Netsanet: በአሰሪዎቾ የታገተችው ኢትዮጵያዊት የሰቆቃ ደምጽ !

Mittwoch, 25. Februar 2015

በአሰሪዎቾ የታገተችው ኢትዮጵያዊት የሰቆቃ ደምጽ !

ገነት አበበ ሞላ ትባላለች የልጅነት ግዜዎን ሩጣ ያልጠገበች በ አስራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ ኮረዳ ነች። ከዛሬ 3 አመት በፊት ነበር በኑሮ ውድነት የተጎሳቆሉ ቤትሰቦቾን ከደህንነት ለመታደግ በወቅቱ እስከ ገጠር በዘለቀው የአሰሪና ሰራተኛ የደላሎች ዘመቻ ከአርሲ ኮሌ ወረዳ ኩዬ ከተማ ተመልምላ የማይጨበጠውን የአረቡን ዓለም መከራ ለመጋፈጥ፡ተስፋ ሰንቃ ወደ ሳውዲ አረቢያ ያቀናቸው ። በወቅቱ በስው ልጆች ህይወት ዶላር ለማግበስበስ በየአካባቢው በተከፈቱ የአሰሪና ሰራተኛ ኤጀንሲ ደላሎች ከእናቶቻቸው ጉያ ተነጥቀው ለአቅመ ሄዋን ያለደረሰውን እድሜዎቻቸውን ቆልለው ፓስፖርት የወሰዱ ህጻናት ሳይቀሩ በቀን ከስክ 1500 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የኮንተራት ሰራተኞች የለህይወት ዋስትና ወደ ሳውዲ አረቢያ በጅምላ ይላኩ የነበረበት ወቅት በመሆኑ ወጣት ገነትም ሰው እንደሆነው እሆናለሁ ብላ በፌስታል የተሞሉ ልብሶቾን እንደነገሩ ይዛ ነበር የምተወዳቸውን ወላጆቾኝ በዕንባ የተሰናበተቸው ። አንድም ቀን ከቤት ወጥታ የማታውቀው ገነት አስረክበው ወደ ቀዬያቸው የተመለሱ ወላጆቾ የገነትን ድምጽ ቢናፍቁም ባህር አቋርጣ ሳውዲ ሄደች ከተባለ ወዲህ ወራት ተቆጥረው ዓመት ቢደፍንም ገነትን የበላ ጀብ አልጮህ አለ ።
ወትሮስ ለማን አቤት ሊባል ? « የገነትን ስቃይ ማን ይወቅላት » ክፉ አጋጣሚ ሆኖ በአሰሪዎቾ « ኃይል» ወደ ሚባል ገጠራማ የሳውዲ ግዛት ለስራ የተወሰደችው ገነት ወግ ባህሉ ቋንቋው ባዕድ በሆነባት ሃገር ሁሉም ነገር እንዳሰበቸው እና እንደተነገራት አልነበረም። ታዲያ ገነት ከቤትሰቦቾ ጋር ስትለያይ ሲያነቡ የነበሩት አይኗቾ እንባ እንደቋጠሩ ነበር ፍጹም ከባድ የሆነውን የአረቡን ዓለም የቤት ስራ የተጋፈጠቸው ፡፤ በማለዳው ምናምን ቢጤ ቀማምሳ ለአመታት ተጠርጎ የሚያውቀውን አቧራ የለበስና ቆሻሻ የተከመረበትን ግቢ ከአሰሪዎቾ በምለክት በተሰጣት ተዕዛዝ ስታፀዳና ከ 4 ያላነሱ መኪኖችን ስታጥብ የዋለቸው ። በዚህ መልኩ ለወራት የተዋሃዳትን የአሰሪዎን የቤት ውስጥ ስራ ጨምሮ የማይመለክታትን ከባድ ስራዎች ሁሉ ካጠናቀቀች በኃላ ለሌላ አረብ ተላልፋ እይተሰጠች የቤት ሰራተኛ ለሌላቸው የሰፈሩ አረቦች ሁሉ አገልጋይ ሆናለች ። ገነት እረፍት የላትም እንደ ዘበኛ መኪና በመጣ ቁጠር የግቢ በር ትከፍታለች የአሰሪዎቾን መኪናና ግቢ ታጥባለች ከባድና ቀላል የሆኑ እቃዎችን እስከ 3ኛ ፎቅ ተሸክማ በመውጣት ከአቅሞ በላይ የሆነና የማይመለከታትን ስራ በግዳጅ እንድትሰራ ትደረጋለች። ከቤተሰቦቾ ከተለየች ወዲህ በስልክ ወላጆቾን አጊታቸው የማታውቀው ገነት ከሥራው ክብደት ይልቅ በናፍቆት ከሰውነት ጎዳና የወጣው ስውነቷና የልጅነት ወዝዎ በቁም የተገነዘች ሬሳ አስመስሏታል ፡፡
በአስሪዎቾ ታግት በደል የሚፈጸምባት ገነት ከሚፈፀምባት ግፍ እና በደል እግር ወደ መራት በመሄድ እርሷን ከባርነት ለመታደግ የሞከርቸበትም አጋጣሚ እደነበር ይነገራል። ከዚያ ወዲህ ገነትን ለማግባባት ብዙ ሞክረው እንዳልተሳካላቸው የተረዱት አሰሪዎቾ ገነት ላይ የሚያደርጉትን ክትትል በማጠናከር የስራ ግዳጆዎን ስትጨርስ ባዶ ቤት ይቆለፉባታል። የቤት ሰራተኛ እጥርት የገጠማት ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በአሰሪዎቾ የታገተቸው ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ገነት አበበ ለአሰሪዎቾ እያበረከተች ካለው ነጻ አገልግሎት ባሻገር በወር እስከ 3800 በሚደርስ ክፍያ ለሦስተኛ ወገን ተላልፋ በመሰጠት ጥሩ የገቢ ምንጭ እስከ መሆን መድረሷ ይነገራል። ከአንዱ የአረብ መኖሪያ ወደ ሌላው የአረብ መኖሪያ ቤት እይተቀባበሉ ያለ በቂ እረፍት የአረብ አገልጋይ ለመሆን የተገደደቸውን ኢትዮጵያዊት የኮንተራት ሰራተኛ ከማለት ይልቅ በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ህጋዊ ፈቃድ አጊቶ በሚንቀሳቀስ አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ የተሸጥች ባሪያ ማለት ይቀላል።
አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ ሚክሲኮ አደባባይ አካባቢ ሴብሪን « sebirn » እይተባለ በሚጠራ አንድ ኤጀንሲ አማካኝነት ተዋውላ ህጋዊ በሆነ መንገድ ለስራ ሳውዲ እንደገባች የሚነገርላት ገነት ዛሬም የይደርሱልኝ ይሰቅቃ ድምጾን ታሰማለች ፡፤
አሁን አሁን ለህይወቷ የምትሳሳው ገነት ይገሉኛል በሚል ስጋት በድብደባ ከተጓሳቆለው አካሏዎ ባሻገር ሌሎች ምስጢራዊ በደሎችን ለግዜው ከመግለጽ መቆጠቧን ለልጅቷ ቅረበት ያላቸው ወገኖች ይገልጻሉ። እነዚህ ወገኖች አቤቱታቸውን በጅዳ ለኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ቢገልጹም እስክ አሁን የገነት የሰቆቃ ድምጽ ምላሽ አላገኘም፤
Ethiopian Hagere Jed Bewadi

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen