Netsanet: ናይሮቢ፥ የምክር ቤት አባልና አጃቢዎች ተገደሉ

Samstag, 7. Februar 2015

ናይሮቢ፥ የምክር ቤት አባልና አጃቢዎች ተገደሉ

ኬንያ መዲና ናይሮቢ ውስጥ ጭምብል ያጠለቁ ታጣቂዎች የሀገሪቱ አንድ የምክር ቤት አባልን ዛሬ አውራ ጎዳና ላይ ተኩሰው በመግደል መሸሻቸው ተገለጠ።

Nairobi Kenia Abgeordnete Parlament Debatte Sicherheitsgesetz 18.12.2014
በተኩስ ሩምታው የኬንያ የምክር ቤት አባል የሆኑት ጂዮርጅ ሙቻይ እና ኹለት የግል ጠባቂያቸው እንዲሁም የመኪናአሽከርካሪያቸው መገደላቸውን የናይሮቢ ፖሊስ እዝ ኃላፊ ፓውል ዋንጃማ አስታውቃዋል። ባለሥልጣኑ እናአብረዋቸው የነበሩት ሦስቱ ሰዎች የተገደሉት ከአንድ ሸቀጥ መደብር ጋዜጣ ለመሸመት መኪናቸውን ባቆሙበት ቅጽበትእንደነበረም ተጠቅሷል። የሟቹ ባለስልጣን ልጆች እና ቤተሰቦች በሌላ ተሽከርካሪ ከኋላ ይከተሉ እንደነበረም ተዘግቧል።አራቱ ሰዎች የተገደሉት ደረታቸው እና ጭንቅላታቸው ላይ በጥይት ተደብድበው ነው ተብሏል። የኬንያ የቀድሞውጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ «ኬንያ እየደማች ነው፤ ፍርኃት እና ተስፋቢስነት በሀገሪቱ እየተዛመተ መጥቷል»ብለዋል። ኬንያ በሶማሊያ ወታደሮች ማሰማራቷን ተከትሎ የሶማሊያን መንግስት የሚወጉት ታጣቂዎች የበቀል ጥቃትለመሰንዘር መዛታቸው ይታወሳል። ግድያውን ተከትሎ በኬንያ ከፍተኛ የደኅንነት ስጋት መከተሉም ተጠቅሷል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ልደት አበበ

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen