Netsanet: ሚሊዮኖች ድምጽ – የመጋቢት 28 የደሴ ሰልፍ ይደረጋል፤ በአዋሳ ግን ተላለፈ !

Donnerstag, 3. April 2014

ሚሊዮኖች ድምጽ – የመጋቢት 28 የደሴ ሰልፍ ይደረጋል፤ በአዋሳ ግን ተላለፈ !

April 1/2014
እንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ የፊታችን እሁድ መጋቢት28 ቀን 2006 ዓ.ም፣ በታላቋ የደሴ ከተማ፣ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርግ ለማረጋገጥ ችለናል። አስፈላጊው ባለስልጣናትን የማሳወቅ ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ አንድነት በደሴ እና በአካባቢዋ ያሉ ነዋሪዎች በሙሉ፣ በነቂስ እንዲወጡና ሰላማዊ ሰልፉ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።
በከተማዋም ቅስቀሳ፣ በጥቂት ቀናቶች ዉስጥ ይጀመራል ተብሎ ይገመታል።
ከስድስት ወራት በፊት፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ክፍል አንድ በደሴ ከተማ መደረጉ ይታወሳል። ከሃምሳ ሺሆች በላይ በተገኙበት የደሴው ሰልፍ፣ ለሰልፉ ጥበቃ ሲያደርጉ ለነበሩ የፖሊስ አባላት የፍቅር መግለጫ አበባ እንደተበረከተላቸው በወቅቱ መዘገቡ ይታወቃል። እንደ ሃይቅ ከመሳሰሉ የደሴ አካባቢዎች፣ ዜጎች ወደ ሰልፍ እንዳይመጡ ፣ የባስና የታክሲ አገልግሎ እንዲቋረጥ በብአዴን ባለስልጣናት እንደተደረገ፣ ሕዝቡም ወደ ሰልፉ እዳይወጣ ማስፋራሪያ እንደደረሰበት፣ እንደዚያም ሆኖ ግን ከደሴ ነዋሪዎች አንድ አምስተኛው የሚሆነው ፣ ደፍሮ ሰልፍ በመዉጣት ለነጻነቱ ድምጹን ማሰማቱ አይረሳም።
በተያያዘ ዜና ፣ መጋቢት 28 በአዋሳ ከተማ ይደረጋል ተብሎ የታቀደው ሰልፍ ፣ ከሳምንት ወይንም አሥራ አምስት ቀናት በኋላ እንዲደረግ በፓርቲዉ መወሰኑም አክሎ የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen