Netsanet: የፊታችን እሁድ የእሪታ ቀን መጋቢት 28 2006 በአዲስ አበባ በደመቀ መልኩ ይደረጋል

Donnerstag, 3. April 2014

የፊታችን እሁድ የእሪታ ቀን መጋቢት 28 2006 በአዲስ አበባ በደመቀ መልኩ ይደረጋል

April 3/2014
‪#‎Ethiopia‬
፤;

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የእሪታ ቀን በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በተያዘለት ቀንና ቦታ እንደሚካሄድ ለመገናኛ ብዙሀን ካሳወቀበት ከትላንትናው እለት ማለትም መጋቢት 24/2006 ዓ.ም ጀምሮ ለከተማዋ ነዋሪዎች ስለሰልፉ ዓላማ የሚገልፅ በራሪ ወረቀት
እያሰራጨ ይገኛል፡፡
እስካሁን ድረስ ከ10.000 ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶች ተሰራጭተዋል ፡፡
የነገውን ቅስቀሳ የአንድነት ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ እና የአዲስ አበባ ከተማ የአንድነት ስራ አስፈፃሚ እንዲሁም የሁለቱ ምክር ቤት አባላት ይመሩታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen