April 7/2014
Minilik salsawi
ሼኽ መከተ ሙሄ ይባላሉ፡፡ የ47 አመት ጎልማሳ ሲሆኑ በጣም የተከበሩ የሀይማኖት ሰው ናቸው፡፡ በጥር 2004 የቋቋመው እና የ 3ቱን የህዝበ ሙስሊሙን ጥያቄዎች ይዞ ሲንቀሳቀስ በነበረው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የነበሩ በመሆናቸውና በህጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድም ለመንግስት የመብት ጥያቄ በማቅረባቸው አሸባሪ ተብለው ከተያዙበት ሐምሌ 2004 ጀምሮ በማእከላዊ እና ቂሊንጦ ለብዙ ግፍ እና ስቃይ ተዳርገዋል፡፡
ዛሬ በዋለው ችሎት መከላከያ ቃለቸውን ያቀረቡት የቀድሞው የሸሪዓ ፍርድቤት ፕሬዝደንት ሼኽ መከተ ሙሄ በማእከላዊ የደረሰባቸውን አሰቃቂ ስቃይ (የቶርቸር ምርመራ) አጋልጠዋል፡፡ ራሳቸውን መርማሪ ብለው በሚጠሩ ግለሰቦች ለተከታታይ ድብደባ መዳረጋቸውን፣ራቁታቸውን በማድረግና ብልታቸውን በመግረፍ በራሳቸውና በጓዶቻቸው ላይ በግድ እንዲመሰክሩ የተፈፀመባቸውን ዘግናኝ ስቃይ ዘርዝረው አስረድተዋል፡፡
ፍትህ ከአላህ እነጂ ከሌላ አንጠብቅም!
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen