Netsanet: ተጨማሪ የአንድነት አባላትና መዋቅሮች ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

Montag, 9. Februar 2015

ተጨማሪ የአንድነት አባላትና መዋቅሮች ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

ጥር 26/2007 ዓ.ም የቀድሞው የአንድነት አባላትና መዋቅሮች በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን ተከትሎ ተጨማሪ የአንድነት አባላትና መዋቅሮች ሰማያዊ ፓርቲን እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ የፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ከጥር 28/2007 ዓ.ም በኋላ ሰማያዊ ፓርቲን ከተቀላቀሉት መካከል የትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር፣ ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ፣ ሀረር፣ አርባምንጭ፣ ወላይታ፣ ቁጫ፣ ቦንጋ፣ ኢልባቡር፣ ሰሞን ሸዋና የጉጂ የአንድነት መዋቅሮች ሙሉ በሙሉ ከሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር ጋር መቀላቀላቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ በቀጣዩ ቀናትም ወደ ሰማያዊ የሚቀላቀሉ መዋቅሮችና በግላቸው የሚመጡ አባላት እንዳሉ ኃላፊው ግልጸዋል፡፡
‹‹በአንድነትና መኢአድ ላይ የተወሰነው ውሳኔ የሰላማዊ ትግሉን ለማዳከም የተደረገ ሴራ ነው›› ያሉት አቶ ስለሽ ፓርቲያቸው ላይ ህገ ወጥ ውሳኔ የተላለፈባቸው የአንድነት አመራሮችና አባላት ተስፋ ሳይቆርጡ ወደ ሰማያዊ ፓርቲ መምጣታቸውና ሰማያዊ ፓርቲም እነዚህን ታጋዮች እጁን ዘርግቶ መቀበሉ የታሰበውን ሴራ ያከሸፈና ሰላማዊ ትግሉን የሚያጠናክር ነው ብለዋለል፡፡ አቶ ስለሽ አክለውም የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም ትግሉን ለማጠናከር ኢትዮጵያውያን የቻሉትን ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen