Netsanet: ሚሊዮኖች ድምጽ – የመጋቢት 28 የአዲስ አበባዉ ሰልፍ በተያዘለት ጊዜ ይደረጋል

Donnerstag, 3. April 2014

ሚሊዮኖች ድምጽ – የመጋቢት 28 የአዲስ አበባዉ ሰልፍ በተያዘለት ጊዜ ይደረጋል

April 1/2014
«አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት፣ ዛሬ ባካሄደው ልዩ አስቸኳይ ስብሰባ መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም ‹‹የእሪታ ቀን››በሚል መሪ ቃል የተጠራው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ማወቅ ለሚገባው አካል ሁሉ የማሳወቅ ስራው የተጠናቀቀ በመሆኑ፣ የአደባባይ ቅስቀሳ ስራው ከነገ ማለትም መጋቢት 24 ቀን 2006 ዓ.ም፣ ጀምሮ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥል እና ሰልፉ በተያዘለት ቀን እንዲደረግ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አስተላልፏል» ሲሉ የአንድነት ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ያሬድ አማረ ገለጹ።
የአዲስ አበባ አንድነት ምክር ቤት ሕጉ እንደሚያዘዉ ለአዲስ አበባ አስተዳደር የማሳወቅ ደብዳቤ መጋቢት 15 ቀን ማስገባቱ አስተዳደርም በ12 ሰዓት ዉስጥ ምላሽ መስጠት ሲኖርበት፣ 48 ሰዓታት ቆይቶ መጋቢት 17 ቀን፣ «ሰልፉ ሊደረግ የተሳበው በዩኒቨሪስቲና፣ ትምህርት ቤቶችና የመንግስት መስሪያ ቤት አካባቢ ነዉ» በሚል ለሰልፉ እውቅና እንደማይሰጥ መግለጹን በስፋት ተዘግቧል።
አንድነት የሰልፉ ቀን እና ቦታ እንዲቀየር መጠየቅ እንጂ ሰልፉን መከልከል ሕግ ወጥ ተግባር እንደሆነና አስተዳደሩ በሕግ እንደሚጠየቅበት በመግለጽ ሁለተኛ ደብዳቤ ያስገባ ሲሆን፣ ደብዳቤዉ የአስተዳደሩ ሰራተኖች አንቀበልም በማለታቸው በሬኮማንዴ መላኩንም ከአንድነት የመጣው ዘገባ ይጠቁማል።
የአዲስ አበባ አስተዳደር አንድነት ላስገባው ሁለተኛ ደብዳቤ፣ ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት በአካል ምላሽ ለመቀበል ወደ አስተዳደሩ የሄዱት የአንድነት መሪዎች፣ «ምላሽ በፖስታ ቤት ልከናል» የሚል መልስ እንደተመለሰላቸው ይናገራሉ።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen