Netsanet: ኢቲቪ የአንድነት ፓርቲን ስም ማጥፋቱ በፍርድቤት ተረጋገጠ::

Dienstag, 1. April 2014

ኢቲቪ የአንድነት ፓርቲን ስም ማጥፋቱ በፍርድቤት ተረጋገጠ::

April 1/2014
ኢቲቪ የአንድነት ፓርቲን ስም ማጥፋቱ በፍርድቤት ተረጋገጠ::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎ETV‬ ‪#‎UDJ‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Akeldama‬ ‪#‎Blueparty‬ ‪#‎Freedom‬
ኢቲቪ ተመጣጣኝ የማስተባበያ አየር ሰዓት ለአንድነት ፓርቲ እንዲሰጥ ታዟል::
የዘገየ ፍትህ እንደተሰጠ ባይቀጠርም በአንድነት ፓርቲ እና በኢትጵያ ቴሌቪዥን መካከል “አኬልዳማ ዘጋቢ ፊልምን አስመልክቶ ለነበረው 3 አመታትን ለፈጀ ክርክር ለአንድነት ፓርቲ ፈርዶ መቋጫ ሰጥቶታል በመሆኑም ኢ.ቲ.ቪ የአንድነት ፓርቲን ስም በማጥፋቱ ተመጣጣኝ የማስተባበያ አየር ሰዓት ለአንድነት እንዲሰጥ ፍርድቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ችሎቱን የተከታተለው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሀብታሙ አያሌው ለፍኖተ ነፃነት ....... “ውሳኔው የአንድነት ፓርቲ ክስ ኢ.ቲቪ የሰራው አኬልዳማ ዶክመንተሪ የፓርቲውን መልካም ስም እና ክብር ለማጥፋት ሆን ተብሎ የተፈጸመ ህገወጥ ድርጊት ነው የሚል ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱም በአንድነት ላይ በደል ተፈፅሟል ሲል ኢቲቪ ጥፋተኛ ነው ያስተባብል ሲል ወስኖበታል፡፡”
በማለት አስተላልፏል፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen