Netsanet: ማኅበረ ቅዱሳን በሚኒሶታ የቴሌቭዥን ስርጭት ጀመረ

Sonntag, 15. Februar 2015

ማኅበረ ቅዱሳን በሚኒሶታ የቴሌቭዥን ስርጭት ጀመረ



(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ የማኅበረ ቅዱሳን የሚዲያ ክፍል ሃላፊ( ተጠሪ) የሆኑት አቶ መለሰ አበበ ለዘ-ሐበሻ እንዳስታወቁት ማኅበረ ቅዱሳን በሚኒያፖሊስ እና በሴንት ፖል ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሆን የቴሌቭዥን ስርጭት ጀመረ:: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ማኅበረ ቅዱሳን የሚኒያፖሊስ ንዑስ ማዕከል በየሳምንቱ እሑድ በሚኒያፖሊስ እና በሴንት ፖል ከተሞች የቴሌቪዥን ፕሮግራሙን የሚያቀርብባቸው ቻናሎች:- ሴንት ፖል SPNN Channel 14 እሑድ 12:30pm-1:30pm እንዲሁም እሑድ 7:30pm-8:30pm ሲሆን በሚኒያፖሊስ MTN ደግሞ Channel 75 እሑድ ከ9pm-10pm መሆናቸው ታውቋል:: እንደ አቶ መለሰ ገለፃ ከሚኒያፖሊስ እና ሴንት ፖል ከተማ ውጭ ወይም አገር የምትገኙ መርሐግብሩን በተመሳሳይ ስዓት በኢንተርኔት ድረ ገጽ በቀጥታ መከታተል ይቻላል ብለዋል:: የኢንተርኔት አድራሻው Channel 75: http://www.mtn.org/channel 75 ነው::

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen