Netsanet: ሚሊዮኖች ድምጽ – ሕዝቡ በራሱ አነሳሽነት እየተንቀሳቀሰ የትግሉን ግለት እየጨመረ ነው!

Donnerstag, 3. April 2014

ሚሊዮኖች ድምጽ – ሕዝቡ በራሱ አነሳሽነት እየተንቀሳቀሰ የትግሉን ግለት እየጨመረ ነው!

April 1/2014
አንድነት በቅርቡ ይፋ ባደረገው የሚሊዮን ድምጽ ንቅናቄ አሥራ አራት የተመረጡ ቢሆንም፣ ከአሥራ አራቱ ከተሞች ዉጭ ያሉ ሌሎች ከተሞችና ወረዳዎች ም «ለምን እኛ ጋር አልተደረገም ?» የሚሉ ጥያቄዎች እያነሱ እንደሆነ ይነገራል።
ከነዚህ ቦታዎች አንዱ ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ የምትገኛው የደራሼ ልዩ ወረዳ፣ የምትገኘው የጊዶሌ ከተማ ናት። በወረዳው ያሉ ነዋሪዎች ፣ «የትግሉ መሪ እኛ ነን ። እባካችሁ በአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሩንና ችግራችንን እንተንፍስ» የሚል ጥያቄ ፣ ለአንድነት አመራሮች እንዳቀረቡ የደረሰን ዜና ያመለክታል። የወረዳው አመራሮች ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የሚችል ኮሚቴ በራሳቸው አነሳሽነት እንዳቋቋሙ፣ ለአንድነት የህዝብ ግንኙነት ክፍል ያሳወቁ ሲሆን፣ ይህም በደቡብ ክልል የአንድነት የትግል ግለት ምን ያህል በጣም እየጨመረ መምጣቱን የሚያመለክት ነው።
ከአስራ ሁለት አመታት በፊት በደራሼና ዛይሴ ብሄረሰቦች መካከል በተፈጠረው ግጭት በርካታ የወረዳዋ ነዋሪዎች እንደሞቱ ይታወቃል። በወቅቱ ለዘመናት ተከባብረዉና ተፋቅረው ሲኖሩ የነበሩ ሕዝቦች መካከል ጥብ እንዲነሳ ያደረጉት የአካባቢዉ የኢሕአዴግ ባለስልጣናት እንደነበሩና የቀድሞዉ የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ በርካቶች ጥፋተኞች እንደተደረጉ ይታወሳል።
የሚሊዮኖሽ ድምጽ ንቅናቄ ክፍል አንድ በአርባ ምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ እና በደብቡ ኦሞ ጂንካ ክለተማ እንቅስቃሴዎችን ማድረጉ ይታወሳል። በሚሊዮኖች ድምጽ ክፍል እንቅስቃሴ የደቡብ ክልል ዋና ከተማ ሃዋሳን ጨምሮ፣ በጂንካ እና በሰላም በር ከተማአ ቁጫ ወረዳ እንቅስቃሴዎች ይደረጋሉ።
በአዋሳ የሚደረገዉን እንቅስቃሴ በአትላንታ ጆርጂያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ስፖንሰር የሚያደርጉ ሲሆን በቁጫ የሚደረገዉን ደግሞ የቃሌ ፓልቶክ ክፍል ስፕንሰር እንደሚያደርግ መዘገቡ ይታወቃል።

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen