልክተነዋል የኢቲቪ የስፖርት ጋዜጠኛ እሁድ ጠዋት ፕሮግራማቸዉ ላይ በቀጥታ ስርጭቱ ዉስጥ ያልተገባ ባህሪወች የተስተዋሉ መሆኑን ገልፆ ነበር፡ ባህር ዳር እንዲህ በሚገርም ሁኔታ እምቢ ለመብቴ እምቤ ለሃገሪ ያለን ትዉልድ እያፈራችልን ትገኛለች፡፡

Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen