Netsanet: የበርሊን ግንብ አጥር የፈረሰበት 25ኛ ዓመት

Sonntag, 9. November 2014

የበርሊን ግንብ አጥር የፈረሰበት 25ኛ ዓመት

እ ጎ አ ከነሐሴ ወር 1961 ዓ ም አንስቶ በርሊንን ከ ሁለት በመክፈል 28 ዓመታት የዘለቀው 15 ኪሎሜትር ርዝማኔ የነበረው የግንብ አጥር የፈረሰበት 25ኛ ዓመት ዛሬ በደመቀ ሥነ ሥርዓት ሲከበር ውሏል። ከበርሊን ውጭ ፤ በአጠቃላይ 155 ኪሎሜትር

ርዝማኔ የነበረው የድንበር አጥርም ፈርሶ ፤ ምዕራብ ጀርመንንና ምሥራቅ ጀርመንን እንዲዋካዱ አብቅቷል። የጀርመን ውሕደት፤ ለአውሮፓና ለቀሪውም ዓለም ምን ዓይነት አስተምህሮት እንዳለው የበርሊኑን ዘጋቢአችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን አነጋግረን ነበር።
ተክሌ የኋላ/ይልማ ኃይለ ሚካኤል

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen