April 7/2014
የዘር የሃይማኖት የፖለቲካ ጽንፈኝነት ሳይጋርደው ይህን ከርታታ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ባልደረባ ከቤተሰብ አልባነት ለመታደግ ይህን ሊንክ በማድረግ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይጠበቅብናል ። ወደ ሙሉ ታሪኩ ይግብ
መጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ገለልቻ እባላለሁ ከ1970 ዓ.ም ጀምሮ በውትድርና ስኖር በ1971 ዓ.ም ኤርትራ ሀገር ሄጄ ከ1ዓመት ቆይታ በኋላ ከወ/ሮ ወይኒቱ ወንድዬ ከ1972 እስከ 1983 ዓ.ም ትዳር መስርቼ አብሬ ስኖር 3 ልጆችን ማፍራት ችያለሁ የልጆቼም ስም 1ኛ. ገመቹ ጉርሜሳ በ1976 ዓ.ም የተወለደ ፣2ኛ. ምህረት ጉርሜሳ በ1977 ዓ.ም የተወለደች ፣ 3ኛ. ሚካኤል ጉርሜሳ የመጨረሻው ልጄ ሲሆን በ1983 ዓ.ም እኔ ግንባር ላይ በነበርኩበት ወቅት ቤተሰቦቼን እየተመላለስኩ እረዳና እጠይቅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ጥቅምት 16 1983 ዓ.ም አዲስ አበባ (ሆለታ ገነት) ለኮርስ ሜጀር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሌ ማሠልጠኛ ተቋም ገባሁ ፡፡በዚያን ወቅት የ9 ወር ስልጠና ወስጄ ልመረቅ ስል ኢህአዴግ ስልጣን ያዘ እና ወደ አስመራ መሄድ አልቻልኩም ፡፡ በስልጠናው ወቅት በደብዳቤ ፣በስልክ ከቤተሰቦቼ ጋር ስንገናኝ የነበረ ሲሆን ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ስልጠናው የተቋረጠ ሲሆን እኔም በእስር ለአመታት ቆይቻለው ፡፡ በ1988 ዓ.ም እስከ 1992 ዓ.ም ስለ ቤተሰቦቼ የተወሰነ መረጃ ባገኝም እነሱን ግን በአካል ለማግኘት ብጥርም አልተሣካልኝም፡፡ እናም ወዳጆቼ እነሱን ማግኘት በጣም ነው የምፈልገው ና ቤተሰቦቼ በፊት ይኖሩ የነበረው ቦታም አስመራ ከተማ ልዩ ስሙ ትልቁ ገጀረት አካባቢ ነበር፡፡ እባካችሁ አድራሻቸውን የምታውቁ ካላችሁ በ 09-35-32-60-98 /011-8-96-76-73 / ደውሉልን፡፡ ወዳጆቼ ሼር በማድረግ ተባበሩኝ !
Ethiopian Hagere መጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ገለልቻ በውስጥ መስመር የደረስኝ
Ethiopian Hagere መጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ገለልቻ በውስጥ መስመር የደረስኝ
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen