April 7/2014
እሁድ፤ መጋቢት 28/2006፤ ፈሰቢር፡-
በማዕከላዊ ከወያኔ በኩል የደረሰባቸው ስቃይና መከራ!
ኡስታዝ አቡበከር ማክሰኞ መጋቢት 23/2006 ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ልደታ (ልዩ) ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ባቀረበው የክስ መከላከያ ላይ የወያኔን ማንነት ላልተረዱ የወያኔን ጭምብል ከፊቱ ላይ መንጭቆ በመጣል አንባገነንነቱን እና እንዲሁም ጨቋኝ እና ረጋጭ የሆነ ጨለምተኛ አገዛዝ መሆኑን በጉልህ አሳይቷል፡፡
ጀግናው የኮሚቴዎቻችን ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር በማዕከላዊ ማሰቃያ ቤት በእሱ ላይና በሌሎቹ የሰላም አምባሳደሮች ላይ የዓለም አቀፍ እና የሀገርኛ ህጎችን ሙሉ በሙሉ በናደ መልኩ በወያኔ የተፈጸመባቸውን ሰቆቃና ግፍ እንዲህም ገልጾት ነበር፡-
“በፍላጎት ጾም፤ በግዳጅ ረሀብና በእንቅልፍ ክልከላ የተዳከመን የተከሳሾችን አካል በመደብደብና ቁጭ እና ብድግ ማለትን ጨምሮ አጆቻቸው በካቴና ታስሮ እንገታቸው ውስጥ አስገብቶ ፂማቸውን በመንጨት፣ ለህግና ለሞራል ተቃራኒ የሆኑ ዘግናኝ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን እስከ ለሊቱ 8፡00 ሰዓት ያለፋታ እንዲሰሩ ያደረጉ ሲሆን በሰብዓዊ ፍጡር ለማይቻሉ 16 ሰዓታት ለህልፈት በተቃረበ ነፍሳቸው ያለ እረፍት እንዲቆሙም በማስገደድ ክፉኛ አሰቃይተዋቸዋል።
ጤናን ወዲያውኑ በሚያቃውስ ቀዝቃዛና ጨለማ ቤት ውስጥ ለረዥም ጊዜ ለየብቻ አስረዋቸዋል፤ ከፊል ተከሳሾችን እርቃናቸውን በማድረግ እያሰቃዩ ቃላቸውን ተቀብለዋል”
ይህን ይመስላል እንግዲህ የወያኔ ጨለምተኛ ኋላቀር አገዛዝ።
ሀገር በተቀነባበረ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ አትመራም!
ለዲናችን እንሞታለን!
አላሁ አክበር!
ለዲናችን እንሞታለን!
አላሁ አክበር!
Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen