April 1/2014
አቃቤ ህጉ እና ዳኛው በተደጋጋሚ ቢያንስ ከ9 ጊዜ በላይ ያቋረጧቸው ሲሆን ኡስታዝ አቡበከር ግን የኢትዬጲያን ሙስሊም ወክዬ በመሆኑ የታሰርኩት፣ህዝበ ሙስሊሙ ውክልናውን ያላነሳ በመሆኑ የህዝበ ሙስሊሙ መፍት አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆኔ ህዝበ ሙስሊሙን ወክዬ አናገራለው በማለት አስደማሚ እና አፍ የሚያዘጋ ፅሁፋቸውን ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፤
#EthioMuslim ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በሚያስገርም የተከሳሽነት ቃላቸው ፍርድ ቤቱን ሲንጡት አርፍደዋል፡፡#Ethiopia #FreedomofReligion
በዛሬው ችሎት አቃቤ ህጉ እና የመንግስታዊ ዳኞቹ መቋቋም ከሚችሉት በላይ ሆኖባቸው ሲጨናነቁ ተስተውሏል፡፡
በዛሬው ችሎት አቃቤ ህጉ እና የመንግስታዊ ዳኞቹ መቋቋም ከሚችሉት በላይ ሆኖባቸው ሲጨናነቁ ተስተውሏል፡፡
ለመጋቢት 23 ተቀጥሮ በነበረው የኮሚቴዎቻችን የፍርድ ቤት ቀጠሮ ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች ባቀረቡት የመከላከያ ጭብጥ ላይ ብይን መስጠቱነ ምንጮች አስታወቁ፡፤ ከቀረቡት አቃቤ ህጉ መቃወሚዎች መካከል የሃይማኖት ሊቃውንቶች ስለ ጀሃድ፣ስለ አህባሽ፣ስለ ሰደቃ.ስለ አዛን ትርጓሜ ለፍርድ ቤቱ እንዲያስረዱ የቀረበውን ጭብጥ ፍርድ ቤቱ ሃይማኖታዊ ጉዳዬችን አድምጦ ምንም ሊወስን ስለማይችል ከፍርድ ቤቱ የወጣ ጉዳይ በመሆኑ የቀረበው ጭብጥ ውድቅ እንዲሆን ወስኗል፡፡ በተጨማሪም ኮሚቴው ኢስላማዊ ቡድን በማቋቋም የሰራው ስራ ሃይማኖታዊ ብቻ መሆኑን ለማስረዳት የተዘጋጀውንም ጭብጥ ውድቅ አድርጎታል፡፤ በሌላ በኩልም ከኡስታዝ በድሩ ሁሴን የተገኙትን የኢሜል መረጃዎች የቴክኒካል ጊዳዬች እንዲጣሩ ተደርጎ መቅረብ እንደሚችሉ ጭብጡን ፈቅዷል፡፡በቀረበው መከላካያ ጭብጥ መሰረት በኢስታዝ በድሩ ሁሴን ውስጥ የተገኙት መረጃዎች ኡስታዝ በድሩ ሁሴን እራሳቸው የላኩት ሳይሆን ተልኮላቸው መሆኑን እና የተላከላቸውም ከታሰሩ ቡሃላ መሆኑን የአይቲ ባለሙያ ገለፃን ያካተተ ነበር፡፤ ይህንንም ፍርድ ቤቱ ተቀብሎታል ::
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በበኩሉ ዳኛውን በመቃወም አቃቤ ህጉ የኡለማ ምክር ቤትን ፈትዋ ፍርድ ቤት አቅርቦ እንደማስረጃ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ አሁን ለኛ ጊዜ ሲሆነ ለምን ይከለከላል በማለት ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡
በመቀጠልም ተከሳሾች የተከሳሽነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ዳኛው ትዕዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኑት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፍርድ ቤቱን ያስደመመ ቃላቸአውን በፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ አቃቤ ህጉ እና ዳኛው በተደጋጋሚ ቢያንስ ከ9 ጊዜ በላይ ያቋረጧቸው ሲሆን ኡስታዝ አቡበከር ግን የኢትዬጲያን ሙስሊም ወክዬ በመሆኑ የታሰርኩት፣ህዝበ ሙስሊሙ ውክልናውን ያላነሳ በመሆኑ የህዝበ ሙስሊሙ መፍት አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆኔ ህዝበ ሙስሊሙን ወክዬ አናገራለው በማለት አስደማሚ እና አፍ የሚያዘጋ ፅሁፋቸውን ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፤
ኡስታዝ አቡበከር የተከሰሱበትን ወንጀል ፈጽሜያለው አልፈጸምኩም ብለህ ተናገር ሌላ ዝርዝር አያስፈልግ ቢባሉም ከ 1 አመት በላይ በእሰር ቆይቻለው፡፡ እስካሁን ምንም ያልኩት ነገር የለም፡፡ አሁን ያለችኝ ገዜ ይሄ በመሆኑ ልታስቆሙኝ አይገባም በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የኮሚቴዎቻችን ጠበቆችም በመነሳት ህጉ በፅሁፍም ይሁን በቃል ቃላቸውን የማቅረብ መብት ሰጥቷቸዋል፡ ይህን መከልከል አትችሉም በማለት ተሟግተውላቸዋል፡፡
ኡስታዝ አቡበከር የሚያቀርቡት ፅሁፍ ረዘም ያለ በመሆኑ የምሳ ሰአት ደርሶ እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ 10 ነጥቦቸን በንባብ ለፍርድ ቤቱ ካቀረቡ ቡሃላ ከሰአት ቡሃላ የተቀረውን እንዲቀጥሉ በማለት ፍርድ ቤቱ ለከሰአት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በዛሬው ችሎት አቃቤ ህጉ እና የመንግስታዊ ዳኞቹ መቋቋም ከሚችሉት በላይ ሆኖባቸው ሲጨናነቁ ተስተውሏል፡፡ የፍርድ ቤቱን የበላይነተ ኮሚቴዎቻችን እና ጠበቆቹ ተቆጣጥረውት አርፍደዋል፡፡ ዛሬም የመሃል ዳኛውን ጨምሮ ከቀኘ በኩል ካለው ጋር አዲስ ዳኞች ናቸው በችሎቱ የቀረቡት፡፡
በችሎቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የጠገኘ ሲሆን ችሎቱ በመሙላቱ ሳብያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ከፍርድ ቤቱ ውጪ ቆሞ መጠበቅ ግድ ሆኖበታል፡፡ የችሎቱ ፀጥታ አስከባሪ ፖሊሶችም በጥሩ ሰነምግባር ጎደለ ቦታ በማየት ሰዎችን እየጠሩ ሲያስገቡ ተሰተውሏል፡፤
በችሎቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የጠገኘ ሲሆን ችሎቱ በመሙላቱ ሳብያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ከፍርድ ቤቱ ውጪ ቆሞ መጠበቅ ግድ ሆኖበታል፡፡ የችሎቱ ፀጥታ አስከባሪ ፖሊሶችም በጥሩ ሰነምግባር ጎደለ ቦታ በማየት ሰዎችን እየጠሩ ሲያስገቡ ተሰተውሏል፡፤
ኡስታዝ አቡበከር አህምድ ያቀረቡትን ፅሁፍ ጭብጥ በዝርዝር በአላህ ፈቃድ ለማቅረብ ይሞከራል፡፡
አላሁ አክበር!!!
አላሁ አክበር!!!
Minilik Salsawi
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen