Netsanet: የዚህ 'መንግስት' ጭካኔ….እሰከ ብልት መግረፍ….(Part 2)

Montag, 7. April 2014

የዚህ 'መንግስት' ጭካኔ….እሰከ ብልት መግረፍ….(Part 2)

April 7/2014

ሼኽ መከተ ሙሄ ይባላሉ፡፡ የ47 አመት
ጎልማሳ ሲሆኑ በጣም የተከበሩ የሀይማኖት ሰው ናቸው፡፡ በጥር 2004 የቋቋመው እና የ 3ቱን የህዝበ
ሙስሊሙን ጥያቄዎች ይዞ ሲንቀሳቀስ በነበረው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የነበበሩ በመሆናቸውና በህጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድም ለመንግስት የመብት ጥያቄ በማቅረባቸው አሸባሪ ተብለው ከተያዙበት ሐምሌ 2004 ጀምሮ በማእከላዊ እና ቂሊንጦ ለብዙ ግፍ እና ስቃይ ተዳርገዋል፡፡
ዛሬ በዋለው ችሎት መከላከያ ቃለቸውን ያቀረቡት የቀድሞው የሸሪዓ ፍርድቤት ፕሬዝደንት ሼኽ መከተ ሙሄ በማእከላዊ የደረሰባቸውን አሰቃቂ ስቃይ (የቶርቸር ምርመራ) አጋልጠዋል፡፡
"ነሀሴ 5 2004 ከፍተኛ የሆነ እንግልት
ደርሶብኛል በዕለቱ አንድ መርማሪ ወደኔ በመምጣት አይኔን በጨርቅ
ከሸፈነ በሀላ ይዞኝ ከታሰርኩበት በማስወጣት ብዙ ደረጃ እያስወጣና
እያስወረደ ወደ አንድ ክፍል ካስገባኝ
በሀላ ፊቴ ላይ የነበረውን ጨርቅ በመፍታት በመርማሪ ተክላይ መሪነት
ሙሉ ልብሴን በማስወለቅ 2,000
ቁጭ ብድግ ስራ ብለውኝ በመስራት
ላይ እያለሁ ከፍተኛ ድካም ደክሞኝ
ተዝለፍልፌ በምወድቅበት ሰዓት ጉልበቴን መቆም እስኪያቅተኝ በመግረፍ ያሰቃዩኝ ሲሆን ከዛም
በመቀጠል ብልቴን በተለያዩ መንገዶች
በመጉዳት ሲያሰቃዩኝ ከቆዩ በሀላ
እራሴን ስቼ ወድቄ የነበረ ሲሆን
መርማሪዎቹም ውሀ በማምጣት
ሲደፉብኝ የነቃሁ ሲሆን በማስከተልም
ውሀ ውስጥ በመዘፍዘፍ ከፍተኛ እንግልት ካደረሱብኝ በሀላ አይኔን
በድጋሚ በጨርቅ በማሰር አንድ ሰው
ወደተወሰነ ቦታ ከወሰደኝ በሀላ ጥሎኝ
የሄደ ሲሆን መቆም ስላቃተኝ
ግድግዳውን ተደግፌ በቆምኩበት ሰዓት አንድ የማረሜያ ቤቱ ፓሊስ ወደኔ በመምጣት ምን ትሰራለህ እዚህ? ለምንስ አይንህን አሰርክ በሚለኝ ሰዓት ማን እዚህ ቦታ እንዳመጣኝ እንደማላውቅና አይኔን እንዳሰሩኝ ነግሬው ፍታውና ከዚህ ሂድ በሚለኝ ሰዓት መፍታት አቅሙ እንደሌለኝ ስነግረው እሱ አይኔን ፈቶልኝ ወዳመጡኝ ክፍል በመውሰድ የጣሉኝ ሲሆን እዛ ጥለውኝ በሚሄዱ ሰዓት ማንም አጠገቤ ባለመኖሩና ቁስሌን እንኳን በቫዝሊን ሚያሽልኝ ሰው በማጣቴ ከፍተኛ ሀዘንና ጉዳት
ደርሶብኛል። ሀላችንም በየክፍሉ ለብቻችን በነበርንበት ሰዓት ክፍሎቻችን ጎን ለጎንና ፊት ለፊት ስለነበረ እነ ኡስታዝ ያሲን፣ አህመዲን እና ሌሎቹም ተሰቃይተው ወደየክፍላቸው እያለቀሱ ሲመጡ መስማት አንጀት የሚበላ አሳዛኝ ድርጊት ነው።"የሱፍ ጌታቸው

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen