Netsanet: ሚሊዮኖች ድምጽ – ነገ ፖሊስ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ መቶዎችን ለማሰር ይዘጋጅ – የአንድነት አመራሮች

Freitag, 4. April 2014

ሚሊዮኖች ድምጽ – ነገ ፖሊስ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ መቶዎችን ለማሰር ይዘጋጅ – የአንድነት አመራሮች

April 3/2014
በአዲስ አበባ፣ በዛሬው ቀን በተደረገው ቅስቀሳ ከአምሳ ሶስት በላይ አባላትና ደጋፊዎች በሺሆች የሚቆጠሩ በራሪ ወረቀቶችን ሲያድሉ ዉለዋል። ከሃምሳ ሶስቱ ወጣቶች ስድስቱ ታስረዋል።
እስረኞችን ለማስፈታት ወደ ፖሊስ ጣቢያዎቹ የሄዱት የአንድነት የአመራር አባላት፣ ለምን እስረኞች እንደታሰሩ የፖሊስ አዛዦችን ሲጠይቁ « ሰልፉ የተፈቀደ ሰልፍ ስላልሆነ ፣ ነገሩን እስክናጣራ ነው እንጂ አላሰርናቸው» የሚል ምላሽ ተሰጧቸዋል።

«ለሰልፍ ፍቃድ አይጠየቅም። ማሳወቅ ነው የሚገባን፤ ለአስተዳደሩ፣ ለፌዴራል ፖሊስና የሚመለከቷቸው አካላት ሁሉ አሳውቀናል። የተጣሰ ሕግ የለም፡ ሕግን እየጣሳቹህ ያላችሁት እናንተ ናችሁ» ሲሉ እስረኞቹ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ፖሊስ ግን የታሰሩት ለመልቀቀ ፍቃደኛ አልሆነም። «ማትፈቷቸው ከሆነ ነገ ፍርድ ቤት በመሄድ ለምን እንዳሰራችሁ መናገር አለባችሁ» ያሉት የአመራር አባላቱ፣ «ነገ በመቶዎች የሚቆጠሩትን ፣ የአመራር አባላትን ጨምሮ ለማሰር ፖሊስ ይዘጋጅ» ሲሉ ፣ አንድነት፣ የአስተዳደሩ ሕገ ወጥ እርምጃን ተቀብሎ ዝም እንደማይል አረጋግጠዋል።
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/13798

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen